TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia 🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች 🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ…
" በመርሕ ደረጃ መጥፎ ሰላም ጥሩ ጦርነት ባይኖርም የስምምነቶች ግልጽነት ማጣት ውጤቱን የተገላቢጦሽ ሊያደርገው ይችላል ! " - የትብብሩ ፓርቲዎች

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አገራችን በሰላም እጦት፣ ሕዝባችን ለዓመታት በዘለቀ ጦርነት ቁምስቅሉን እያየ እንዳለ ምሥክር መቁጠር አይሻም። " ብለዋል።

" በተለይ በብዙ ተስፋና ጉጉት ተጠብቆ የነበረው ' ለውጥ ' የኋልዮሽ መሄድ ከጀመረ ወዲህ ሰላም ማደር ብርቅ፣ ፍጅትና ትርምስ ጌጣችን ከኾነ ሰነበተ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዚህ ቀደም ኤርትራ በረሃ ከኦነግ ጋር በክልል አመራሮች ደረጃ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ከተደረገ በኋላ ሕዝብ ደስታውን ሳያጣጥም የሰላም ተፈራራሚው ኃይል " ቃል የተገባልኝ አልተፈጸመም " በሚል ሰበብ ተመልሶ ጫካ ከገባ ወዲኽ እንደ አገር ባጠቃላይ በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ያየው ቁምስቅል ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑ መንግሥት ' ኦነግ ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተወሰነ ቡድን ሰላም መፈረሙ በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡን የገለጹት ፓርቲዎቹ " መጥፎ ሰላም የለም በሚል ጥቂቶች እንኳን የሰላም አካል መኾናቸውን በበጎ የምንመለከተው ነው " ብለውታል።

ከዚኹ ጋር ተያይዞ " የታጣቂ ቡድኑ መሪ ናቸው የተባሉ ግለሰብና የተወሰኑ ወጣቶች ከክልል አመራሮች ጋር ስምምነት ሲፈራረሙ ታይተዋል " ብለዋል።

" ከስምምነቱ ማግስትም አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለሦስት ቀናት በዘለቀ ተኩስ ስትናጥ ከርማለች " ያሉት ፓርቲዎቹ " በተኩሱ እስከ አኹን አንዲት እናት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠናል " ብለዋል።

ይኸው ድርጊት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሂደቱ ጥርጣሬን እንዳጫረባቸው ጥርጣሬያቸው የሚነሳውም ከስምምነቱ ግልጸኝነት ማጣት ብቻ ሳይሆን ከእንዲህ ዓይነት ክስተቶች ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

" ስምምነቱ መሣሪያ ማውረድን አይጨምርም ወይ ? " ያሉት ፓርቲዎቹ " የከተማ አስተዳደሩ ርችት እንኳን እንዳይተኮስ ሲከለክል እንዳልከረመ እንዴት ሙሉ ትጥቅ ተይዞ መግባትንና ለቀናት ጭምር የድልነሺነት ብሥራት በሚመስያመስል መልኩ ተኩስን ሊፈቅድ ቻለ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፦

° ' ከተማ ውስጥ ኹከት ለመፍጠር የመጡ ' በሚል በመታወቂያ ማንነት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው የመጡ ነብሰ ጡሮችና አረጋውያን ጭምር ከአዲስ አበባ መግቢያ ክብረ ነክ በኾነ መንገድ ሲመልስ የነበረ ኃይል አኹን የት ሄዴ ?

° ከዚኹ መሐል ሲገድል ሲቀማ የነበረ በውል ተጣርቶ ተጠያቂነት አይኖርም ወይ ?

° መንግሥት የሰላም ስምምነት ፈጸመ ከተባለው ግለሰብና ቡድን ጋር ከዚኽ ቀደም የነበረው ግንኙነት ምን ነበር ?

° ታንዛኒያ ድረስ ኹለት ጊዜ አድካሚ ሙከራዎች ተደርገው ጫፍ እየደረሱ የተናፈቀው ሰላም ሲጨነግፍ በአቋራጭ አዲስ አበባ እውን የኾነበት ተዓምር ምን ቢኾን ነው ?

° የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ሥነልቡናዊ ጫና እንዲደርስበት ታስቦ ተሠርቷል ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ፓርቲዎቹ አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ የለአንድም ቀን እንኳን ሰላም መስፈን እጅጉን እንሻለን ብለዋል።

" የአንድም ሰው የሰላምን መንገድ መምረጥ ያስደስተናል " ሲሉ አክበላለዋል።

" በአንጻሩ ደግሞ በሂደቱ ዙሪያ የግልጽነት አለመኖርና የሰላሙ ዘላቂነት እጅግ ስለሚያሳስበን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲኖሩ ማንሳት በጎ ይመስለናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፦

➡️ የሰላም መጥፎ የለውምና የተደረሰውን ስምምነት ከነገዘፉ ችግሮቹ በበጎ እናየዋለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት የስምምነቱን ሂደትና ዝርዝር ነጥቦች የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በአጽንኦት አሳስበዋል።

➡️ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለቀናት የዘለቀው ተኩስ፣ በሰላም ስምምነት የመጣ ሳይኾን ኾን ተብሎ የሕዝብን ሥነ ልቡና ለመስለብና ለማስፈራራት የተደረገ መኾኑን ሕዝባችን እንዲያውቀው እንሻለን ብለዋል።

➡️ በዚኹ የተኩስ እሩምታ ሰበብ መገናኛ አካባቢ ለተገደሉት እናት መንግሥት ሓላፊነት የሚወስድ ኾኖ ቢያንስ ቤተሰባቸውን ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት ከሽርፍራፊ ደስታና ማስመሰል ወጥቶ ዘላቂ ሰላምን በሰጥቶ መቀበል መርኅ በገለልተኛ ታዛቢዎች አማካይነት ድርድር ለማድረግ ፈቃደኝነቱን በመግለጽና ለዚህም ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኙ፣ በአፋጣኝም ተኩስ አቁም እንዲታወጅ በአጽንዖት አሳስበዋል።

#እናትፓርቲ
#መኢአድ
#ኢሕአፓ
#ዐማራግዮናዊንቅናቄ

@tikvahethiopia