TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የውሃ_ዋጋ 📈

🔹" በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም " - ውሃ አምራች ኩባንያዎች

🔹" ከአከፋፋዮች የሚሸጥልን ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል " - ነጋዴዎች

🔹" የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲቀርብ ጭማሪ ተደርጓል " - አከፋፋዮች

▪️ የታሸገ ውሃ አከፋፋዮች ምን ያህል ዋጋ ነው የጨመራሁት ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ዋጋውን ከመናገር ተቆጥበዋል።

በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ከሰሞኑ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።

በታሸጉ የፕላስቲክ ጠርሙስ ዉሃ ምርቶች ላይ የተደረገዉ የዋጋ ጭማሪ ከጥሬ ዕቃ መወደድ ጋር የተያያዘ መሆኑ አምራቾች ሲገልፁ በአንድ በኩል ደግሞ ከአከፋፋዮች የምንረከበዉ ምርቶች ላይ ጭማሪ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ነጋዴዎች ተናግረዋል።

በተለይ ከሶስት ሳምንታት ወዲህ በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሲሸጡ ከነበረበት ዋጋ ላይ በእያንዳንዱ ምርት የ5 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ካፒታል ጋዜጣ አደረኩት ያለውን ቅኝት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

የዋጋዉን ጭማሪ አስመልክቶ ማን ምን አለ ?

#አምራች_ኩባንያዎች ፦ ጭማሪው ከጥሬ እቃ መወደድ እና በቅንጦት እቃዎች ላይ በሚጣለዉ ኤክሳይስ ታክስ ሳቢያ መሆኑን አንስተዋል። ቢሆንም ግን በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም ሲሉ አሳውቀዋል።

" በሁሉም ምርቶች ላይ ከአንድ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገበትም " የሚሉት የዉሃ አምራች ፋብሪካዎቹ ነገር ግን በገበያ ላይ የሚሸጥበት ዋጋዉ ከእነርሱ እዉቅና ዉጪ መሆኑን አስረድተዋል።

#ነጋዴዎች ፦ ከዚህ ቀደም ሲረከቡበት የነበረዉ የዋጋ ተመን ላይ ጭማሪ መደረጉን ገልፀዉ ከአከፋፋዮች የሚሸጥላቸዉ ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።

#አከፋፋዮች ፦ የዋጋዉ ጭማሪ ከፋብሪካዎቹ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲያቀርብ ጭማሪ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል። ምን ያህል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ የዉሃ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ፤ የዋጋዉ መጨመር መኖሩን አረጋግጠዋል።

ለዚህ በምክንያትነት ያነሱት " ፕላስቲክ ጠርሙሶቹ የሚሰሩት ከነዳጅ ተረፈ ምርት በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች በጦርነቱ ሳቢያ ሊጨምር በመቻሉ ፣ ኤክሳይስ ታክስ ከፍተኛ መሆን ፣ ለአምራቾቹ ለስራ ማስኬጃ የብድር እጥረት መኖር ዋነኛዎቹ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

በገበያ ላይ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበዉ ምላሻቸዉን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

Credit - #CAPITAL #ካፒታል_ጋዜጣ

@tikvahethiopia