TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰላም ሚኒስቴር ምን አለ ?

* ጋዜጠኞች ምላሽ እንዳይሰሙ እንዲወጡ ተደርጎ ምላሽ በዝግ ተሰጥቷል።

የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርቦ ነበር።

የሰላም ሚኒስቴር ባቀረበው ሪፖርት፦
- የጎሣ ግጭቶች #ስለመቀነሳቸው
- በክልሎች ውስጥ እንጂ፣ በክልሎች መካከል የሚደረግ ግጭትም እየቀነሰ ስለመሆኑ አስታውቋል።

ከቋሚ ኮሚቴው ግን ብዙ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። 

በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሐን ላይ ጉዳት እየደረሰ፤ እየሞቱ፤ እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው ስለመሆኑ እንዲሁም የሕዝብ የመንቀሳቀስ መብት እየተገደበ ፣ መንገድም የተዘጋባቸው አካባቢዎችም ያሉ መሆናቸው ተነስቶ ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ምን ሠሩ ? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። 

ግጭቶች መታየት እና የታጠቁ ኃይሎች ሕግን የመጣስ፣ ሰላምን የማደፍረስ ምክንያት ፤ በንፁሃን ዜጎች ሕይወት፣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ፣ ንፁሃን እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቁ ስለመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ለሚኒስቴሩ አመራሮች ሌሎች ጥያቄዎችም ቀርበው ነበር።

" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች በተለይ አሁን አማራ ክልል ያለው ፣ ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ጉዳይ ከግጭትም አልፎ የውስጥ የትጥቅ ግጭት-ከዚያም ሲያልፍ ወደ የእርስ በርስ ወደሚመስል ነገር የሚሄዱ ነገሮች ናቸው የሚመስሉት " የሚል ጥያቄ ተነስቷል።

በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በተመለከተ ግጭቱን #አመላካች ነገሮች አልነበሩም ወይ ? በሚል የግጭት ቅድመ መከላከል ላይ ምን ተሰራ የሚል ጥያቄም ቀርቦ ነበር።

ለዚህና ለሌሎች የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆን እንዳይከታተሉ ጋዜጠኞች የሰላም ሚኒስቴርን ሪፖርት እና የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች ብቻ ታድመው እንዲወጡ በሕ/ተ/ም/ቤት የውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመታዘዙ ምላሹን ምን እንደነበር አልታወቀም።

ለምን ይህ ለምን ይሆናል ? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ " በዝግ የሚደረግ " መሆኑን ከመግለጽ በቀር ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም። 

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ታዬ ምን አሉ ?

- መገናኛ ብዙሃን የሚኒስቴሩን ምላሽ እንዳይዘግቡ ተቋማቸው አለመከልከሉን ገልጸዋል።

- በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ቅድመ ትንተና እንደነበር፣ ሆኖም ግን " በሚመለከተው " ባሉት በግልጽ ባልጠቀሱት አካል ፋጣን ርምጃ ባላመውሰዱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

-  የአማራ ክልል ጉዳይ- " የተ/ም/ቤት ጭምር ሄዶ ህዝብ ባነገረትበ ጊዜ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች መኖራቸው ቀድም ብሎ ተለይቶ ነበር። ግን ችግሮችን ከመፍታትና አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነትና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል " ብለዋል።

- መንግሥት ከሕወሓት ጋር እንዲሁም ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በበጎ ጠቅሰዋል። በአማራ ክልል ያለውም በዚያው መንገድ " ሊታይ ይችላል የሚል እምነት " እንዳላቸው ገልፀዋል።

- " በመንግሥትም በኩል ረጅም መንገድ ሄዶ፣ በሌላ ወገን ያለውም ያለበት መንገድ አዋጭ እንዳልሆነ በማመን መሀል መንገድ ላይ መነጋገር ያስፈልጋል ተብሎ አቅጣጫ ተሰጥቶ በዛ ደረጃ እየተሰራ ይገኛል የአማራ ክልልም ጉዳይ በዚሁ ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚል እምነት አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

Credit - DW RADIO / ሰለሞን ሙጬ

@tikvahethiopia