TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ #ዋግኽምራ " ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ 9 አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። … የህፃናትና የእናቶች የህክምና አገልግሎት አደጋ ውስጥ ነው " - የዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ፦ * የመድኃኒት፣ * የትራንስፖርት፣ * የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ በዞኑ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ፈተና እንደሆነባቸው በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ…
#ዋግኽምራ

" ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም" - ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ

በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- ድርቁ በጣም #እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት ነው ያለው።

- የምግብ እጥረት እንዳለባቸው በተረጋገጠው መሠረት #ህፃናት #ነፍሰጡር#አጥቢ እናቶች ወደ ተለያዩ ፕሮግራሞች ገብተው ሊደገፉ ነበር። እስቲል ማሟያ ምግብ በምንለው እጥረት እስካሁን ምንም  አልተደረገላቸውም። እኛ #እየጮህን ነው። እስካሁን የመጣ፣ የተደረገ ድጋፍም የለም።

- በሌላ በኩል ድርቅ በተከሰተባችው አካባቢዎች አጠቃላይ የጤና መድህን የምንለው ፕሮግራም የአመት ክፍያው የሚያልቀው አሁን ነው። አልፎ ለማስከፈልም አልቻልንም። በጠቅላላ የጤና አገልግሎታቸው በጣም #የሚያሳዝን ሁኔታ እየገባንበት ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምን ያህል ህፃናትና እናቶች ናቸው አሁን አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው? 

* በድርቅ የተጎዱት ወደ 33,000 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው ከአንድ ወረዳ ብቻ። በአጠቃላይ እንደ ዞን በዚህ ድርቅ ተጎድተዋል ብለን የምናስባቸው ከ180,000 በላይ ህዝቦች ናቸው። 

* ከእዚህ ውስጥ የሚበዙት ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ናቸው። ወደ 7,000 ይደርሳሉ #ነፍሰጡርና አጥቢዎች ብቻ። ከአምስት ዓመት በታች #ህፃናት ኦልሞስት ወደ #18,000 አካባቢ ይደርሳሉ። እነዚህ ሁሉ አስቸኳይ ምግብ የሚፈልጉ ናቸው።

አቶ አሰፋ ታጣቂዎችን በተመለከተ ምን አሉ ?

° ታጣቂዎች የመጀመሪያ ታርጌታቸው ጤና ተቋማትን መዝርፍ ነው። እኛ አገልግሎት ላለማቋረጥ እየታገልን ነው እንጂ እስካሁን 3 የሚደርሱ ጤና ጣቢያዎች፣ ወደ 12 የሚደርሱ ጤና ኬላዎች አሁንም በየቀኑ በታጣቂ ኃይሎች ይዘረፋሉ።

° መጀመሪያ በስፋት #ፕላምፕሌት አልሚ ምግቦችን ሲወስዱ ነበር። እነርሱ ምግቦች ለሕፃናትና ለእናቶች ካልደረሱ ወደዛ መውሰድ አስፈላጊ አይደለም ብለን  ስናስቆማቸው ጤና ኤክስቴሽኖችን እናንተ ናችሁ የደበቃችሁት አምጡ አስልኩ አይነት ነገር ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ድብደባዎች እያደረሱ ነው።

° ጋዝጊቭላና ድሀና ወረዳዎች አዚላ የሚባል ክላስተር አለ፣ በዚያ ስር ያሉ ጤና ኬላዎች፣ በጋዝጊብላ ወረዳ ደግሞ አዱፍቃ፣ አርካ ጤና ጣቢያዎች ስር ባሉ ጤና ኬላዎች ላይ ነው እንግልት እየተደረገ ያለው።

° የጤና አገልግሎቱ እየተቆራረጠ ነው። በቋሚነት እየተሰጠ አይደለም። ከአንድ እስከ ሶስት ቀናት በተከታታይ ይሰጣል። ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመጡና እደገና ያቋርጡታል። ኮሚዩኒቲ ሰርቪስ የምንለው በጤና ኬላ ደረጃ የሚሰጠው ኦልሞስት እየቆመ ነው። 

ለመፍትሄው ከማን ምን ይጠበቃል?

☑️ የአጋር ድርጅት ድጋፍ የተቀዛቀዘ ነው። ድጋፍ ማድረግ ቢችሉ የሰዎችን ሕይወት ይታደጋሉ። ከጸጥታው  ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል ኤኒይወይስ ስለ ረሀብ ደግሞም ስለ ህፃናት፣ ነፍሰጡር አጥቢ እናቶች ረሃብ ነው እያወራን ያለነው። 

☑️ አይደለም እንደዚህ ድርቅ ተከስቶ አፍጦ መጥቶ ኖርማል በመደበኛ ሁኔታ እንኳ እንደዚህ ለይተናቸው የምግብ እጥረት እንዳለባቸው ሲታወቅ ወዲያውኑ ወደ ፕሮግራም ገብተው መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia