TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሴጅ_ማሰልጠኛ_ኢንስቲትዩት

7ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy and Auditing) ስልጠና ምዝገባ ላይ ነን።

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

ስልክ ፡ 0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://t.iss.one/sagetraininginstitute
Tiktok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
#Hawassa

" አደጋ ለመከላከል ተብለው የተቀመጡ የፍጥነት መቀነሻዎች ወይም ስፒድ ብሬከሮች ምልክት ስለሌላቸው እራሳቸው የአደጋ መንስኤ እየሆኑ ነው " - ነዋሪዎች

" ችግሩ ጎልቶ የሚታይበትን ዋና መንገድ የሰራዉ የፌደራል መንግስት ነው የፍጥነት መቀነሻዎችን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክትም ሆነ ከርቀት እንዲታዩ የሚረዳ ቀለም የመቀባት ኃላፊነት አለበት " - የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት  መምሪያ

በሀዋሳ ከተማ ያሉ የፍጥነት መቀነሻዎች ወይም ስፒድ ብሬከሮች የአደጋ መንስኤዎች ሆነዉብናል ሲሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታቸዉን ገለጹ።

በከተማዉ የተለያዩ መንገዶች በተለይም ከተማዉን አልፎ በሚሄደዉ አዉራ ጎዳና ላይ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት ለመቀነስ በርካታ የፍጥነት መቀነሻዎች እንዳሉ ይታወቃል።

ይሁንና እነዚህ መቀነሻዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸዉ ከመሆኑ በተጨማሪ ለአካባቢው አዲስ ለሆኑ አሽከርካሪዎች ምልክት አለመቀመጡንና የተለየ ቀለም አለመቀባታቸዉን ተከትሎ ከፍተኛ አደጋ እየፈጠሩ ነዉ ሲሉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የከተማዉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸዉ የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት  ምክትል የመምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ በበኩላቸዉ ቅሬታዉን ቀድመዉ እንደሚያዉቁት ገልጸዋል።

ችግሩ ጎልቶ የሚታይበትን ዋና መንገድ የሰራዉ የፌደራል መንግስት መሆኑን በመግለጽ ለተሰሩ የፍጥነት መቀነሻዎችም ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክትም ሆነ ከርቀት እንዲታዩ የሚረዳ ቀለም የመቀባት ሀላፊነት ያለበት ራሱ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን መሆኑን ያነሳሉ።

አቶ አበራ አክለዉም አሁን ላይ ችግሩን ለመቅረፍ በቅርቡ ከፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ጋር ዉይይት ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዉ ምናልባትም ሀላፊነቱን የከተማዉ መንገድ ትራንስፖርት መቀበል ከቻለ ማስተካከያዎችን በቅርብ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

መረጃ ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OROMIA #Peace

" . . . እርቁ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

አቶ ጃዋር መሀመድ የኢፌዴሪ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ያደረጉት የሁለተኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት ከተበተነ በኃላ ድርድሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ምን አሉ ?

- መንግስትንና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO-OLA) ለማስታረቅ የተደረገው 2ኛው ዙር ሙከራ አለመሳካቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ነው።

- በሕዝቡ በኩል ቢያንስ ሁለቱም ወገኖች በዚህ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ ተደርጎ ነበር። በተለይ የጦር አዛዦች ከጦር ሜዳ ለውይይት መምጣታቸው እርቀ ሰላሙን ያሳካል የሚል ተስፋ ፈጥሮ ነበር።

- ድርድሩ አለመሳካት እንደ ትልቅ ውድቀት ሲቀርብ እናያለን ነገር ግን ውይይቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ርቀት ተጉዟል። እርቅ ከማያስፈልግበት ወይም ከማይቻልበት ደረጃ ተነስተን የሁለቱም ወገን አመራሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየት ደረጃ ደርሰናል።

- ይህ እርቅ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም። ተስፋ ልንቆርጥም አንችልም። ሌላ መፍትሄ የለንምና። ስለዚህ የሰላም ድርድሩ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።

🕊አቶ ጃዋር መሀመድ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ላይ ከተሳተፉት አካላት እና ከተለያዩ ምንጮች ተረዳሁት ያሉትንና ለቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር ያግዛሉ ያሏቸውን ሃሳባችን በዝርዝር አቅርበዋል።

➜ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ሁለቱም ወገኖች በእውነት #እርቅ/#ሰላም ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።

በዚህ የተነሳ ሁለቱም ወገኖች ልክ እንደ ህዝቡ ይህ ምዕራፍ በእርቅ ስምምነቱ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ (expectation) ይዘው ነበር የቀረቡት።

ሁሉም ተሳታፊዎች (WBO / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ መንግስት እና አሸማጋዮች) በሰላም፣ በእርቅ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ይዘው ስለሄዱ ግባቸው ላይ ባለመድረሳቸው የመናደድ ስሜት ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ምክንያት ለቀጣዩ የሰላም ውይይት በር ከመክፈታቸው በፊት ተለያይተዋል።

➜ ሁለቱም ወገኖች በቅን ልቦና ለመታረቅ ቢሄዱም፣ አንዱ ከአንዱ የሚፈልገውን (demands/concessions) ለመስጠት እና ለመቀበል ሙሉ በሙሉ የተዘጋጁ አይመስሉም።

በመጀመሪያው ዙር እርስ በርሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ተረድተው ተለያይተዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ አንዳቸው ለሌላው መስጠት የማይችሉትን ያወቁ ይመስለኛል።

አሁንም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነት ካላቸው፣ ቀጣዩ እርምጃ ሁለቱም ወገኖች ጥያቄዎቻቸውን ለማስተካከል (modifying demands) መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ማለት እንዱ መቀበል የማይችላቸው ነገሮች ላይ በመግፋት መጋጨት መተው አለባቸው።

በሰላም ድርድር ውስጥ የሚፈልጉትን እና ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማግኘት አይቻልም። ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማጣትም አይቻልም። ሁለቱም ወገኖች ወደ መካከለኛው አቋም መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

➜ የሰላም ድርድሩ ዋነኛው #እንቅፋት እየሆነ ያለው ዋና ምክንያት አንዱ ከአንዱ የሚፈልገው ነገር ላይ ተራርቀው ነው ብዬ አላስብም። ትልቁ እንቅፋት #አለመተማመን ነው። በሁለቱ ወገኖች በታሪክ ካለው ግንኙነት እና ከአገራችን የፖለቲካ ባህል አንፃር አለመተማመናቸው ይጠበቃል። የውጪው አካል ያስፈለገበትም ምክንያት ይሄ ችግር ስለተረዳ ነው። እነዚህ አስታራቂዎች የእርቅ ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህንን አሻሚ የሆነ ችግር ለማሻሻል ይጠቅማል።

➜ ከውስጥ ከውጭ " እርቅ ሊመጣ ነው " ብለው እያዘኑ የነበሩት ወገኖች አሁን በመፍረሱ በደስታ እየፈነደቁ ነው። ሌላ ዙር ድርድር እንዳይደረግም እያሴሩ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) እና የመንግስት አመራሮች አሁንም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል አቋም ካላቸው እነዚህ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ሁሉንም ክፍተቶች መዝጋት አለባቸው። በተጨማሪም የሚቀጥለውን ዙር እድሎች ከሚያጠብ ወይም ከሚያርቁ ድርጊቶች እና ቃላት መቆጠብ አለባቸው። ይህም የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የመስክ ውጊያን አለማባባስን ያካትታል።

➜ እኔ እስከተረዳሁት ድረስ ከ2ቱም ወገን ደጋፊዎች በኩል የነበረው የ " #ምታ - #ስበር - #አጥፋ " ዘመቻ ባለፉት አመታት በጣም መቀነሱን ነው። የእርቅ ሀሳብ መደገፍ እና ሰላም እንዲወርድ ያላቸው ምኞትም ከየትኛውም ጊዜ በላይ እያደገ መጥቷል።

➜ አሁንም የሁለተኛው ዙር ሙከራ ስላልተሳካ እርስ በርስ ጣት መቀሳሰር እና መደማማት ምንም ፋይዳ እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል። የሚጠቅመው የሚደግፉትን ወገኖች ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ እና የሚጠበቅባቸውን እንዲሰጡ ማበረታታት እና ጫና ማድረግ ነው።

➜ በመጨረሻም ፤ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ይሄ የሰላም ድርድር የጦር ሜዳ ውጤቶች አይደለም።

ሁለት የሚዋጉ ወገኖች ለእርቅ ድርድር የሚቀመጡት በሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ነው።

የመጀመሪያው ፦ በጦር ሜዳ ላይ አንደኛው የበለጠ የበላይነት አግኝቶ ወደ ድል ሲቃረብ እና ሌላኛው ወገን ሙሉ በሙሉ ከመሸነፉ በፊት ለመታረቅ ሲወስን ነው።

ሁለተኛው ፦ ከረዥም ጊዜ ጦርነት በኋላ ሁለቱም ወገኖች መሸናነፍ ካልቻሉ ነው። በWBO-OLA እና በመንግስት መካከል ያለው ጦርነት የመሸናነፍ ወይም የመድከም ደረጃ ላይ አልደረሰም። በአጭር ጊዜ ውስጥም እዚህ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም። ይህ ውይይት የመጣው በህዝብ እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ግፊት ነው።

በተለይም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትኩረት ያልተጠበቀ እና ትልቅ እድል ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት በፍጥነት እየተቀየረ ነው። ስለዚህ ፤ ጉዳያችን ትኩረት ባገኘበት በዚህ ወቅት በፍጥነትና በብልሃት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን እድል መጠቀም ካልቻልንና የሚባክን ከሆነ ለረጅም ጊዜ እንቆጫለን።

#JawarMohammed

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

#TikvahEthiopiaAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አህያ🫏 በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል። ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም ባለስልጣኑ የገለፀ ሲሆን ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካል እስከ…
#አህያ🫏

" ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ አለኝ " - አሰላ የሚገኘው የአህያ ቄራ

አሰላ ከተማ የሚገኘው የአህያ ማረጃ ቄራ " የአህያ ምርቶች በሙሉ ለቻይና ገበያ የሚቀርብ እንጂ አገር ውስጥ የሚቀር ምርት የለም " አለ።

" ሮግቻንድ " የተባለው የአህያ ማረጃ ቄራ አስተባባሪ የሆኑት ቺቺ አማን ቄራው በቀን ከ50 እስከ100 አህዮችን እያረደ ቆዳቸውን፣ ሥጋቸውን እና አጥንታቸውን ወደ ቻይና እንደሚልክ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ከአህዮች እርድ የሚገኙት ሁሉም ምርቶች " አንጥንታቸው እንኳ ሳይቀር ተፈጭቶ ወደ ውጪ ይላካል። እዚህ የሚቀር ምንም የለም " በማለት ተናግሯል።

" የአህያ ሥጋ ምርት ከበሬ ሥጋ ጋር ተመሳስሎ በልኳንዳ ቤቶች ለገበያ እየቀረበ ነው " ስለተባለው መረጃ ፤ አቶ ቺቺ " ይህ መረጃ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ነው " ብለዋል።

እርሳቸው የሚያስተዳድሩት ቄራ በግብርና ሚኒስቴር ክትትል እንደሚደረግበት ተናግረዋል።

ይህ ቄራ ባለፉት 3 ዓመታት የአህያ ቆዳ፣ ሥጋ እና አጥንት ወደ ቻይና ሲልክ መቆየቱን የሚገልጹት አስተባባሪው፤ በዓመት ከአንድ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ እንዳስገኘ ገልጸዋል።

ቄራው " በኢትዮጵያ የሚገኙ አህዮችን ቁጥር ያመናምናል " በሚል ለሚነሳው ቅሬታ አቶ ቺቺ " እኔ ይሄ እምነት የለኝም " ብለዋል።

ለእርድ ወደ እኛ የሚመጡት አህዮች " ከሞት የተነሱ ናቸው " ያሉት ቺቺ  ለእርድ የሚቀርቡት አህዮች አካላዊ የጤና ጉድለት ያለባቸው እና የአገልግሎት ዘመናቸውን እያጠናቀቁ ያሉ ናቸው ፤ አገለግሎት የሚሰጡ አህዮች ለቄራው አይቀርቡም ብለዋል።

" በጣም የተጎሳቆለ አገልግሎት የማይሰጥ ወንድ አህያ ነው ወደኛ የሚመጣው። ሴት አህያ እኛ ጋር ለእርድ አይቀርቡም። ገጠር ውስጥ ሰዎችን አደራጅተን ጀርባቸው የቆሰሉ፣ እግራቸው የተሰበረ ወይም ዐይናቸው ጠፍቶ ለአውሬ የተተዉ አህዮችን ፈልገን በመኪና ጭነን ነው የምናመጣቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የአህያ ቄራ እንዲዘጋ የሚጠይቁ ድምጾች መሰማታቸው ቢቀጥልም የአህያው ቄራ ግን ወደፊት ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸውን አህዮችን በማረድ ለአገር የማስገኘውን ጥቅም ከፍ ለማድረግ አቅጄ እየሰራሁ ነው " ብሏል።

በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 100 አህዮች እያረደ ሲገኝ ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ እንዳለው ገልጿል።

ለ250 ሰዎች የሥራ ዕድልን መፍጠሩን በማመልከት፣ በዚህም በአካባቢው የተደራጁ ወጣቶች ለእርድ የሚሆኑትን አህዮችን ፈልገው በመግዛት ለቄራው ያቀርባሉ ብሏል።

የአህዮቹ እርድ መከናወን እንዲችል ከአካባቢው ማኅብረሰብ ጋር ባለፉት ሁለት ዓመታት ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን በማንሳት " የአካባቢው ማኅበረሰብ ቄራው የእኔ ነው ብሎ አምኖ ተቀብሏል " ብለዋል።

የአህያ ሥጋ፣ ቆዳ እና አጥንት በቻይና ገበያ ተፈላጊ ነው።

ለዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ ምክንያቱ የቻይና ባሕላዊ መድኃኒቶችነ ለመሥራት የሚረዳው " ኢጂአኦ " የተባለ ንጥረ ነገር በአህዮች ውስጥ ስለሚገኝ ነው።

በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ የሚገኘው ቄራ ከዚህ ቀደም ወደ ሥራ መግባቱን ተከትሎ ተቃውሞዎች ተሰምተው ሥራው እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር።

በርካቶች በባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ምክንያቶች የአህዮች መታረድን በመቃወም ድምጽ ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተጨማሪም አህዮች ለገጠሩ ማኅብረሰብ በተለይ ለሴቶች የሚሰጡትን ግልጋሎት እንዲሁም ሰብዓዊነትን ከግምት በማስገባት የአህያ እርድን የሚቃወሙ በርካቶች ናቸው።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
የድህረ ክፍያ ወርሃዊ የሞባይል ጥቅሎች
ለድርጅት ደንበኞቻችን በተመጣጣኝ ዋጋ !

ከ200 ብር ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ከእንኳን ደህና መጡ መቀበያ እና ከተጨማሪ የዓለም አቀፍ ጥሪ ስጦታ ጋር የቀረቡትን ጥቅሎች በአቅራቢያዎ ከሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ይግዙ፤ የ2 ዓመት ውል በመግባት እስከ 45% የሚደርስ ተጨማሪ ያግኙ።

ለበለጠ መረጃ https://bit.ly/3MRIoEX

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
" ለተመራቂም ሆነ ለነባር እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ አልተደረገም " - ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለየትኛውም የተቋሙ ተማሪ ጥሪ እንዳላደረገ ገልጸ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከተቋሙ ጥሪ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

አንዳንድ የተቋሙ ተማሪዎች ፤ ከሶስት ቀን በፊት በዲፓርትመንት ኃላፊዎች በኩል ተመራቂ ተማሪዎችን ለመጥራት ስለመታሰቡ መስማታቸውን ፤ ትላንት ምሽት ደግሞ በክፍል ተወካዮች በኩል " ተመራቂዎች ከ19/03/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲገቡ መወሰኑንና በሰዓቱ መጥተው ሪፖርት እንዲያደርጉ " የሚል አጭር የፅሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ ጥሪ ምን ያህል እውነተኛ ነው ? የሚለውን ለማረጋገጥ ወልድያ ዩኒቨርሲቲን አነጋግሯል።

በተማሪዎች ጥሪና ቅበላ ዙሪያ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሀን ደጀን ፤ ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለየትኛውም የተቋሙ ተማሪ ጥሪ #አለመደረጉን አረጋግጠዋል።

ለተመራቂም ሆነ ለነባር እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ አለመደረጉን ኃላፊው ገልጸዋል።

የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ተሻሽሎ ተማሪዎች ለመጥራት የሚቻልበት ሁኔታ ሲፈጠር ወደፊት ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው የጠቆሙት።

በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቸው እስካሁን ጥሪ ያላደረጉ ሲሆን ተማሪዎችም ያለ ትምህርት ለወራት በቤታቸው መቀመጣቸውንና በዚህም ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተደጋጋሚ መጠየቃቸው አይዘነጋም።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
የተሽከርካሪዎች_ጨረታ_ጉምሩክ_ኮሚሽን_አዳማ_.pdf
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ !

" ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች

" በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ እንጠይቃለን " - ጉምሩክ ኮሚሽን

ከሰሞኑን የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ያወጣው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ውዝግብ የፈጠረ ሆኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ፤ " ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን በመጣስ 237 ተሽከርካሪዎች ለሐራጅ አወጣብን " በሚል ከሰዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ፤ " ምንም አይነት የህግ ጥሰት አልፈተፈፀም ህጉን እና አሰራሩን በተከተለ መልኩ ነው ተሽከርካሪዎቹ ለጨረታ የቀረቡት " ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-24

@tikvahethiopia
#ግሎባል_ባንክ_ኢትዮጵያ

በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ
ይገምቱ ይሸለሙ!!

ተጠባቂውን የማንቺስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሜሊግ ጨዋታ
1. ትክክለኛ ውጤት ግምት
2. ማን ጎል እንደሚያስቆጥር በትክክል ለሚገምቱ 5 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የ500 ብር ካርድ እንሸልማልን፡፡
ያስታውሱ ግምቱ ሽልማት የሚያስገኘው በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ ለሚገምቱ ነው ፡፡

ግምትዎን ይህን ሊንክ በመጠቀም ያስቀምጡ፡፡
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION🔊 በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ / ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው። እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ ፦ - በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79,828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል። - በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት  በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ…
#Update

" 10, 572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም " - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር

በዳሰነች ወረዳ ተከሰተ የተባለው የጎርፍ አደጋ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ ፣ በአደጋው የሰውና የእንስሳት ሕይወት እንዳለፈና እንዳላለፈ፣ በንብረት ላይ  ምን ያህል ውድመት እንደደረሰ  ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ማልኮ እንደገለጹት ከሆነ፣ 10,572 ሰዎች ደሴት ላይ ገና በውሃ ተከበው አልወጡም። እንዲሁም በጎርፍ አደጋው 4.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

69,256 ቤተሰቦች ከወንዙ እንደወጡ ያስረዱት ያሉት አስተዳዳሪው፣ 79,828 ሰዎች በአጠቃላይ በጎርፉ ጉዳት የደረሰባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም፣ እንስሳት የዳልጋ ከብት፣ በግና ፍየልን ጨምሮ 889,454 ከወንዙ እንደወጡ ገልጸው፣ "በጎረፍ አደጋ የሞተ የለም። እንስሳት ላይም ሞት የለም። ተቋማትና የአርብቶ አደር ቤቶች በጎርፍ እንደተያዙ ይገኛሉ" ብለዋል።

መፍትሄው ምን እንደሆነ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽም፣ መንግሥት ማህበረሰቡን ወንዝ ወደማይደረስበት ማስፈረና ትልልቅ የመስኖ አውታር በማቋቋም ወደልማት ፊታቸውን እንድያዞሩ ማድረግ፣ አስፈላጊው መሰረተ ልማት በሰፈሩበት ቦታ ማሟላት አለበት ብለዋል።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰሠረት ከኅዳር 15 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄደው የምኅላ ጸሎት በሁሉም አድባራትና ገዳማት በወጣለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በሀገሪቱ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነት እንዲሰፍን በሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናት ጾም፣ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸም መወሰኑ አይዘነጋም።

" የአሁኑ ጸሎተ ምኅላ የሚደረገው ፦
- አለመግባባት በምክክር፣ በውይይት፣ በመደማመጥ እንዲፈታ፤
- መከራን በመረዳዳት እንድንሻገር፣ እንደየ ኃላፊነታችን የሚጠበቅብንን ለመወጣትና የሕዝባችንን ጥያቄ ለመመለስ እንድንችል፣ ችግራችን ሁሉ ተፈትቶ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ከሃሊው አምላክ እንዲያግዘን በአንድነት ለመጮኽ ነው " ማለቱም ይታወሳል።

አስቀድሞ የደረሰውንና፣ አሁንም እየደረሰ ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ሁሉም ምዕመን  ከጸሎትና ምኅላው ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም ቤተክርስቲያን ማዘዟ አይዘነጋም።

Photo Credit - የኢኦተቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት / መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም

@tikvahethiopia
#ሙስና📈

" ዛሬ እኮ አገልግሎት ተፈልጎ ክፍለ ከተማ ቢኬድ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ፣ ተደብቆ ነው ሲሰጥ የነበረው "

በኢትዮጵያ ውስጥ #ሙስና ከመቀነስ ይልቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ፣ የሚፈፀምበትም መንገድ እየተራቀቀ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ የትራንስፖርት ፣ የመሬት፣ የካርታ፣ የግንባታ ፍቃድ ፣ የመታወቂያ ... ሌሎችም አገልግሎት ለማግኘት ሲኬድ ከእጅ መንሻ ጋር እንደሆነ መረዳቱን ገልጿል።

✦ የተቋሙ ዋና እምባ ጠባቂ ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ምን አሉ ?

- በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሙስና እንደሚፈፀም ተገልጋዮች ተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርባሉ።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት የሚጠየቁት ጉቦ በድብቅ ሳይሆን በግልፅ ነው።

- ለሙስና ተጋላጭ ናቸው የተባሉ ተቋማት ተለይተዋል እየተባለ ቁጥጥሩ ለምን እንደላላ ግራ የሚያጋባ ነው።

- " ዛሬ አገልግሎት ፈልገህ ክፍለ ከተማ ብትሄድ እኮ በግልፅ የሚጠየቅበት (ጉቦ) ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ከዚህ በፊት እንደውም በካኪ ታሽጎ ምናምን ነው ሲሰጥ የነበረው፤ ዛሬ በካኪ ታሽጎ የሚሰጠውን ገንዘብ እዛው ፊትለፊት ላይ የሚቀዱ የመንግሥት ሰራተኞች ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው ፤ ምንም እንኳን የየስራ ባህሪያቸው ቢለይም። "

- የስርዓት ለውጥ ነው የሚያስፈልገው፤ ሙስናን መሸከም የማይችል፣ ሙስናን ማስተናገድ የማይችል ስርዓት ፣የህግና የተቋም ስርዓት ነው መዘርጋት ያለበት።

- የስነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሰጠው ኃላፊነት ሙስናን ለመከላከል በቂ አይደለም። ይህ ኮሚሽን ተጠሪነቱ ለአስፈፃሚው አካል ነው፤ ነፃና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚያስችለው አይደለም። የተቋሙ ኃላፊዎች የሚሾሙት በአስፈፃሚው አካል ነው፤ ተጠሪናታቸውም ለዛ አካል ነው እንጂ ለምክር ቤት አይደለም። ሌላው እየሰራ ያለው መከላከል ላይ ነው፤ የህግ ማስከበሩን ለፍትህ ሚኒስቴር ነው የተሰጠው አሁን ካለው ከፍተኛ የሙስና ችግር አንፃር የህግ ማስከበሩንም የመከላከሉንም ስራ መስራት የሚችል ጠንካራ ኮሚሽን ማቋቋም ያስፈልጋል።

- ጠንካራ ኮሚሽን ባልተቋቋመበት ሁኔታ ኮሚቴ እያቋቋሙ ሙስናን የመከላከል የሚቻልበት ሁኔታ የለም።

◾️የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ምን ይላሉ ?

- ሙሰኞች ላይ የሚወሰድ እርምጃ ጠንካራ ስላልሆነ ሙስና ከመቀነስ ይልቅ እንዲጨምር ሆኗል።

- የፖለቲካ መዋቅሩ በራሱ አጥፊዎች እንዳይጠየቁ እድል የሚሰጥ ነው። ብሄርና ትውውቅን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በአጥፊውና በጠያቂው መካከል ልዩነት እንዳይኖር ሆኗል።

- " ሰዎች ሙስና ሰርተው ሲያጠፉ በግልፅ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጥፋተኛ መሆን ሲገባቸው እንደውም ከለላና ሽፋን ሲያገኙ ፣ ከበላበት ቦታ ወደሌላ ቦታ ዘወር ሲል ፣ ሃብትና ንብረት እንዲያገኙ ሲመቻችላቸው ይታያል። ይሄ ሁሉ የፖለቲካ ስሪቱ ነው። የፖለቲካ ስሪቱ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑነው። ይሄ ብሄርን መሰረት ያደረገ አደረጃጀት የሰላ ትግል እንዳይደረግና ተጠያቂነት እንዳይመጣ ያደርጋል። "

- የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን መክሰስም ሆነ የመመርመር ስልጣን ቢሰጠው አሁን ካለው ስራ የተሻለ ማድረግ አይችልም። ለ16 ዓመታት ይሄ ኃላፊነት ተሰጥቶት የሰራው ስራ ታይቷል።

- አሁን የሚበጀው አጥፊዎች የሚጠየቁበትን ህግ ማጠናከር ነው።

- " ሰው በዚህ ሰመን በካልኩሌሽን መታሰር ጀምሯል። ለምሳሌ አንድ የሙስና ወንጀል የፈፀመ ሰው 10 ሚሊዮን ብር ቢያገኝ በቀላሉ 10 ዓመት ቢታሰር / ቢወሰንበት ምን ብሎ ያስባል ' ይሄን 10 ሚሊዮን ብር በ10 ዓመት ላፈራው አልችልም ደግሞ ማንኛውም ታራሚ አመክሮ ስላለው በ7 ዓመት / በ6 ዓመት ብወጣ ይሄን 10 ሚሊዮን ብር መብላቱ / መመዝበሩ የተሻለ ነው ፤ ምክንያቱም በ6/7 ዓመት ውስጥ ላፈራው አልችም ' ብሎ ሰው በካልኩሌሽን መታሰር የጀመረበትና የደረሰበት ዘመንና ሁኔታ ላይ ደርሰናል "

- መፍትሄው ሙስና የሚፈፅሙ አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ህጉን ጠንካራ ማድረግ ብቻ ነው።

🔹በስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን የጥቅም ግጭት መከላከል መሪ ስራ አስፈፃሚ መስፍን በላይነህ ምን ይላሉ ?

- የሙስና ጉዳይ በጣም እየጎላ መጥቷል።

- ሁሉም ዘርፍ ከሙስና ተግባር የፀዳ አይደለም ፤ ግን ደረጃው ይለያያል።

- የእኛ ኮሚሽን ሙስናን መከላከል እንጂ ከተፈፀመ በኃላ የመመርመር፣ የመክሰስና የማገድ ኃላፊነት አልተሰጠውም። ዋናው ተልዕኮ የስነምግባር ትምህርትን ማስተማር ነው።

- በአብዛኛው ዓለም ላይ ሶስቱንም ማለትም፦
• የማስተማር፣
• የመመርመር ፣
• የመክሰስ አውድ ይዞ ነው የሚኬደው ፤ እኛ ሀገርም ተሞክሯል ከ1993 - 2008 ተሞክሯል። ከ2008 በኃላ የሙስና ወንጀል ምርመራ ብሎም ክሱ ወደሌላ አካል ተለልፋል። ቅንጅት ከተፈጠረ ይህ መሆኑ ችግር የለውም። ፖሊስ ይመረምራል፣ አቃቤ ህግ ይከሳል፣ ፍርድ ቤት ፍርድ ይሰጣል። ህብረት ያስፈልጋል። ቅንጅቱ ግን ጠንካራ አይደለም።

- ብዙ ሀገራት ላይ ይህን ዘርፍ በአንድ ተቋም ነው የሚመሩት ፤ እኛ ሀገር በተለያየ ተቋም ነው የሚሰራው ይህንን የሚመሩ አካላት እንደ አንድ ተቋም ሊሰሩ ይገባል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ / ጋዜጠኛ ያሬድ እንዳሻው ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM