TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥቆማ

የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ተሳተፉ !

መኖሪያ ቤት/ቦታ ማለት ለአንድ ሰው ወይም ለአንድ ቤተሰብ ምን ማለት ነው ?

ሕይወት፣ ትርጉም ያለው ሕይወት፣ ምንድን ነው ? የአንድ ኢትዮጵያዊት ሴት፣ ወይም የአካል ጉዳተኛ ወይም የተፈናቃይ ወይም የአረጋዊ ሕይወት ምን ይመስላል ?

በሕይወት እና በመኖሪያ ቤት ዙርያ እነዚህን እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለኪነጥበብ አፍቃሪዎች፣ ለኪነጥበብ ሙያ ተማሪዎች፣ ባለሞያዎች እና አማተሮች እንዲሁም ለመገናኛ ብዙኃን አባላት እና ሌሎችም በኪነጥበብ እና በሰብአዊ መብቶች መካከል ያለውን ትስስር ማሳየት ለሚፈልጉ ሁሉ፣ በኢሰመኮ አዘጋጅነት በሚካሄደው የ3ኛው ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር የቀረቡ ናቸው።

ኑ፣ ተሳተፉ፣ አብረን እንድናሰላስል የሚረዱ የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ሥራዎቻችሁን ለዕይታ አቅርቡ!
በውድድሩ ለመሳተፍ እና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዝርዝሩን በዚህ ይመልከቱ - https://bit.ly/46sReAw
#ጥቆማ #ከጠቀማችሁ

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወርሰው የሚገኙ 171 ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ተጨራቾች የጨረታ ሰንድ በመግዛት በጨረታው ላይ የሚወጡትን ተሽከርካሪዎች በአካል በመመልከት መጫረት ትችላላችሁ ተብሏል። ጨረታው በ26/02/2016 ዓ/ም ጥዋት 4 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:15 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0221118429 ላይ መወደል ይቻላል።

አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የቤትና የጭነት ተሸከርካሪዎች ፦
- DUMP TRUCK፣
- IVECO FIAT፣
- TOYOTA HAILUX፣
- TOYOTA COROLLA፣
- TOYOTA  VITZ፣
- TOYOTA HAICE፣
- TOYOTA YARIS፣
- TOYOTA CHR፣
- HYUNDAI፣
- SUZUKI፣
- MISTUBUSHI ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የተጠቀሱት ተሸከርካሪዎች የጨረታ ሰነድ ከቀን 20/02/2016 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት ይቻላል።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

  የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከፎኔክስ ኢንደስትሪ ኃ/የ/የግ/ማህበር የተያዘ፦
- የኘላስቲክ ወንበር ማምረቻ ማሽን፣  የማሽኑ ማቀዝቀዣ (cooler)፣ የማሽኑ ጥሬ ዕቃዎችና ሌሎች ተጓዳኝ ዕቃዎች፣

ከተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ ፦
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የመብራት አምፖሎች፣
- ፍሎረሰንቶች፣
- ፖውዛዎች እና የውሃ ተቀባሪና ተንጠልጣይ የተለያዩ ቧንቧዎች፣

🚘 ከቲ.አይ.ቢ ኬተሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህ እና ኦክስፎርድ አማልጌትድ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 3 ተሽከርካሪዎች ናቸው።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

#ጉምሩክኮሚሽን #አዲስዘመን #ገቢዎችሚኒስቴር

* ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በጥቆማ መልክ የቀረበ።

@tikvahethiopia
#NEBE

በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በለቀቁት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ምትክ አዲስ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ለመተካት 8 አባላት ያሉት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ ዛሬ ተሰይሟል።

ይኸው ኮሚቴ የተሰየመው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነው።

የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ላይ በሰፈረው መሰረት #ጠቅላይ_ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል።

የተቋቋመው መልማይ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱ የተነገረ ሲሆን በቅርቡ #ጥቆማ መቀበል እንደሚጀምር ተገልጿል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሰቢ መልማይ ኮሚቴው ፦
- ቀሲስ ታጋይ ታደለ (ሰብሳቢ)
- ፕ/ር ተከተል ዮሐንስ (አባል)
- አቶ ባዩህ በዛብህ (አባል)
- ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ (አባል)
- አቶ ካሳሁን ፎሎ (አባል)
- ወይዘሮ ርግበ ገብረሃዋርያ (አባል)
- ወይዘሮ እንግዳዬ እሸቴ (አባል)
- ኢ/ር መላኩ እዘዘው (አባል)

መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#TOYOTA

ቶዮታ / Toyota ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ በዓለም ገበያ በዋነኝነት #በአሜሪካ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን  ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዟል።

ቶዮታ እንዲሰብሰቡ ያዘዘው ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎችን ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የ " ኤርባግ " ደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።

ከ2020 እስከ 2022 ወደ ገበያ የቀረቡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች (በዋነኝነት #አሜሪካ) ከ " ኤርባግ " ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል።

ችግሩ በፊት ለፊት ተሳፋሪ መቀመጫ በኩል በስህተት ከተሰራ የ " ኤርባግ ሴንሰር " ጋር የሚያያዝ ሲሆን ምናልባትም በአደጋ ጊዜ " ኤርባጉ " አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል። ይህ አደጋ በሚፈጠር ጊዜ ኩዳቱ እንዲጨምር ያደርጋል።

ቶዮታ የትኞቹ ሞዴሎች ይሰብሰቡ አለ ?

#ቶዮታ

ኮሮላ (2020 - 2021)
ራቭ4 ፣ ራቭ4 ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ሃይላንደር፣ ሃይላንደር ሃብሪድ (2020 - 2021)
አቫሎን ፣  አቫሎን ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ካምሪ፣ ካምሪ ሃብሪድ (2020 - 2021)
ሴና ሀይብሪድ (2021)

#ሌክሰስ

ES250 (2021)
ES300H (2020-2022)
ES350 (2020-2021)
RX350 (2020-2021)
RX450H (2020-2021) የተሰኙ ከ2020 እስከ 2022 ላይ የተመረቱት የ " ኤርባግ " ችግር ስላለባቸው ይሰብሰቡ ብሏል።

ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን #እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።

የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው #ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል።

ምርመራው ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር መታየቱን ገልጿል።

ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

#ጥቆማ ፦ ከደህንነት ጋር በተያይዘ በተለይም በአሜሪካ እንዲሰበሰቡ የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን ቼክ ለማድረግ https://www.nhtsa.gov/recalls በዚህ አድራሻ መጠቀም ይቻላል። የመኪናውን መለያ ቁጥር (VIN) በማስገባት ማወቅ ይቻላል።

Credit - #AlAiN / #Reuters / #Toyota_News_Room

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፤ የገና ሥጦታ ሎተሪ በትላንትናው ዕለት መውጣቱን ገልጿል።

10 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የዕጣ ቁጥር 1616519 ሆኖ ወጥቷል።

አጠቃላይ የዕጣ ዝርዝሩ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#የሥዕል_ውድድር #ጥቆማ

በመቐሌ እና አከባቢው የምትገኙ የሥዕል ችሎታ ያላችሁ ወጣቶች ሪድም ዘጀነሬሽን ከUSAID/OTI ጋር በመተባበር ላዘጋጀው የቡድን የስዕል ውድድር ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ቀደም በሰላም ጉዳዮች ላይ ተከታታይ ውድድሮች ያካሄደው ሪድም ዘጀነሬሽን አሁን ደግሞ በመቐሌ ለሚገኙ ችሎታው ላላቸው እድሜያቸው 13 - 18 ላሉ ታዳጊዎችና 19 - 29 ላሉ ወጣቶች በአጠቃላይ ለ50 ተሳታፊዎች እድሉን አመቻችቷል።

ዘላቂ ሠላም፤ ጽናት፤ እንዲሁም የማኅበራዊ ችግሮችን ማከም በሚችሉ ኃሳቦች ላይ ተወዳዳሪዎች ተመርጠው የሥዕል ውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ይደረጋል። በውድድሩ የተመረጡ ሥራዎች በክልሉ በሚዘጋጁ ፎረሞች ላይ የሚቀርብ ይሆናል።

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፥ እስከ ጥር 24 ድረስ ማመልከት የሚችሉ ሲሆን በተከታዩ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።  https://forms.gle/qYmEMneTagoSgKVQA

ዝርዝር መስፈርቱን ለማግኘት https://telegra.ph/Art-as-a-path-to-Healing-01-29

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን በጨረታ ለሽያጭ አቅርቧል።

ኮርፖሬሽኑ ፤ " ያለብኝን የፋይናንስ እጥረት በመፍታት ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቼ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንድችል ከዲዛይን ግንባታ ቢሮ ጋር በመሆን በመንግስት በተመደበ ካፒታል በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው #የተጠናቀቁ
➡️ 3,146 የመኖሪያ ቤቶችን
➡️ 306 የንግድ ቤቶችን በድምሩ 3,452 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሬ በሽያጭ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ " ሲል አሳውቋል።

ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ከ27/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/06/2016 ዓ.ም ድረስ ቅዳሜን እስከ 11፡00 ሰአት እና እሁድ ግማሽ ቀን ጨምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ማታ 1፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላል ተብሏል።

የሰነድ መሸጫ ቦታ ከላይ ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ [email protected] / [email protected] ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ክረምቱ ይገባል በኛ በኩል ጊዜውን ከዚህ በላይ መግፋት አንችልም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " ምርጫው የሚደረግባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታ፣ የበጀት እና ድምፅ የሚሰጥበት ቀን እና ጊዜ ይታሰብበት " - ተፎካካሪ ፖርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፀጥታ ችግር ምክንያት 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ያልተደረገባቸው እና ቀሪ ምርጫ የሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣…
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ አስፈፃሚዎችን አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።

ቦርዱ ፦

👉 በአፋር ክልል (በ ዞን 5 በሚገኙ ወረዳዎች በሙሉ ፣በ ዞን 3 ቡሬሞዳይቱ እና ገዋኔ፤ በዞን 2 ዳሎል እንዲሁም በዞን 4 ጉሊና) የምርጫ ክልሎች

👉 በቤንሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ዞን አሶሳ ሆሃ፣ አሶሳ መገሌ፣ መንጌ እና ኦዳብልድጉል፤ በካማሺ እና መተከል ዞኖች ሁሉም ወረዳዎች

👉 በሶማሌ ክልል ጅጅጋ ከተማ

👉 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቃን ማረቆ 2 ላይ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ይህንን ተከትሉ መስፈርት የሚያሟሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን አወዳድሮ ለመቅጠር እንደሚፈልግ ገልጿል።

➡️ ከ18 አመት በላይ የሆናቸው
➡️ ከዚህ በፊት በምርጫ አስፈጻሚነት ያገለገሉ
➡️ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆኑ
➡️ 12ተኛ ክፍል እና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጀት ያላቸው
➡️ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ መስራት የሚችሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት ክፍት በሚሆነው የቦርዱን የማመልከቻ ሊንክ ፦ https://pw.nebe-elections.org/recruitment  በመጠቀም ማመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል።

ቦርዱ ፤ የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ እንደሚያበረታታ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

" የ2024 ESP ማመልከቻ ማስገባት ይቻላል " - የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የEducation USA Scholars Program (#ESP) 2024 ማመልከቻ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

ESP በአካዳሚክ ጠንካራ የሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ወደ አሜሪካ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች #እንዲያመለክቱ የሚረዳ የአራት ሳምንታት የሥልጠና መርሃ ግብር ነው።

ዓላማውም ደግሞ የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሰለጠኑ እና ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መሪዎችን ማፍራት እንደሆነ ኤምባሲው አመልክቷል።

ከአመልካቾች 20 ከፍተኛ የአካዳሚክ ብቃት ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በኤምባሲው ይለያሉ። ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ሪከርዳቸው፣ እንዲሁም በኢንተርቪው እንዲለዩ ይደረጋል።

ከጠቅላላው 20 የመጨረሻ እጩዎች መካከል፣ 15 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በኢኮኖሚ የተቸገሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ፈተናዎች፣ ከአሜሪካ ቪዛ ክፍያ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን በሚሸፍነው የOpportunity Program Fund (#OPF) ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመረጣሉ።

የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ስኬታማ ዕጩዎች ወደ አሜሪካ የራውንድ ትሪፕ ትኬት ያገኛሉ።

ቀሪዎቹ 5 ተማሪዎች በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ #በነጻ ይሳተፋሉ ነገር ግን የዝግጅት ወጪን ከራሳቸው ምንጭ ይሸፍናሉ። የሞባይል ዳታ ወጪዎች ለሁለቱም የፕሮግራም ተሳታፊዎች በኤምባሲው ይሸፈናሉ።

ማመልከቻ እስከ ሚያዚያ 10/2024 (5:00 pm EAT) ማስገባት ይችላል ተብሏል።

ለማመልከት አስፈላጊ መስፈርቶች ምንድናቸው ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩና ትምህርታቸውንም እዚሁ ኢትዮጵያ እየተከታተሉ ያሉ።

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ/ች #ኢትዮጵያዊ ተማሪ፣

በዚህ የትምህርት አመት መጨረሻ 11ኛ ክፍልን ያጠናቅቁ እና ከመስከረም 2024 ጀምሮ 12ኛ ክፍል የሚማሩ፣

በጠቅላላ 4 ሳምንታት የESP መርሃግብር ለመሳተፍ ቃል መግባት የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ስታመለክቱ የሚያስፈልጉ ፦
1ኛ. የሁለተኛ ደረጃ ትራንስክሪፕት (9፣ 10፣ 11)
2ኛ. ከትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3ኛ. የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸውና ለOpportunity Fund Program (OFP) የሚያመለክቱ ከትምህርት ቤት ወይም ከቀበሌ የቤተሰብን #ዝቅተኛ የኢኮኖሚያ ሁኔታ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ያስፈልጋል።

የማመልከቻ ሊንክ እና ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይመልከቱ ፦ https://sites.google.com/amspaceseth.net/educationusa-esp2024

@tikvahethiopia