TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም አሰላ ከተማ ዙሪያ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

-  ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብን የመጠየቅ ተግባር ህብረተሰቡን አማሯል።

- ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ገጠራማ ቀበሌያት፤ በተለይም ሄጦሳ ወረዳ፤ #ቂሊሳ በሚባል አከባቢ በሌሊት ሰዎችን በማገት ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ሆኗል። ይህ ቦታ ቁሉምሳ ከሚባለው የአሰላ ከተማ መግቢያ አከባቢ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

- በዶዶታም ተመሳሳይ የእገታ ተግባር በሌሊት ይፈፅማል።

- ከከተማ ውጪ ያለው የትኛውም አከባቢ መሰል ስጋት አለ፡፡

-  ሰዎች ሲታገቱ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በአጋቾቻው ይወሰንባቸዋል።

- የታገቱት ሰዎች የተጠየቁትን ተደራድረው ከፍለው ከመውጣት ውጪ ህይወታቸውን የማቆያ ሌላ ስልት የለም።

- አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ አይታወቅም እሱ ነው ትልቁ ችግር።

- ከፍተኛ የአርሶ አደር የኢኮኖሚ አቅም የሚስተዋልበት አከባቢ ነው በቀጣይም ለመሰል ዘረፋ ተጋላጭ እንዳኆን ስጋት አለን።

- ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች አከባቢውን ለቀው ወደ ከተማ በመሸሽ ላይ ሲሆኑ አቅም የሌለው ግን አከባቢው ላይ ተቀምጦ የሰቀቀን ህይወት ይመራል።

ፖሊስ ምን ይላል ?

የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ ከድር ፦

▸ ችግሩ ጎልቶ የሚስተዋለው ከከተማ ራቅ ባሉ ደናማ አከባቢዎች ነው፡፡ እንደሚባለው ሳይሆንም አልፎ አልፎ በአንዳንድ አከባቢዎች በደን በተሸፈኑ ገጠራማ አከባቢዎች በተለይ ወደ አኖሌ ባሉ ደናማ የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ አዋሳኝ ነው።

▸ በተለያዩ ጊዜያት ተግባሩን ለማስቆም የሚወሰዱ ኦፕሬሽኖች በመኖራቸው እንዲህ ጎልቶ በከተማ ዙሪያ የሚፈጸም ነገር የለም፡፡

▸ በተለይ በአሰላ ከተማ ዙሪያም ሆነ በአስፓልት መንገዶች ላይ እንዲህ ያለ ነገር የለም፡፡ ወንጀሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው በዶዶታ እና ሁሩታ ወረዳዎች ዳገታማ አከባቢዎች እና ከምስራቅ ሸዋ ዝዋይ ዱግዳ ጋር ከሚያዋስኑን አከባቢ ነው፡፡

▸ መሰል ተግባርን የሚፈጽሙ በውንብድና ስራ የተሰማሩ አሉ፡፡ አንዳዴ ኦነግ ሸኔ በሚል ትጥቅ አንግቦ በጫካ የሚንቀሳቀሰውን ሃይል እንደ ሽፋን በመጠቀም በዝርፊያው የተሰማሩ መኖራቸውን አረጋግጠናል፤ በዝርፊያ ላይ እያሉም ጭምር ተቆጣጥረን ለህግ ያቀረብናቸው አሉ።

• ምን ያህል ሰዎች ተያዙ ? የሚለውም ጥያቄ ላይ ዝርዝር ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል።

▸ በተለያየ ጊዜ ኦፕሬሽኖችን እያካሄድን ነው ፤ ከታጣቂዎች በተጨማሪ በታጣቂዎች ስም የተደራጁ መኖራቸውን ህዝቡን እናስገነዝባለን፡፡ እነዚህ ማህበረሰቡን በስልክ ጭምር እየደወሉ የሚያስፈራሩትን ተከታትለን እየያዝን ነው፡፡

(ከዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃለምልልስ የተወሰደ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ዛሬ ህዳር 3/2016 ዓ.ም በመቐለ የተካሄደው የታክሲ አገልግሎት የማቆም አድማ ከማህበራቱ እውቅና ውጪ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ሶስት የታክሲ ማህበራት ባወጡት መግለጫ አሳወቁ። ማህበራቱ ከሰዓት በኃላ ባሰራጩት ይፋዊ መግለጫ ፤ " ለመንግስት ያቀረብነው ጥያቄ በህጋዊ መንገድ እንዲመለስ ጥረት እያካሄድን ባለንበት ጊዜ አገልግሎት ማቋረጥ አግባብ አይደለም " ብለዋል። አድማ…
#Update

" የምንሰጠውን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማው የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ላይ #ጥብቅ_እርምጃ ይወሰዳል " - ወ/ሪት ራሄል ሃይለ

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በመቐለ የተደረገው የታክሲ አገልግሎት ማቋረጥና አድማ " ህጋዊ አይደለም " ብሏል።

ቢሮው ከመቐለ የትራንስፓርት ፅህፈት ቤትና ፓሊስ በጋራ ' አካሄድኩት ' ባለው ግምገማ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀድም ሲል አገልግሎት ለማቋረጥና አድማ ለመምታት የሚያበቃ ቅሬታና ጥያቄ አላቀረቡም ሲል ገልጿል።

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ራሄል ሃይለ ህዳር 3/2016 ዓ.ም አመሻሽ ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል በመሆኑ በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መክረዋል።

የመንግስት ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ለምለም ኪሓ ፣ ህዳሴና ሓወልቲ የተባሉ የመቐለ የታክሲ ማህበራት አመራሮች በማህተም አስደግፈው ህዳር 3/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ለሚድያዎች በላኩት መግለጫ ፤ አግልግሎት ማቋረጡና አድማው ከእውቅናቸው ወጪ የተደረገ ኢ-ህጋዊ ነው ማለታቸው መዘገባችን ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

በመቐለ ከተማ የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ባደረጉት አድማ ነዋሪዎች ለእንግልት እና አላግባብ ለሆነ ወጭ ተዳርገዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ ያነጋገራቸው የታክሲ ባለንብረቶች እና አሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ በመሄድ ላይ የሚገኘው የኑሮ ሁኔታ ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ መወደድ የሹፌርና የረዳት ክፍያ ገበያ ላይ ባለው ታሪፍ መሸፈን እጅግ እንደከበዳቸው ፤ ያለው ታሪፍ እንዲስተካከል ከአንድ ወር በፊት መንግሥትን በማህበራቸው በኩል ቢጠይቁም ምላሽ ስላላገኙ ወደ አድማ እንደገቡ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" . . . ፌክ ዶክሜንት አሰርተው እነርሱ አይደለም ለማስተማር ለመማር ያልቻሉ ሰዎች ገብተው ትውልዱን ሲያበላሹ እያየን ነው " - አንጋፍ እሸቱ

የአዲስ አበባ ሴቶች ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2015 ዓ.ም ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ለተመረቁ ፣ 12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴቶች ተማሪዎች ሽልማትና የምስክር ወረቀት፣ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ውጤታማ የሆኑ ሴቶች ተሞክሯቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር።

በዚህም መድረክ ላይ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሴት ተማሪዎች የ10 ሺሕ ብር ሽልማትና የምስክር ወረቀት ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ከኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂና ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ለተመረቁ ሴት ተመራቂዎች የ15 ሺሕ ብር ሽልማትና የምስክር ወረቀትና አበርክቷል።

ከተሸላሚዎች መካከል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አካውንቲንግ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ውጤት (3.92) ያመጣችው ተማሪ አንጋፍ እሸቱ አንዷ ናት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪ አንጋፍ እሸቱን አነጋግሯል።

አንጋፍ እሸቱ ምን አለች ?

(ስለ ትምህርት ፖሊሲው)

" አሁን ላይ የትምህርት ፖሊሲው መቀየር አለበት ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አሁን ባለው የትምህርት ፓሊሲ ላይ ያለውን ተማሪ እያየነው ነው።

ይሄ ሁሉ ተማሪ የወደቀው አሁን ባለው አሰራር ነው። ችግሩ ሁሉም ላይ ነው ተማሪ ላይ ብቻ አይደለም። ከመምህራኑም፣ ከአመራሩም፣ ከፓሊሲውም ነው ብዬ አምናለሁ።

ስለዚህ በመጀመሪያ ከሥር መሠረቱ ፖሊሲውን ማስተካከል፣ ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት ማስተካከል ያስፈልጋል።

መምህራን እውነት ብቁ ናቸው ወይ ለሚያስተምሩት ትምህርት የሚለውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። ምክንያቱም በጣም ብዙ ነገሮችን እንሰማለን ፌክ ዶክሜንት አሰርተው እነርሱ አይደለም ለማስተማር ለመማር ያልቻሉ ሰዎች ገብተው ትውልዱን ሲያበላሹ እያየን ነው። 

ስለዚህ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች የሚያገኙት ትምህርት የተሻለ ነው? ወይ ብሎ ትኩረት ማድረግ አለበት። ' ጋርቤጅ ኢን ጋርቤጅ አውት ' የሚባል ኮንሰፕት አለ። ተማሪዎች ከጥናት በተጨማሪ ተምረው ባስገቡት ልክ ነው ፈተናቸውን የሚሰሩት።

ስለዚህ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች ፈተና ስላላለፉ ብቻ ችግሩ ተማሪዎቹ ላይ ብቻ ነው ብዬ አላስብም። "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-14
TIKVAH-ETHIOPIA
#HoP ነገ ማክሰኞ ጥዋት ከ2:00 ሰዓት ጀምሮ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል። ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሏል። @tikvahethiopia
#Update #አሁን

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡

ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው ከተወካዮች ም/ ቤት አባላት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ?

- የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ፣

- የሀገራዊ ትርክት ጉዳይ ፣

- የዜጎች ደህንነት ጉዳይ፣

- በየቦታው ያሉና ህዝቡን ሰላም እየነሱ ያሉ ታጣቂዎችን በተመለከተ ምን እየተሰራ እንዳለ፤

- የትምህርት ጥራት አፈፃፀም፣ የመፅሀፍት እና የቁሳቁስ እጥረት ጉዳይ፣ በተጨማሪ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች እጣፈንታ ምንድነው ?

- ከባህር በር ጉዳይ ጋር ተያይዞ እንዲሁም በአጠቃላይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስላለው የዲፕሎማሲ ሁኔታ፤

- ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት የሚታይባቸው እንደ መሬት አስተዳደር፣ ገቢዎች  ፣ የጉምሩክ አገልግሎት ፣ ትላልቅ ግዢዎችና ትላልቅ የኮንስትራክሽን ስራዎች ከሌብነት እና ብክነት ለማፅዳት መንግስት ስለያዘው አቋም ፤

የሚመለከቱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ተነስተዋል።

የሚሰጡት ምላሾችን እና ሌሎች ሀሳቦችን ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው፡፡ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትም ጥያቄዎችና አስተያየቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ። እስካሁን ባለው ከተወካዮች ም/ ቤት አባላት ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ ? - የኦሮሚያ እና አማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ፣ …
#ጥያቄ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ከድጃ ያሲን ፦

" ... የብልሹ አሰራር ከማስወገድና የፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር አንፃር መንግሥት በየደረጃው ተጠያቂነትን ለማስፈን ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? በፀረ-ሌብነት ትግሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ይጠበቃል ?

ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት በሚታይባቸው ለምሳሌ እንደ #መሬት_አስተዳደር#ገቢዎች#የጉምሩክ_አገልግሎት ፣ ትላልቅ ግዢዎች እና የኮንስትራክሽን ዘርፍን ከሌብነት እና ከብክነት የፀዳ እንዲሆን እንደ መንግስት የተያዘው አቋም ላይ ማብራሪያ ይሰጥ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥያቄ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ከድጃ ያሲን ፦ " ... የብልሹ አሰራር ከማስወገድና የፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር አንፃር መንግሥት በየደረጃው ተጠያቂነትን ለማስፈን ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? በፀረ-ሌብነት ትግሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ይጠበቃል ? ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት በሚታይባቸው ለምሳሌ እንደ #መሬት_አስተዳደር፣ #ገቢዎች፣ #የጉምሩክ_አገልግሎት ፣ ትላልቅ…
#ጥያቄ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ፦

" የሀገራችን የኢትዮጵያ ህዝብ የባለፈው ምርጫ አካሄድ ምንም ይሁን ምን እርሶንና ፓርቲዎን መርጦ መንግሥት ከመሰረተ ሁለት አመት አገባደን ሶስተኛ አመት ይዘናል።

በዚህ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በአግባቡ በተወዳደሩበት ቦታ በአብዛኛው ህዝቡ ፓርቲዎን አምኖ ሳይሆን ለእርሶ በነበረው እምነትና ፍቅር የመጡበትም ጊዜ ውስብስብ እና ያደረና የገነነ የብሄርተኝነት ችግር እግር ተወርች ጠንፎ ይዟቸዋል ፦
- እድል እንስጣቸው ፣
- እሳቸው ጊዜ ሲያገኙ ቃል የገቡልንን ሁሉ ይፈፅሙልና ፓርቲያቸውንም ያጠሩታል ፣
- የዴሞክራሲ ተቋማት ጠንካራ ሆነው እንዲወጡ ያደርጋሉ ፣
- ፍትህ ያሰፍናሉ፣
- መፈናቀል፣ ስደት ፣ውርደት ያስቀሩልናል
- የስራ አጥ ቁጥር ይቀንሳሉ ፣
- የዜጎችን ደህንነት ያስጠብቃሉ፣
- የኑሮ ውድነትም ይቀንሱልናል በጥቅሉ ከንግግራቸውና አንዳንድ ከወሰዷቸው እርምጃዎች አንፃር የተሻለ ሊለውጡ ሀገራችንን የሚያሻግሩት እሳቸው ናቸው በሚል ነበር።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በእውነት እኔም በግሌ እምነት ነበረኝ። ብዙ ለውጥና ውጤቶችን አይቻለሁ። የህዳሴው ግድብ እውን ሆኖ ማየት፣ በሀገር ገበታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ያሉ አፈፃፀሞች፣ ሰፋፊ የግብርና ስራዎች ጅማሮዎች ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ከምንም በላይ ግን ፦

∘ ዜጎች እየሞቱ ነው፤ እየተፈናቀሉ ፣ እየተሰደዱ ነው።

∘ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቄዬ በላይ ላያቸው ቤት ይፈርስባቸዋል፤ ተሰደዋል።

∘ ብዙ ዜጎች እስር ላይ ይገኛሉ የፍርድ ሂደቱም የተዛባ፣ የተንዛዛና የተጓተተ ነው።

∘ ሀገራችን ከጦርነት ልትላቀቅ አልቻለችም ፣የትግራይ ጦርነት በሰላም ቢቋጭም በሌላ በኩል በሌሎች አካባቢዎች ጦርነት ተፋፍሟል፣ በሰላም ለመፍታት የተኬደበት ርቀት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፤ እልህ መጋባትም ይታይበታል።

∘ እውነተኛው እና ጤነኛው የንግዱ ማህበረሰብ ከንግዱ እየወጣ ነው። ህገወጡ እያበበ፣ ሀገሪቱ ጥቂት ህገወጥ ከበርቴዎች እንዳሻቸው የሚሆኑባት እየሆነች ነው።

∘ የፋይናንስ ተቋማት እየከሰሙ ያሉበት፤

∘ የባንክ ማናጀሮች ከበላይ ተቋሞቻቸው በጥቅም ትስስር ምክንያት በአቅም ማነስ እና በሙስና መቆጣጠር ያለበት ተቋም በቸልታ የሚያይበት 10 ሺህ ብር እንኳን ለማግኘት ችግር የሆነበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። እርምጃ ሲወሰድ አይታይም።

∘ የኑሮ ውንድነቱ ዜጎች ሳይወዱ በግድ ጎዳና እያስወጣ ነው።

∘ የኢትዮጵያውያን የአኗኗር ሁኔታ እጅግ ተለያይቷል። መንግስት እና ህዝብ ጀርባ ለጀርባ እየሆነ መጥቷል።

∘ የዜጎችን እንቅስቃሴ የሚገድብ አስጊ ሁኔታ ላይ እንገኛለን።

ክቡር ፕሬዚዳንት በንግግራቸው አማላይ የሆኑ የ3 ዓመት የኢኮኖሚ እቅድ አቅርበዋል። ነገር ግን የኢኮኖሚ እድገት ከላይ ተዘረዘሩ ችግሮች ባሉበት ሁኔታና ሌላው ቀርቶ የፓርቲዎ አባላት እርስ በእርሳቸው በማይተማመኑበት ሁኔታ እንዴት ሊሳካ ይችላል ?

እነዚህን ለማረም ምን አይነት የመፍትሄ ሀሳብ ይዘው ቀርበዋል ?

ሀገር እና መንግሥትዎን እንዴት ሊታደጉ አስበዋል ? "

@tikvahethiopia
" አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መንግሥትን በክላሽ ፈፅሞ መጣል አይቻልም " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትስር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክላሽ መንግስትን መጣል ፈጽሞ አይቻልም " አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

አሁን ባለው ሁኔታ መንግስትን ፈፅሞ በክላሽ መጣል አይቻልም ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " ከክላሽ ይልቅ ብእርና ሃሳብ ይዘን ለመወያየት ቅድሚያ መስጠት ይገባል፡፡ " ብለዋል።

" በመገዳደል ልናሳካው የምንችለው ዓላማም ሆነ የሚገኝ ትርፍ የለም፡፡ ለኢትዮጵያ የሚበጀውም በውይይት የበለጸገች አገር መገንባት ነው " ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይዞት የመጣውን ዕድል እንዳያመልጠን " እለምናለሁ እመክራለሁም " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

" ይሄ National Dialogue እድል ለኢትዮጵያ መባከን የሌለበት ፤ ካባከነው ሌላ ረጅም ጊዜ የሚጠይቀን ጉዳይ ስለሆነ የምንቃወምም ፣ የምንቃረንም የምንፎካከርም ፣ የምንታገልም ሁላችንም በሰከነ አእምሮ ይሄንን እድል ለመጠቀም መሞከር ይኖርብናል። " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#ሪፈረንደም

" ህዝብ የሚያቀራርብ ሌላ መፍትሄ ካለ መጠቆምና መነጋገር ይቻላል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ጥያቄ በሚነሳባቸው የአማራ እና ትግራይ አካባቢዎች ጉዳይ መንግሥት ይዞት ከመጣው መፍትሄ የተሻለና የተለየ መፍትሄ ያለው ማቅረብ ይችላል አሉ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ የፌደራል መንግስት በትግራይና አማራ ክልሎች አወዛጋቢ የሆኑ የወሰን ጉዳዮች #በህዘበ_ውሳኔ እንዲፈታ እንደሚፈልግ አሳውቀዋል።

ይህ የመፍትሄ ሀሳብ በክልሎቹ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም አንዱ ተደስቶ ሌላው እንዳያኮርፍ የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ለዚህም ፌዴራል መንግሥት ከሁለቱም ክልሎች አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉንና አቅጣጫ አስቀምጦ እየሰራበት እንደሆነ ተናግረዋል።

" የህዝበ ውሳኔው / ሪፈረንደም ብቸኛ አማራጭ አይደለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የሁለቱንም ክልሎች ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ፤ ህዝብ የሚያቀራርብ ሌላ መፍትሄ ካለ መጠቆምና መነጋገር ይቻላል " ብለዋል።

" የአማራ እና ትግራይ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ተወያይተው ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ መፍትሄ አለን ካሉ በደስታ እንቀበላልን " ሲሉ ገልጸዋል።

" መንግሥት ሪፈረንደም ይደረግና በህግ መሰረት በአካባቢዎቹ ዘላቂ ሰላም ይስፈን ብሎ እየሰራ ነው ፤ ከዚህ ውጭ አማራጭ ያለው ያቅርብ " ብለዋል።

መፍትሄ መጠቆም ሳይቻል ግን በመንግስት የቀረበውን የመፍትሄ ሃሳብ አለመቀበል ግን ተገቢ አይደለም፤ ወደ ሰላም አይወስድም ፤ ለአንዱ ቢመለስም ለሌላው ጥያቄ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#StockMarket

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የ ' ስቶክ ማርኬት ' ስራ እንደሚጀመር ተገለፀ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚጀምረውን የ ' ስቶክ ማርኬት ' ለመደገፍ ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።

ስቶክ ማርኬት በከፍተኛ ደረጃ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይደግፋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " በጣም ብዙ ሰው ሃሳብ አለው ገንዘብ የለውም፤ ጥቂት ሰዎች ደግሞ ገንዘብ አላቸው ሃሳብ የላቸውም ፤ ጥቂቶች ደግሞ ገንዘብ አላቸው ሃሳብም ገብቷቸዋል ተቋም የላቸውም ፤ ስቶክ ማርኬት ማለት ገንዘብ ያለውን ሃሳብ ያለውንና ተቋምን የሚያገናኝ ምርጥ ሀሳብ ማለት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ለአብነት ፦
- በአረብ ሀገራት ያሉ እህቶች ' ስቶክ ማርኬት ' ውስጥ ሼር ገዝተው እዛ እየሰሩ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚችሉ ፤

- አርሶ አደሮችም ከስቶክ ማርኬት ሼር ገዝተው እያረሱ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ ፤

- ዲያስፖራዎችም ወደ ሀገር ሲመለሱ ምንም የሌላቸው እንዳይሆኑ ከወዲሁ ዋና ዋና ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ ቴሌኮሚኒኬሽን በቅርቡ የተወሰነ ፐርሰንት ለህዝቡ እንደሚሸጥ አሳውቀዋል።

በሂደት ቴሌን፣ አየር መንገድን የህዝብ ተቋማት የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

" እኛ ሂልተንንም፣ ጊዮንንም፣ አየር መንገድንም፣ ቴሌኮምን ይዘን አንዘልቀውም " ያሉ ሲሆን እነዚህ ኩባንያዎች ላይ ብዙዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉበት ካደረግን የተሻለ እድገት ሊያመጡ ይችላሉ፤ ለኢትዮጵያ እድገትም እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ምክር ቤቱ ከወዲሁ ድጋፍ ለማድረግ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ጥሪ_ማሳመሪያ ጥሪት ያተርፋል!

የመኪና፣ ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች፣ ስማርት ቴሌቪዥኖች፣ የ5ጂ ስማርት ስልኮች፣ በርካታ የ5ሺህ ብር እና የሞባይል ጥቅል ሽልማቶች አሸናፊ ለመሆን:

ወደ 822 ወይም *822# ይደውሉ አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ከ 645 ለሚደርስዎት ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ።

መልካም ዕድል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
ተወዳጁ Canal+  በመላው ኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች የጎዳና ላይ የዲኮደር ሽያጭ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ጉዞውን አዲስ አበባ ላይ መነሻ በማድረግ እስካሁን በቢሾፍቱ ፣ አዳማ ፣ ሻሸመኔ ፣ ሃዋሳ ፣ አርባምንጭን ያዳረሰ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ በጅማ ፣  መቀሌ ፣ ሐረር ፣ ድሬዳዋ እና ጋምቤላ ሽያጩን የሚቀጥል ይሆናል። 

ከዲኮደር ሽያጮቹ ባለፈ ይህ ጉዞ የጉዳና ላይ ስፖርቶች፣ኮንሰርቶች እንዲሁም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያካተተ ነው። በእነዚህ ቀናቶች ላይ ልዩ ልዩ የCanal+ ዲኮደሮችን በመግዛት ነጻ የሁለት ወር የፌሽታ ጥቅሎችን ያግኙ! ከዚህ በተጨማሪ ነባር ደንበኞች የ250 ብር ጥቅላችሁን በማሳደስ ብቻ የ500 ብር ፌሽታ ጥቅል ይሸለሙ።

CANAL+ን ከታች ባሉት የማህበራዊ ትስስር ገፃቻችን ሊንኮችን በመጫን ይከታተሉን!
Click on the below links to Follow CANAL+ on all our social media pages!

Telegram  @canalplusbusiness

#CANALPLUSEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የምንሰጠውን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማው የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ላይ #ጥብቅ_እርምጃ ይወሰዳል " - ወ/ሪት ራሄል ሃይለ የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በመቐለ የተደረገው የታክሲ አገልግሎት ማቋረጥና አድማ " ህጋዊ አይደለም " ብሏል። ቢሮው ከመቐለ የትራንስፓርት ፅህፈት ቤትና ፓሊስ በጋራ ' አካሄድኩት ' ባለው ግምገማ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች ቀድም…
#Update

በመቐለ ከተማ በአድማ ምክንያት ለአንድ ቀን ተቋርጦ የነበረው የታክሲ አገልግሎት ዛሬ በከፊል ሲሰጥ ውሏል።

የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ለአንድ ቀን የጠሩት ስራ የማቆም አድማ " ሰርአት አልበኝነት ነው " ያሉት ተጠቃሚዎች ፤ " መንግስት አፋጣኝና ወቅቱ የሚዋጅ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል " ብለው ነበር። 

ለምለም ኪሓ ፣ ሓወልትና ህዳሴ የተባሉ ሦስት የታክሲ ማህበራት ህዳር 3/2016 ዓ.ም በማህተም አስደግፈው ባወጡት የጋራ መግለጫ የተፈፀመው ስራ የማቆም አድማ " ከእውቅናችን ውጭ የተፈፀመና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው " በማለት ውድቅ አድርገውታል።  

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወ/ሪት ራሄል ሃይለ ህዳር 3/2016 ዓ.ም ለሚድያ በሰጡት መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መክረው ነበር።

የመንግስትን ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲሉም ምክትል ኃላፊዋ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

በዚሁ መሰረት የመቐለ ታክሲዎች ህዳር 4/2016 ዓ.ም ከሰአት በኃላ በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                      
@tikvahethiopia