#እንድታውቁት
ወባ (Malaria)
" በኢትዮጵያ ተከታታይ በሆኑ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እንዲሁም ሌሎች ወረርሽኞች ሳቢያ በባለፉት 2 ዓመታት ላይ ተመስርቶ በወጣ ሪፖርት የወባ በሽታ ቁጥር ከ150%-120% ጭማሪ አሳይቷል " - #WHO Ethiopia
ወባ ተላላፊ በሽታዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን የሚተላለፈውም Plasmodium በሚባል የፕሮተዞአ ዓይነት በሴቷ አኖፊለስ የወባ ትንኝ አማካኝነት ነው።
- የወባ ትንኝ ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታ ላይ በብዛት ትራባለች።
- የወባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ብዙ በመሆናቸው የሚያስከትሉት ችግር አንዱ ከአንዱ ይለያያል። ለሞት የሚዳርጉ አሉ፤ቀለል ያለ ህመም የሚያስከትሉም አሉ። በኛ ሀገር ሁለቱም ይገኛሉ። በዋናነት የከፋ ችግር የሚያስከትሉት P.falciparum እና p.vaivax ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
▫️P.falciparum የተባለው በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ላይ በስፋትም በገዳይነትም ብዙውን ድርሻ ይወስዳል፡፡
-ለወባ በሽታ ማንኛውም ሊጋለጥ ይችላል::የወባ በሽታ ከተላላፊ በሽታዎች በገዳይነቱ ወደር የሌለው ነው።በተለይ በህፃናት፣ ነብሰ ጡር እናቶችና አረጋዊያን ላይ ሲከሰት የገዳይነት ጉልበት ያገኛል።
ምልክቶቹ ፦
▪️ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ
▪️ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
▪️ሆድ ህመም፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ
▪️ራስ ምታት፣ሰውነትን ጥምቅ ሚያደርግ ላብ
- ወባ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል። የከፋ ከሚሆንባቸው አንዱ አንጎልን ሲያጠቃ ነው። በተለምዶ የጭንቅላት ወባ (Cerebral malaria) ተብሎ ይጠራል።
- ሌላው ወባ የኩላሊት መድከምን ሲያስከትል ነው። አንዳንዴ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ደረጃም ላይ ይደርሳል።
- የልብና የሳንብ ችግር በማስከተል ለሞት የመዳረግ አቅም አለው። በተጨማሪም የደም ማነስ ያስከትላል።
* መከላከያ መንገዶች
የወባ ትንኝ ንክሻን በመከላከል፤ የመራባት አቅሟን በማስቆም፣ ቅድመ መከላከል መድሐኒት በመውሰድ መከላከል ይቻላል።
- በወባ በሽታ በብዛት ተጠቂ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቤት ውስጥ ፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማድረግ እንዱሁም ደግሞ በፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበርን በአግባቡና በትክክል መጠቀም፤ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታን በማፋሰስ የወባ ትንኝ እንዳትራባ ማድረግ እና ወባ በብዛት ያለበት ቦታ ልንሄድ ከሆነ ሃኪም በማማከር ቀድመን ፀረ-ወባ መድሃኒት መውሰድ ናቸው፡፡
▪️ከላይ የተባሉትን ምልክቶች ብዙ ጊዜ በሽታውን በያዘችው ትንኝ ከተነከስን ከጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ልናይ እንችላለን፤አንዳንድ የወባ በሽታ አይነቶች ግን እስከ አመት ድረስ ምልክት ሳያሳዩ በሰዉነታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።
▫️ምልክቶቹን ካየን ግን በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።
#WHO, #EthioDemographyAndHealth
@tikvahethiopia

#የውሃ_ዋጋ 📈
🔹" በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም " - ውሃ አምራች ኩባንያዎች
🔹" ከአከፋፋዮች የሚሸጥልን ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል " - ነጋዴዎች
🔹" የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲቀርብ ጭማሪ ተደርጓል " - አከፋፋዮች
▪️ የታሸገ ውሃ አከፋፋዮች ምን ያህል ዋጋ ነው የጨመራሁት ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ዋጋውን ከመናገር ተቆጥበዋል።
በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ከሰሞኑ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መደረጉ ተነግሯል።
በታሸጉ የፕላስቲክ ጠርሙስ ዉሃ ምርቶች ላይ የተደረገዉ የዋጋ ጭማሪ ከጥሬ ዕቃ መወደድ ጋር የተያያዘ መሆኑ አምራቾች ሲገልፁ በአንድ በኩል ደግሞ ከአከፋፋዮች የምንረከበዉ ምርቶች ላይ ጭማሪ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ነጋዴዎች ተናግረዋል።
በተለይ ከሶስት ሳምንታት ወዲህ በታሸጉ የዉሃ ምርቶች ላይ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሲሸጡ ከነበረበት ዋጋ ላይ በእያንዳንዱ ምርት የ5 ብር ጭማሪ ማሳየቱን ካፒታል ጋዜጣ አደረኩት ያለውን ቅኝት ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
የዋጋዉን ጭማሪ አስመልክቶ ማን ምን አለ ?
#አምራች_ኩባንያዎች ፦ ጭማሪው ከጥሬ እቃ መወደድ እና በቅንጦት እቃዎች ላይ በሚጣለዉ ኤክሳይስ ታክስ ሳቢያ መሆኑን አንስተዋል። ቢሆንም ግን በዚህ ልክ የተጋነነ ጭማሪ አልተደረገበትም ሲሉ አሳውቀዋል።
" በሁሉም ምርቶች ላይ ከአንድ ብር በላይ ጭማሪ አልተደረገበትም " የሚሉት የዉሃ አምራች ፋብሪካዎቹ ነገር ግን በገበያ ላይ የሚሸጥበት ዋጋዉ ከእነርሱ እዉቅና ዉጪ መሆኑን አስረድተዋል።
#ነጋዴዎች ፦ ከዚህ ቀደም ሲረከቡበት የነበረዉ የዋጋ ተመን ላይ ጭማሪ መደረጉን ገልፀዉ ከአከፋፋዮች የሚሸጥላቸዉ ዋጋ የሶስት ብር ጭማሪ አሳይቷል ብለዋል።
#አከፋፋዮች ፦ የዋጋዉ ጭማሪ ከፋብሪካዎቹ በተወሰነ ደረጃ ቢሆንም የነዳጅ ወጪዎች በመኖራቸዉ እሱን ለማካካስ ለነጋዴዎች ሲያቀርብ ጭማሪ ማድረጋቸዉን ተናግረዋል። ምን ያህል እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ የዉሃ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ መርዕድ ፤ የዋጋዉ መጨመር መኖሩን አረጋግጠዋል።
ለዚህ በምክንያትነት ያነሱት " ፕላስቲክ ጠርሙሶቹ የሚሰሩት ከነዳጅ ተረፈ ምርት በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች በጦርነቱ ሳቢያ ሊጨምር በመቻሉ ፣ ኤክሳይስ ታክስ ከፍተኛ መሆን ፣ ለአምራቾቹ ለስራ ማስኬጃ የብድር እጥረት መኖር ዋነኛዎቹ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
በገበያ ላይ ያለዉ የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ በመሆኑ ቁጥጥር እንዲደረግበት ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበዉ ምላሻቸዉን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
Credit - #CAPITAL #ካፒታል_ጋዜጣ

#አቢሲንያ_ባንክ
መጽሐፍ ማንበብ ብቻ ሳይሆን መክፈልም በአፖሎ ቀሏል። ከጃዕፈር መጽሐፍት - መጽሐፍቶችን ገዝተው በአፖሎ ሲከፍሉ የ20% ቅናሽ ያገኛሉ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

በቴሌብር ሱፐርአፕ በነዳጅ ማደያ፣ በካፌ፣ በሬስቶራንት ወይም ማንኛውም ቦታ ግብይት አከናውነው በተሰጠዎ መስተንግዶ ከረኩ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ቲፕ/ጉርሻ መስጠት ይችላሉ!
ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
ትክክለኛው የኢትዮ ቴሌኮም ቴሌግራም ገፅ ፦ https://t.iss.one/ethio_telecom

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሀዋሳዋ ጸጋ በላቸዉ ፍትህ ከምን ደረሰ ?
ከወራት በፊት በሀዋሳ ከተማ ወስጥ ጸጋ በላቸዉ የተባለች የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ታፈነች የሚለዉ ዜና መሰማቱን ተከትሎ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን በመከታተል ተጠርጣሪውም በቁጥጥር ስር ማዋሉ አይዘነጋም።
በወቅቱ በርካታ የክልሉ ባለስልጣናት በሰጡት አስተያዬትም የጸጋን መብት አስከብሮ ተጠርጣሪዉን ለህግ ማቅረብ ከተከሰተዉ ችግር ባለፈ ለብዙሀኑ ትምህርት ይሰጣል በማለት ቃል ሲገቡም ነበር።
ይሁንና ተጠርጣሪዉ ለህግ ቢቀርብም ጉዳዩን የያዘዉ አካል ግን አሁንም የፍርድ ሂደቱን ማጠናቀቅ አልቻለም።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸዉን የሰጡን የሀዋሳ ከተማ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጉዳዩ ለብዙዎች ትምህርት ለተጎጅዋም ፍትህ ይሰጣል ብለዉ ቢጠብቁም የፍርድ ሂደቱ መዘግየቱ እንዳሳዘናቸዉ ጠቅሰዉ " የዘገየ ፍትህ እንደቀረ ይቆጠራል " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የሚመለከታቸው አካላት እስካሁን ፖሊስ በጠየቀዉ መሰረት የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ መቆየቱንና የመረጃ ማሰባሰብ ስራዉ ጠለፋዉን ከፈጸመው ምክትል አስር አለቃ የኋላመብራቱ ወልደማሪያም በተጨማሪ መረጃ በማቀበል ተጎጅዋ እንድትያዝ ያደረገችዉ የወይዘሪት ወርቅነሽ አጌታ ላይ የሚደረግ መሆኑን በመግለጽ ጥቅምት 20 በተሰጠዉ ቀጠሮ መሰረት የክስ ሂደቱ እንደሚጀምር ገልጸዉ ዝርዝር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ አባል ችሎቱን ተከታትሎ የሚያቀርበዉ ይሆናል።

" ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም " - ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ በከንቲባነት ዘመኔ ቅንጣት ታክል ጥፋት አልሰራሁም አሉ የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሬፌሰር ፀጋዬ ቱኬ። የቀድሞ ከንቲባ ይህ ያሉት ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባወጡት ፅሁፍ ነው። በቅርቡ በተደረገ ግምገማ በ" ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው የተነሱት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በእሳቸው…
#Update #Sidama
የሲዳማ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ፤ የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገለፀ።
የክልሉ ፖሊስ ፤ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው በህግ ሲፈለጉ ነበር ብሏል።
ዛሬ 13/2/2016 ዓ.ም ረፋድ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መያዛቸውን ገልጾ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ሀዋሳ ከተማ የእስረኛ ማቆያ ይገኛሉ ብሏል።
የቀድሞው ከንቲባ ከተጠረጠሩበት ወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ የከፍተኛ የአመራር ግምገማ ረግጠው በመውጣት ተሸሽገው ነበር ያለው የክልሉ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የፀጥታ ግብረ ሀይል ያልተቋረጠ ክትትል ሲደረግ ነበር ሲል አሳውቋል።
የክልሉ ፖሊስ ያወጣው መረጃ የቀድሞውን ከንቲባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር የዋሉት ወደ ሀገር ሲገቡ ወይስ ከሀገር ሊወጡ ሲሉ የሚለውን በግልፅ አያስረዳም።
ከወራት በፊት በሲዳማ ክልል በተደረገ ግምገማ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በ " ብልሹ አመራር " እና " በአፈፃፀም ድክመት " ከስልጣናቸው እንደተነሱ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት መግለፁ አይዘነጋም።
ፅ/ቤቱ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ግምገማውን ረግጠው እንደወጡ ከዛ በኃላም ያሉበትን አድራሻ እንደማያውቅ ገልጾ ነበር።
በኃላም የቀድሞው ከንቲባ የት ሀገር እንደሚገኙ በግልፅ ሳይናገሩ በህክምና ክትትል ላይ እንዳሉና በቅርቡ በህዝብ መኃል ተገኝተው እውነታውን እንደሚያጋልጡ ተናግረው ነበር።
በተጨማሪ ፦
- በከንቲባነት ዘመናቸው ህዝብን የሚጎዳ ቅንጣት ታክል ጥፋት እንዳልሰሩ፤
- እሳቸውን ማሳደዱ የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ ካልሆነ በስተቀር ፣ በክልሉ ይፋ ያልወጡ በህዝብ እንባና ላብ የከበሩ እንኳን ህግ ፈጣሪም ይቅር የማይለዉ ወንጀል/ጥፋት የፈጸሙ የህዝብን ሀብት በሽፋን የሚዘርፉ አካላት እንዳሉ። እነዚህ አካላት የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በቅርብ ይፋ እንደሚወጡ፤
- በክልሉ ያለው ነባራዊ ሁኔ ቡድንተኝነትና በሴራ ፓለቲካ የተተበተበ በመሆኑ እሳቸውም ሆኑ በተሻለ አፈጻጸም ላይ የነበሩ አመራሮች የፓርቲን መርህ ባልተከተለ መልኩ ከኃላፈነት መነሳታቸውን፤
- እድል ያገኙ ቀን እዉነቱን በማውጣት በመረጃና በማስረጃ እንደሚታገሉ ገልጸው ነበር።
በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል ፖሊስ እንዳሳወቀው ግን የቀድሞ የሲዳማ መዲና ሀዋሳ ከንቲባ በህግ ሲፈለጉ ከቆዩ በኃላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

#ለጥንቃቄ
በ " ፌስቡክ " እንደልብ በሚተዋወቁ መልዕክቶች ምክንያት በርካታ ወጣቶች ውድ ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን እየተባሉ እየተጭበረበሩ ነው።
" ፌስቡክ " ላይ ግለሰቦች ክፍያ ከፈፀሙ " Sponsored " የሆኑ መልዕክቶችን ብዙ ሺህ ተጠቃሚዎች ጋር ያደርሳሉ።
ተቋሙ ገንዘብ እየተቀበለ የማያሰራጫቸውን መልዕክቶች ትክክለኝነት እያረጋገጠ ይሁን አይሆን የሚታወቅ አንዳች ነገር ባይኖርም በርካቶች ግን በሀሰተኛ መልዕክቶች ወጣቶች እየተጭበረበሩ ይገኛሉ።
ከሰሞኑን ስለ " ሀሰተኛ የትሬድ ስራ " እና በዛ ምክንያት ገንዘባቸው ተበልቶ እና መፍትሄ አጥተው ስለተቀመጡ ሰዎች ዳሰሳ መስራታችን ይታወሳል።
ለዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ መልክ ስለሚደረግ ማጭበርበር በአጭሩ እንመለከታለን፤ ይኸውም ዋና ዓላማቸው ስራ የሌላቸውን ወጣቶች እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን በሀሰተኛ መልዕክቶች አታሎ ገንዘባቸውን ማጭበርበር ነው።
በፌስቡክ ላይ ስፖንሰር በሚሆን መልዕክት "
- ስራ የሌላችሁ ስራ እንቀጥራችኃለን፣
- በቀን ውስጥ ከ20 ሺህ ብር በላይ ትሰራላችሁ ፣
- በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ ገንዘብ በማግኘት የራሳችሁን ስራ ትጀምራላችሁ " የሚሉ የማጭበርበሪያ መልዕክቶች በስፋት ሲሰራጩ ተመልክተናል።
ወጣቶች እነዚህን አካላት ለዚሁ ጉዳይ በሚያናግሯቸው ጊዜ በቅድሚያ የምዝገባ ገንዘብ ይጠይቋቸዋል፤ በኃላም የውሃ ሽታ ይሆናሉ።
የወጣቶችን ስራ ማጣት እንደ አጋጣሚ ተጠቅመው ከሌላቸው ገንዘብ ላይ ለመንጠቅ የሚሰሩት እነዚህ አስነዋሪ አጭበርባሪዎች መልዕክታቸውን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚጠቀሙ ቢሆንም በይበልጥ የተከፈለባቸው የ " ፌስቡክ " መልዕክቶች ዋነኛዎቹ ናቸው።
ምን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ?
- አንድ የስራ ማስታወቂያ ስንመለከት ስራው የት እንደሆነ ? የቢሮው አድራሻ ? ህጋዊነቱን የሚያሳይ ማስረጃ ? መጠየቅ አለብን።
- " ስራ ለመቀጠር ብር ክፈሉ " የሚሉ ዘራፊዎችን ለምን ? ብሎ ማፋጠጥ ፤ እንዲሁም ስልካቸውን እና አድራሻቸውን መመዝገብ ይገባል።
- አንድ ስራ በቀን 100 ሺህ ፣ 50 ሺህ ብር ይከፈልበታል ሲባል እንዴት ? በምን መልኩ ? ምን ተሰርቶ ? በየትኛው ህጋዊ መንገድ ብሎ መጠየቅ እና መጠራጠር ይገባል።
በ " ፌስቡክ " ወይም በ " ቴሌግራም " ላይ የማረጋገጫ ምልክት ያላቸው ሰዎች ሁሉ እውነተኛ ናቸው ብላችሁ እንዳታምኑ፤ እነዚህ ምልክቱን ገዝተው መጠቀም ይችላሉና።
ከምን በላይ በተለይ " ፌስቡክ " በክፍያ የሚያስተላልፋቸውን መልዕክቶች ትክክለኝነትን የሚያረጋግጥበትን መንግድ መዘርጋት ካልቻለ ትልቅ ቀውስ መፍጠሩን ይቀጥላል።
ማንኛውም ሰው ተነስቶ ለፌስቡክ የመክፈያ መንገድ ካበጀ ፤ ዜሮ ተከታይ ቢኖረም ፤ ህገወጥ ዝርፊያ ላይ የተሰማራ ቢሆንም እስከከፈለ ድረስ ማስረጃ የሌለው መልዕክት ሊያሰራጭ ይችላል።
በተለይም በርካታ ወጣቶች ስራ ፈላጊ በመሆናቸው ስራ ያላቸው ዜጎችም ከሚያገኙት ገቢ የተሻለ ለማግኘት ሲሉ እነዚህን አካላት ያነጋግራሉ። የሚጠየቁትን ገንዘብም ክፈሉ ሲባሉ ሊከፍሉ ይችላሉ።
አንደንዶች ደግሞ በፌስቡክ የክፍያ መልዕክት የሌላቸው እና የማይሸጡትን ዕቃ በማስተዋወቅ ሰዎችን ገንዘብ ካስላኩ በኃላ የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ።
" ፌስቡክ " አሰራሩን ማስተካከል ካልቻለና ገንዘብ እየሰበሰበ ብቻ በትንሽ ዶላር ብዙሃን ጋር ያልተረጋገጡ መልዕክቶችን የሚያሰራጭ ከሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር ባለማድረጉ በተጠቃሚዎች ላይ ለሚደርሰው ድርጊት ኃላፊነት ሊውስድ ይገባል።
ከምንም በላይ ግን ተጠቃሚዎች እንዲሁም ውድ ቤተሰቦቻችን እራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ።
#TikvahEthiopia

ለ116ኛው የሰራዊት ቀን ከረቡዕ ለሊት 8 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።
116ኛው የሰራዊት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይከበራል፡፡
በዚህም መርሃግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል።
በዚህ መሰረት፦
- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ ፣
- ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ ፣
- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ ዝግ ) ፣
- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ፣
- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ ላይ፣
- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ራስ ሆቴል ላይ ፣
- ከሃያሁለት አደባባይ ወደ ኡራኤል የታችኛው መንገድ ሙሉ ለሙሉ
- መስቀል አደባባይ፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ፣ልደታ ፀበል እና የመከላከያ ግቢ ድረስ በመምጫና በመመለሻ ወቅት ፣
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ ፣
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣
- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባንቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ
- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ECA ጫፍ ላይ ለጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም አጥቢያ ረቡዕ ከለሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ግብረኃይሉ አሳውቋል።

ወርቃማው!!
ጊዜ ወርቅ ነው ፤ ወርቅ ደግሞ ሃብት ነው
በጥረትዎ ያገኙትን በወርቃማው ያስቀምጡ!!
የባንካችንን የወርቃማ ዘመን የቁጠባ ሒሳብ በመክፈት የ 9% ወርቃማ ወለድ ተጠቃሚ ይሁኑ::
ለአዳዲስና ፈጣን መረጃዎች የቴሌግራምና የፌስቡክ ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡
Telegram - https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
Facebook - www.facebook.com/globalbankethiopiasc
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!!

Computer Vision Syndrome(CVS)
- ለረጅም ሰዓት ኮምፒውተር ወይም ዲጂታል ስክሪን ላይ መመልከት (ጊዜ ማሳለፍ) ዓይናችን ላይ ከሌላው ጊዜ የበለጠ ጫና ያሳድራል፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ችግሮች አብረው ይከሰታሉ፡፡
እነዚህ ችግሮች የሚከሰተቱትም ፦
▪️ሳያቋርጡ ለረጅም ሰዐት መጠቀም
▪️የክፍላችንና የስክሪናችን ብርሀን ሳይመጣጠን ሲቀር
▪️ስክሪናችን ከዓይናችን የተመጠነ ርቀት ላይ ሳይቀመጥ ሲቀር
▪️ልክ ያልሆነ አቀማመጥ
▪️ያልታከመ የዕይታ ችግር ካለ
ምልክቶቹ ፦
- ብዥ ማለት
- የዓይን መድረቅ፣የዓይን መቅላት
- ከዕይታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የራስ ምታት(Eye strain)
- ዓይን መድከም (eye fatigue)
- የአንገትና ትከሻ ህመም
ምን እናድርግ ?
- ስክሪናችንን ከዓይናችን ቢያንስ ከ40-50cm(በክንድ ርቀት) ላይ ማስቀመጥ
- ክፍላችን በቂ ብርሃን እንዲኖረዉ ማድረግ
- የዕይታ ችግር ካለ ወደ ህክምና በመሄድ መታከም
- የአንገትና የትከሻን ህመም ለመከላከል አቀማመጣችንን ማስተካከል
- ከስክሪን ጨረር የሚከላከሉ መነፅሮችን እንደ(Blue cut, Anti-reflective coating) መነፅሮችን መጠቀም
- በየመሀሉ ዕረፍት መውሰድ (በየ20 ደቂቃው ዓይን ዘና እንዲል ለ20 ሰከንድ ያህል ከስክሪኑ ራቅ ወዳሉ ነገሮች መመልከት)
- ዓይን ማርገብገብ (እንባ በደንብ እንዲሰራጭና ዓይናችን ለብዙ ሰዐት ትኩረት ከማድረግ የተነሳ የሚመጣውን የዓይን ድርቀት ይከላከላል፡፡)
▫️በዚህ ጊዜ የአብዛኞቻችን ህይወት ከዲጂታል ስክሪን ጋር የተቆራኘ ነውና የዓይናችን ጤንነት ግድ ሊለን ይገባል።
#AmericanOptometricAssociation

እርዳታ ለሚፈልጉ ወገኖች ምን ያህል ድጋፍ እየተደረገ ነው ?
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን፦
- ኪረሙ፤
- ሁሙሩ እና አጋምሳ፣
- ቤጊ፤
- ጊዳሚ፤
- ቆንዳላ፤
- ሆሮ ሊሙ በተሰኙ ቦታዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር እንዲሁም በትግራይና በአፋር ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸው፣ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ሕልፈተ ሕይወት መድረሱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መልዕክት ያስረዳል።
በተለይ በኦሮሚያ፣ አማራና አፋር ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ረሃቡ እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የድጋፍ ፈላጊዎቹን ጥያቄ ለብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ያቀረበ ሲሆን፣ የኮሚሽኑ ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያና ተወካይ ዳይሬክተር አቶ አታለል አቦሃይ፣ "ወደ ዋግኽምራ፣ ወደ ሰሜን ጎንደር ድርቅ ያጠቃቸው አካባቢዎች ብዙ ጊዜ ትግራይን ጨምሮ አልሚ ምግብ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ነው ሲሰጥ የነበረው። እርሱ ከእርዳታው ከወጣ ስምንት ወራት አልፎታል የእርሱ መውጣት ተፅዕኖ ይኖረዋል" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ድርቅ በተከሰተባችው አካባቢዎች ድጋፍ ለሚሹት ዜጎች ሁሉ እርዳታ ተደራሽ እንዳደረጉና እንዳላደረጉ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ አታለል፣ "አሁን የተላከው እህል እኮ ለአንድ ክልል በቂ ላይሆን ይችላል ግን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ይማዳረስ ሥራ ነው እየሰራይ ያለነው" ሲሉ አስረድተዋል።
የሕዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያው አጠቃላይ እንደ አገር 20 ሚሊዮን ተረጂዎች እርዳታ ፈላጊ ሰዎች እንዳሉ ገልጸው፣ "ለ20 ሚሊዮኑ ሁሉ አድርሰናል አንልም" ነው ያሉት።
አክለውም፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ 20 ሚሊዮን እርዳታ ፈላጊዎች ሁሉ ድጋፍ ማድረስ ስለማይቻል የቅድሚያ ቅድሚያ የሚያስፈልጋቸው ተብሎ ከየክልሉ ተለይተው በደብዳቤ ለተላኩ ተረጂዎች ሁሉ ግን ከአሥር ቀናት በፊትም ለ4 ሚሊዮን ሰዎች 610 ሺሕ ኩንታል እህል መላካቸውን ተናግረዋል።
አሁንም የቅድሚያ ቅድሚያ ተብለው የተለዩ እንዳሉ የጠቆሙት አቶ አታለል፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እርዳታ ቢያቆምም መንግሥት ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንደከዚህ ቀደሙ እርዳታ ለማድረግ ከመጣ የኮሚሽኑ ቢሮ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎችና ድርቅ ተከስቶባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች፣ በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር ዞን፣ በዋግኽምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር፣ በኦሮሚያ ክልል በተለይ ወለጋ ዞን፣ በአፋር ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች በከፋ ረሃብ ውስጥ መሆናቸው በተደጋጋሚ ይነገራል።
ዩኒሴፍ በበኩሉ ጉዳዩን በተመለከተ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው ሪፓርት በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን፣ ከ942 ሺሕ በላይ ስደተኞችን፣ ከ16 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ጨምሮ በአጠቃላይ የሰብዓዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር ከ34 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ማስታወቁ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያፈልጋቸው 34.4 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ ከ674 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ፣ ከዚህም ውስጥ 345.4 ሚሊዮን ዶላር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች፣ 255.7 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሚደረግ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚሆን፣ ይሁን እንጅ የተገኘው ገንዘብ 187.7 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደሆነ ሪፓርቱ ያስረዳል።
ጥንቅሩ በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

ከአንድ ሲኒ ቡና ዋጋ በታች ካርድ በመሙላት ቀኑን ሙሉ በነፃ እንደዋወል! የ5ብር ካርድ እንሙላ ከሳፋሪኮም ሳፋሪኮም በነፃ እንደዋወል::
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#EthiopianCargo 🇪🇹
በትላትናው ዕለት በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣ #ዱባይ በተካሄደ የ " አረቢያን ካርጎ አዋርድ " በደንበኞች ምርጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ " በአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየርመንገድ " ተብሎ ተመርጧል።
በዚሁ የሽልማት ዘርፍ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ኦፕሬት የሚያደርጉት አየር መንገዶች በእጩነት ቀርበው የነበረ ቢሆንም አየር መንገዱ ሁሉንም በመብለጥ ነው በአፍሪካ - ምርጡ የካርጎ አየር መንገድ ተብሎ የተሸለመው።