TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አርባ_ምንጭ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። #PMO #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከወላይታ ሶዶና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው። #PMO
ምን ያህል ችግኝ ተተከለ?

√ኦሮሚያ 132 ሚሊዮን
√አማራ 38 ሚሊዮን
√ደቡብ 45 ሚሊዮን
√ትግራይ 8 ሚሊዮን 400 ሺህ
√አዲስ አባባ ከ3 ሚሊዮን በላይ

ይህ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በወላይታ ሶዶ እያደረጉት ባለው ስብሰባ ደርሷቸው የገለፁት ነው። #PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶክተር_አብይ_አህመድ

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ፦

#PMO የሲዳማ ዞን የክልልነት #ጥያቄን በተመለከተ፤ ክልል የመሆን ጥያቄው ለረጅም ዓመታት የነበረ መሆኑን እና ከለውጡ በኋላ ጎልቶ መውጣቱን አንስተዋል። የክልልነት ጥያቄው ከፖለቲካ በተጨማሪ #የሀብት_ክፍፍል እና ህጋዊ ሂደቶች ያስፈልጉታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ የክልልነት ጥያቄውን መሰረት በማድረግ ህዝበ ውሳኔው ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚከናወንም አስገንዝበዋል። #fbc

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጠባቂዎቻቸው ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ ችግኝ ተክለዋል።

Via #fbc/#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMO

የሴት ሚኒስትሮች የአመራርነት ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀ። ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው። በስልጠናው ላይ ሁሉም ሴት ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።

ስልጠናው ሴቶች በአመራርነት ወቅት የቤት ውስጥ ስራቸውን እና ማህበራዊ ህይዎታቸውን እንዴት አጣጥመው መሄድ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው ተብሏል። በስልጠናው ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን እና የቀድሞዋን የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍን ጨምሮ የአፍሪካ ሃገራት የስራ ሃላፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል።

ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ልምድ ያላቸውና ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የስራ ሃላፊዎች ስልጠና ሰጥተዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይም ሚኒስትሮቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ችግኝ ተክለዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMO

ጠ/ሚ ዶክተር #አብይ_አህመድ ብሄራዊ የኢንቨስትመንት እና የስራ እድል ፈጠራ መሪ ኮሚቴን ስራ አስጀመሩ። የብሄራዊ ኮሚቴው መቋቋም ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓ.ም በቢሯቸው ተወያይተዋል። የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል።

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል። በለውጡ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በውይይቱ የተነሡ ሲሆን፥ በአንዳንድ አካላት እየተፈጸሙ ያሉ ጥፋቶችን በማንሣት ጳጳሳቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም የእርሳቸውም ሆነ የመንግሥታቸው ፍላጎት የተጠናከረች፣ ለሀገር ግንባታ የሚቻላትን ሁሉ የምታደርግና አንድነቷ የተጠበቀ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማየት መሆኑን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት መጠናከርና አንድ መሆን ጥቅሙ ለእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

የቀረቡት ችግሮች በለውጥ ውስጥ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሡ ሲሆን፥ ዓይነታቸው ቢለያይም የተለያዩ የእምነት ተቋማት በለውጡ ሂደት ፈተና አጋጥመዋቸዋል፤ በመሆኑም ዕንቅፋት የሚፈጥሩትን አካላት መታገል ያለብን በጋራ ነው ብለዋል።

https://telegra.ph/ETH-09-06-2

Via #PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢንቨስትመንት ላይ ያለው ተጽዕኖ እና የመንግስት ምላሽ - #PMO

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚቃኝ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሀገር አቀፍ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የተከበሩ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተካሄደ።

በመርሃ ግብሩ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ፣ የተገኙ ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በተደረገ የመድረክ ላይ ወግ ፣ ዘርፉን ከሚመሩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ የፖነል ውይይት ተዳሰዋል።

በውይይቱ ወቅት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ረገድ ሀገራችን መልካም ጅማሮዎች እና ወሳኝ ምዕራፎች ላይ የምትገኝ መሆኗን አንስተው በመሰረተ ልማት፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሁም በዲጂታል ፋይናንስ የተሰሩት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አክለውም፣ መንግስት ለዲጂታል ጉዞ አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን በመግለጽ የግሉ ዘርፍ በበኩሉ በዲጂታል ሥነምህዳሩ የተፈጠረለትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በዘርፉ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት እንደሚገባው አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምናደርገውን ጉዞ በይበልጥ ለማፋጠን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ሃገራዊ ካውንስል እንዲቋቋም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #MINT
#PMO #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #ITU #SmartAfrica #HOPR #HOF

(ኢትዮ ቴሌኮም)