#Oromia
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትን በ20 በመቶ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወንኩ ነው አለ።
ይህን ያለው የክልሉ የትምህርት ጥራት ሽግግር የመጀመሪያው ጉባኤ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።
እንደ ቢሮው መረጃ ፦
- ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱት የክልሉ ተማሪዎች 1.8 በመቶ ብቻ ናቸው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡት።
- የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተኑት 518 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።
- የተመዘገበው የ12ኛ ክፍል ውጤት የትምህርት ጥራት ችግር እጅጉን አሳሳቢ መሆኑን ማሳያ ነው ብሏል። በዘንድሮው ፈተና ውጤቱን በ20 በመቶ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ሲል አሳውቋል።
- የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 40 በመቶ ብቻ ወደ ዘጠነኛ ክፍል አልፈዋል።
- በክልሉ የ8ኛ ክፍል ካስፈተኑት 9 ሺህ 585 ትምህርት ቤቶች መካከል 971 የሚሆኑት አንድም ተማሪ አላሳለፉም።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመለየት ጥናት ማካሄዱን ገልጿል።
በዚህ ጥናት መሰረት ፦
* 47 በመቶ የሚሆኑት መምህራን የተሰጣቸው የትምህርት ክፍለ ጊዜ በአግባቡ ያለመጠቀማቸው አንዱ ችግር መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።
* በትምህርት ዘርፉ የአመራር ሰጪነት ብቃት ማነስና የፖለቲካ አመራር አባላቱ ለዘርፉ ትኩረት ማጣት እንዲሁም የሱፐርቫይዘሮች ድጋፍና ክትትል ማነስ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው ሲል ገልጿል።
ክልሉ የትምህርት ጥራት ችግሮቹን ለመፍታት 15 ሺህ 520 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ከመገንባት ባለፈ ከ140 በላይ የሁለተኛ፣ ልዩና አዳሪ ትምህርት ቤቶች መገንባቱን ቢሮ አሳውቋል።
በተጨማሪ ብቁ መምህራን ለማፍራትና የመማር ማስተማር ስነ ዘዴን ለማሻሻል የሙያ ምዘና፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራ፣ የአይሲቲ ልማትና የትምህርት ቤቶች ደረጃ ማሻሻል ላይም እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
በዘንድሮው የ6ኛ፣ የ8ኛና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እየተሰራ ነው ብሏል።
🔵 በኦሮሚያ ክልል ከ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አሉ።
#ENA
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ አስታወቀ።
ካቢኔው ህዳር 16/2016 ከሰዓት በኃላ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በከባድ የድርቅ አደጋ ለተጎዱ መርጃ የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያስረዳል።
ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ፤ በተለይ በሦስት ዞኖች ፣ 12 ወረዳዎችና 47 ቀበሌዎች ከባድ የድርቅ አደጋ ማጋጠሙ ተከትሎ በርካታ ስዎችና እንስሳት ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል።
የተመደበው ገንዘብ በቂ እንዳልሆነ የጠቆመው መግለጫው ፤ የክልሉ ተወላጅ ባለሃብቶች ፣ ዳያስፓራዎችና የትግራይ ህዝብ ወዳጆች የሚቻላቸው ድጋፍ በማድረግ የወገንና የእንስሳት ህይወት እንዲታደጉ አደራ ብሏል።
በድርቅ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጠው ህዝብ ለማዳን የውጭ እርዳታ ከመጠበቅ የውስጥ አቅም አማጦ መጠቀም ወሳኝ ነው ያለው የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤቱ መግለጫ ይህንን ለመተግባር ጊዚያዊ አስተዳደሩ አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በባለፉት የክረምት ወራት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት በተለያዩ #የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ ጉዳት እየደረሰ ነው።
በተለይ አበርገለ ጭላ ወረዳ የበረታ ድርቅ በመከሰቱ የሰዎች ህይወት እንዲጠፋ ምክንያት እንደሆነ በርካቶችም ከቄያቸው ወጥተው ወደልመና እንዲገቡ እንዳደረጋቸው ተነግሯል።
መረጃውን ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

" ከዛሬ ጀምሮ የ24 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል " - ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር)
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው " አብርሆት ቤተ -መጻሕፍት " ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ 24 ሰዓት ማሳደጉን አስታውቋል፡፡
ቤተ-መጻሕፍቱ ከሕዳር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምሽቱ ስድስት ሰዓት አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ የቤተ-መጻሕፍቱ ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር) ገልጸዋል።
ከዛሬው ዕለት ጀምሮም የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል።
የቤተ-መጻሕፍቱ አገልግሎት ፈላጊ ቁጥር የአገልግሎት ሰዓቱን ለማሻሻል ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል።
በሌላ በኩል ቁጥር 2 የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሊገነባ መሆኑ የቤተ-መጻሕፍቱ ዋና ዳይሬክተር ውብአየሁ ማሞ (ኢ/ር) አሳውቀዋል። #ኤፍቢሲ

#AddisAbaba
የ32 ዓመቷ ወጣት በፖሊስ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ይገኛል ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ተመታ ህይወቷ አልፏል።
በፖሊስ አባል ጥቃት የደረሰባት ኢየሩሳሌም አስራት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃቱ ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና እና ሕክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረ ቢሆንም ህይወቷ ሊተርፍ አልቻለም።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ቀበሌ 25 ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰአት አካባቢ በወጣቷ ጓደኞች እና በሌሎች ሰዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በቦታዉ የደረሰዉ የፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ እንዳለፈ ተገልጿል።
እየሩሳሌም አስራት #ከጀርባዋ በመመታቷ ነው ህይወቷ ያለፈው።
ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደስ ፤ ወንጀሉን የፈፀመዉ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዉሎ " ለምን እና በምን ሁኔታ ዉስጥ ሊተኩስ ቻለ ? " የሚለዉ ጉዳይ እየተጣራ ነው ብለዋል።
ወደፊትም እንደ አስፈላጊነቱ የፍርድ ሂደቱ በመከታተል ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሐዱ ሬድዮ ኤፍ ኤም 94.3 ነው።

#ሙስና📈 " ዛሬ እኮ አገልግሎት ተፈልጎ ክፍለ ከተማ ቢኬድ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ፣ ተደብቆ ነው ሲሰጥ የነበረው " በኢትዮጵያ ውስጥ #ሙስና ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ፣ የሚፈፀምበትም መንገድ እየተራቀቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ ...…
የሙስናው መባባስ . . .
የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ፦
" ሙሰኞች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ጠንካራ ስላልሆነ ሙስና ከመቀነስ ይልቅ እንዲጨምር ሆኗል።
የፖለቲካ መዋቅሩ በራሱ አጥፊዎች እንዳይጠየቁ እድል የሚሰጥ ነው።
ሰዎች ሙስና ሰርተው ሲያጠፉ በግልፅ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጥፋተኛ መሆን ሲገባቸው እንደውም ከለላና ሽፋን ሲያገኙ ፣ ከበሉበት ቦታ ወደሌላ ቦታ ዘወር ሲሉ ፣ ሃብትና ንብረት እንዲያገኙ ሲመቻችላቸው ይታያል።
ይሄ ሁሉ የፖለቲካ ስሪቱ ነው። የፖለቲካ ስሪቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑነው። ይሄ ብሄርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት በሙስና ላይ የሰላ ትግል እንዳይደረግና ተጠያቂነት እንዳይመጣ ያደርጋል።
የፖለቲካ ስርዓቱ #ብሄር እና #ትውውቅን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአጥፊውና በጠያቂው መካከል ልዩነት እንዳይኖር ሆኗል።
መፍትሄው ሙስና የሚፈፅሙ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህጉን ጠንካራ ማድረግ ብቻ ነው። "

ሰላም አርባ ምንጭ!
የ07 ኔትዎርክን በመቀላቀል ማርሻችንን
ወደ ፈጣኑ ያልተገደበ ኢንተርኔት ፍጥነት ያለው 4G ኔትዎርክ እንቀይር።
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

" እርዳታው ከተላከ ከአንድ ሳምንት በላይ ሆኖታል እስካሁን ግን ቦታው ላይ አልደረሰም " - ቀይ መስቀል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ላጋጠመው ድርቅ እርዳታ ቢልክም እስካሁን ቦታው ላይ አልደረሰም። እርዳታው ቦታው ላይ ያልደረሰው በፀጥታ ችግር ነው ብሏል። የማህበሩ የፕሮግራም ኃላፊ አቶ ድረስ ደስይበለው ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ እርዳታው…
#ትኩረት
" ተጨማሪ ሁለት ሰዎች በረሃብ ህይወታቸው አልፏል። ... አካባቢው ረሃብ ብቻ ነው፤ እርዳታም አልመጣም ፤ ሰው እያለቀሰ ነው ያለው " - የቢላዛ ቀበሌ አስተደደር
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፤ ሳህላ ሰየምት ወረዳ ቀበሌ 10 አካባቢ ከረሃብ ጋር በተያያዘ ባለፉት አስር ቀናት ውስጥ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
የቢላዛ ቀበሌ አስተዳደር ሁለት ሰዎች በረብ እንደሞቱ ማረጋገጡን ገልጾ ወደ ሟቾች ቤት ሲኬድ የሚበላም ሆነ የሚጠጣ አንዳች ነገር እንዳልተገኘ አመልክቷል።
ወደ አካባቢው እርዳታ ሊገባ እንዳልቻለ ያመለከተው የቢላዛ አስተዳደር ነዋሪው በከፍተኛ ችግር እና ረሃብ ላይ ነው፤ አካባቢው ረሃብ ብቻ ነው ብሏል።
ከዚህ ቀደም በዚሁ ቀበሌ የመኸር ወቅቱ ድርቅ ባስከተለው ረሃብ 6 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በቅርቡ የሞቱትን አንድ አዛውንትና አንዲት ሴትን ጨምሮ የሟቾች ቁጥር 8 መድረሱ ተነግሯል።
ከ4 ሺህ በላይ ህዝብ በሚኖርበት በዚህ ቀበሌ እስካሁን 15 ኪሎ ግራም ፉርኖ ዱቄት የእርዳታ እህል ማግኘት የቻሉት 800 ሰዎች ብቻ ናቸው።
አስተዳደሩ በቂ የእርዳታ እህል እየቀረበ አይደለም ብሏል። አሁንም ቢሆን እርዳታ በአፋጣኝ ካልደረሰ የከፋ ችግር ይከሰታል ሲል አሳስቧል።
አካባቢው ለተሽከርካሪ የማያመች ሲሆን ከፍተኛ የመንገድ ችግርም አለበት። አሁን እየከፋ በመጣው ረሃብ ቀደም ሲል የገባውን እርዳታ ለማጓጓዝ ጥቅም ላይ የዋሉ አህያዎች በመኖ እጥረት ምክንያት አቅማቸው በመዳከሙ እርዳታ ቢገኝ እንኳን ማጓጓዝ አይቻልም ተብሏል።
ከመንገድ በተጨማሪ የክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ የእርዳታ እህል ለተጎጂዎች ለማድረስ አስቸጋሪ እንዳደረገው ተገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ሰሞኑን ወደ ዋግኽምራ ሳህላሰየትም ወረዳ ሊላክ የነበረው የእርዳታ እህል በፀጥታና ደህንነት ምክንያት ባህር ዳር ላይ ለቀናት እንደቆመ መግለፁ ይታወሳል።
የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ዋግኽምራ እንዳይሄዱ ብቸኛው መንገድ (በማክሰኚት - ምስራቅ በለሳ -አርባያ-ጉአላ) ምቹና አስተማማኝ ስላልነበር እርዳታውን ወደ ሌላኛው ከፍተኛ የድርቅ ተጎጂዎች ወዳሉበት ሰሜን ጎንደር ወረዳዎች እንዲሰጥ መደረጉን ቀይ መስቀል አሳውቋል።
ቀይ መስቀል እርዳታው ወደ ዋግኽምራ እንዳይሄድ የመንገድ ደህንነት ችግር በመሆኑ ከአዲስ አበባም ከወጣ 20 ቀን አካባቢ ባህርዳር ላይ በመቆሙ ከመበላሸቱ በፊት በድርቅ እኩል ለተጎዱ የሰሜን ጎንደር ወረዳዎች እንዲከፋፈል ተደርጓል ብሏል።
አስተማማኝና ምቹ ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ እርዳታው ወደ ሰሜን ጎንደር መላከው ያስረዳው ቀይ መስቀል ለሳሃላሰየምት ሌላ ድጋፍ ይፈለጋል ሲል አሳውቋል።
የዋግኽምራ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ወደ ቢላዛ ቀበሌም ሆነ ወደሌሎች አካባቢዎች እርዳታ እንዳይደርስ የመንገድ እና የፀጥታ ችግር ፈተና እንደሆነበት ገልጿል።
ከፌዴራል እና ከክልል መንግስት የተላከ እርዳታ ቢኖርም በቂ እንዳልሆነም ገልጾ በቀጣይ ወር ለተጎጂዎች የተዘጋጀ ምንም ሰብዓዊ ድጋፍ የለም ብሏል።
ስለሆነም፦
- መንግሥት
- መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት
- በጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ተማጽናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ቪኦኤ አማርኛው አገልግሎት ነው።

#Tigray የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለአስቸኳይ ህይወት አድን የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ አስታወቀ። ካቢኔው ህዳር 16/2016 ከሰዓት በኃላ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በከባድ የድርቅ አደጋ ለተጎዱ መርጃ የሚውል 50 ሚሊዮን ብር መመደቡ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያወጣው መግለጫ ያስረዳል። ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ፤ በተለይ በሦስት ዞኖች ፣ 12 ወረዳዎችና 47 ቀበሌዎች…
#ትግራይክልል
በትግራይ ላለፉት ሁለት አመታት የታየው የእርሻ ግብአት እጥረት ፣ ጊዜው ያልጠበቀ ዝናብ ፣ የአንበጣ መንጋ ወረራና የተካሄደው ጦርነት ተከትሎ በቂ የምግብ እህል ባለመገኘቱ በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች ደርቅ አጋጥሟል።
ባጋጠመው ድርቅ ምክንያትም በርካቶች ለሞት ፣ ለረሃብና ለመፈናቀል ተዳርገው እንደሚገኙ ተነግሯል።
የድርቅ ችግሩ ለማቃለል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሃብት የማሳባሰብ ጥሪ ማቅረቡ ተከትሎ ማሕበራዊ ረድኤት ትግራይ (ማረት) ደደቢት ማይክሮፋይናንስ እያንዳንዳቸው ብር 10 ሚሊዮን በድምር 20 ሚሊዮን ብር መስጠታቸው የተቋሞቹ ሃላፊዎች ይፋ አድርገዋል።
ተቋሞቹ የተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ከድርቅ ችግሩ ስፋት አንፃር በቂ ባለመሆኑ የአገር ውስጥና የአገር ውጭ ለጋሾች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
" ቫራይቲ " የተባለ የግል የንግድ ተቋም በበኩበደርቅ ለተጎዱ ወገኖች 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሰጥቷል።
በትግራይ ካለው ድርቅ ጋር በተያያዘ የሰው ህይወት ከመጥፋቱ በተጨማሪ ሰዎች ቄያቸውን ለቀው ወደ ልመና መግባታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ መቅረታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ፎቶ - ድምፂወያነ