#ኢትዮጵያ #ቻይና
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው።
ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል።
ከሁለትዮሽ ውይይቱ በመቀጠል ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ጠ/ሚ ሊ ኪያንግ በተገኙበት በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ መስኮች 12 ያህል የትብብር ስምምነቶች እና ሁለት የፍላጎት ሰነዶች ተፈርመዋል።
ዶ/ር ዐቢይ በቻይና ይፋዊ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ ከአራት ዓመት በኃላ ሲሆን በቀጣይ በሚካሄደው 3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ አለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፎቶ፦ #PMOffice
@tikvahethiopia

የእህቱ ልጅ በሆነ የሰባት አመት ህፃን ላይ የግብረሰዶም ወንጀል የፈፀመ ተከሳሽ በፅኑ እስራት መቀጣቱ ተገለጸ።
ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸመው በሰኔ ወር 2014 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ማሪያም ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚኖርበት ቤት ውስጥ ነው።
የ37 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ እና የተከሳሹ እህት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ተከሳሹ ሰው የሌለበትን አጋጣሚ ጠብቆ የሰባት ዓመት ዕድሜ ያለው የእህቱን ልጅ በስለት በማስፈራራት የግብረ ሰዶም ወንጀል ፈፅሞበታል።
ፖሊስ በቀረበለት ጥቆማ መነሻነት ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል፡፡
የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጥ ሰሞኑን በዋለው ችሎት በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ወላጆች ልጆቻቸው ለእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆኑ ዕድሜያቸውን መሰረት በማድረግ አስቀድመው በግልፅ መወያየት እና ተገቢውን ክትትልና ጥበቃ ማድረግ እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፏል።
#AddisAbabaPolice

TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው። ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል። ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ…
#ትግራይ
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርዓት ከታወጀ ዛሬ 3ኛ ቀኑ ሲሆን ፤ ሌላ ጊዜ በሳምንታዊ የሰኞ ገበያዋ ከመላ ክልሉ ፣ ከዓፋርና የአማራ ክልል አዋሳኝ አከባቢዎች በመጡ ገበያተኞች ትድምቅ የነበረች መቐለ የንግድ ተቋማትዋ ተዘግተው ፣ መኪኖች መንቀሳቀስ አቁመው ጭር ማለትዋ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ፤ በውጭ አገራት የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ የክልሉ የሰማእታት የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአት በማስመልከት ሃይማኖታዊ ፀሎትና ሌሎች ዝግጅቶች ማከናወናቸውን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ።
በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ፦
- በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፣
- በኔዘርላንድ ፣
- በጀርመን ሙኒክና ፍራንክፈርት ከተሞች ፣
- በእንግሊዝ ለንደን፣
- በስዊድን ስቶክሆልም ከተማ ፣
- በአሜሪካ ዋሽንግተን ደሲና አከባቢዋ ፣
- በአረብ አገራትና በሌሎች የሚኖሩ የትግራይ ዳያስፓራ አባላት ሰማእታት የሚዘክር የፀሎት ፣ የሻማ ማብራትና የተለያዩ ስነ-ሰርአቶች አከናውነዋል።
በተያያዘ ዓለም አቀፍ የትግራይ ማሕበረሰብ ሙሁራንና ባለሞያዎች ማህበር (GSTS) የሰማእታት የሃዝንና የክብር ቀን ስነ-ሰርዓት አስመልክቶ ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ የተሰማው ጥልቅ ሃዘን በመገለፅ ሰማእታቱ የተሰውለት የትግራይ ድህንነትና ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር ከመታገል ጎን ለጎን የሰማእታቱ ቤተሰቦች ለማቋቋምና ትግራይ መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሌ እወጣለሁኝ ብሏል።

#ETHIOPIA
ከሰሞኑን የባህር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።
ጉዳዩ ክብደት እንዲያገኝ ያደረገው ደግሞ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ መነሳቱ ነው።
አንዳንዶች ጉዳዩ መነሳቱን እና መነጋገሩን ሲያደንቁ ሌሎች ደግሞ " ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ፤ አጀንዳ ለመስጠት ነው ፤ በቅድሚያ የሀገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ይቀድማል " በሚል ተቃውመዋል።
ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የህዝብ እንደራሴዎችን ሰብሰበው የሰጡት ማብራሪያ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተሰራጭቶ ነበር።
በዚህም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።
- ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎትን በግልፅ አስቀምጠዋል።
- የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሄደው እና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ሃሳብ የሕልውና ጉዳይ ነው መሆኑን አመልክተዋል።
- ቀይ ባሕር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና ጥፋት መሠረት እንደሆኑ በመግለፅ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ መሸሽ እንደማይስፈልግ ገልጸዋል።
- ለባህር በር መተላለፊያ መገኘት ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊላንድ አማራጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማንሳት ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊሳካባቸው የሚችልባቸውን #ከግጭት_ውጪ ያሉ አማራጮችን አስረድተዋል።
ይህም ፦
የታላቁ ሕዳሴ ግድብን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሎኮም ጨምሮ በትልልቅ የአገሪቱ ተቋማት ውስጥ ድርሻ መስጠት እና የመሬት ልውውጥ ማድረግ እንደሚቻል ነው።
- በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የባህር በር ጉዳይ ከመነጋገር ከመመካከር መሸሽ እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ነጥሎ ስለ አንድ ሀገር ትኩረት ያላደረገ ቢሆንም ከኢትዮጵያውን አልፎ #ኤርትራውያንም ስለጉዳዩ አስተያየት ሲሰጡበት ተስተውሏል።
አንዳንዶች ስርዓት ባለው መልኩ ቢሰራበት እና እስካሁን ያልተፈቱ ችግሮች ተፈተው መግባባት ላይ ተደርሶ ቢሰራበት መላው ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም ጉዳይ እንደሆነ ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ በፍፁም ይህ ጉዳይ ለውይይትም ሆነ ለንግግር ሊቀርብ አይገባም ባይ ናቸው።
ዛሬ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ሰሞነኛው አጀንዳ ስለሆነው የውሃና የባህር በር ጉዳይ " ሰም ያልጠቀሰ " አጭር መግለጫ አሰራጭቷል።
የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአስመራ ያወጣው ስም ያልጠቀሰው አጭር መገለጫ " በቅርቡ ጊዚያት ስለ ውሃ እና የባህር በር የመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች የተባለና ' ተብለዋል ' የተባለው መጨበጫ የለውም። ይህም ያላስገረመው ታዛቢም የለም " ይላል።
ስም ያልጠቀሰው ይህ አጭር መግለጫ የኤርትራ መንግስት እንደ ሁልግዜው ይህንን ወደ መሰሉ የባህር በር እና ተያያዥ ጉዳይ መድረኮች የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።
" ይህን መሰል ነገር እንደማንታደም ደጋግመን እናረጋግጣለን " ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ " ሁሉም አስተዋዮች እና ተቆርቋሪዎች በዚህ እዳይቆጡ " ሲል አክለዋል።
መግለጫው በግልፅ ስለ የትኛው አካልና በየትኛው አካል ስለተነሳ ጉዳይ እንዲሁም ስለየትኛው መድረክ እንደሚያወራ ግልፅ ያለው አንዳች ነገር የለም።

በችሎት ላይ ፤ ዳኞች ፊት 7 ዓመት ሙሉ በትዳር አብራው የኖረችውን ሴት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በጩቤ ወጋግቶ የገደለው ግለሰብ " እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል " ይለናል ተከታዩ ከኢቢሲ የተገኘ መረጃ።
ወንጀሉ የተፈፀመው በቀን 21/11/2015 ዓ.ም ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ነው።
የተፈፀመበት ቦታ ደግሞ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን የበደኖ ወረዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲሆን በአቶ ደረጀ ሰይፉ እና በወ/ሮ ትዕግስት ልኬለው መካከል በፍትሐ ብሔር የተወሰነ #የፍቺ_ሂደት እና #የንብረት_ክፍፍል ውሳኔ አፈፃፀም ሂደትን ለመስማት በተጠራ ችሎት ላይ ነው።
በዕለቱ ተከሳሽ አቶ ደረጀ ሰይፉ ሆን ብሎ እና ተዘጋጅቶበት በብብቱ ስር ይዞ በገባው ጩቤ የቀድሞ ባለቤቱ የነበረችውን ትዕግስት ልኬለውን እዛው ፍርድ ቤት ደጋግሞ በመውጋት በአሰቃቂ ሁኔታ #ገድሏታል።
አቃቤ ህግ ተከሳሽ ደረጀ በባለቤቱ ላይ ከፈፀመው የግድያ ወንጀል በተጨማሪ ፦
- በወቅቱ በቁጥጥር ስር ሊያውለው የነበረን የፖሊስ አባል ለመግደል ሙከራ አድርጓል፣
- ችሎትን ተዳፍሯል፣
- የመንግስት ስራን አስተጓጉሏል የሚሉ ክሶችን መስርቶበታል።
ተከሳሽ ደረጀ ከባለቤቱ ትዕግስት ጋር ለ7 ዓመታት በትዳር የቆዩ ቢሆንም በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ፍቺ ለመፈፀም በመስማማት የንብረት ክፍፍል ውሳኔ አፈፃፀምን ለመከታተል በችሎቱ በተገኙበት ወቅት ወንጀሉ መፈፀሙን አቃቤ ህግ አስረድቷል።
ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክር እና የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርብ በታዘዘው መሰረት የመከላከያ ምስክር ማቅረብ አለመቻሉ ፤ ከ14 ዓመታ በታች የሆኑ የ4 ልጆች አባት እና አስተዳዳሪ መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ ፦
- አንደኛ ባለቤቱ ላይ በፈፀመው የግድያ ወንጀል፣
- ሁለተኛ ተከሳሽ ከዚህ ቀደም የወንጀል ሪከርድ ያለበት በመሆኑ
- ሶስተኛ ወንጀሉን የፈፀመው በችሎት ፊት በመሆኑ አቃቤ ህግ ባቀረበው የእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።
ይህንን መረጃ ከተመለከቱ በኃላ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጉዳይ አስደንጋጭ እንደሆነባቸውና ፍርዱ በቂ ነው ብለው እንደማያምኑ ሲገልጹ ተመልክተናል።
- ችሎት ውስጥ እሷ እስልትገደል (ያውም ተደጋግሞ ተወግታ እስክትገደል) ድረስ ፖሊስ ምን ይሰራ ነበር ?
- እሷን እና እሱን አንድ ላይ ካላስቀመጧቸው እንዴት ደርሶ ሊገድላት ይችላል ?
- እዛው ዳኞች ፊት የተፈፀመ ወንጀል ላይ ለመወሰን እስከዛሬ ለምን ቆየ ? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ፍትህ ካለ በዚህ ወንጀል ገዳይ ብቻ ሳይሆን ይህን መከላከል ያልቻሉ ሁሉ ሊጠየቁ ይገባል ፤ ግለሰቡ የሞት ፍርድ እንጂ እስራት አገባውም ነበር የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተው ተመልክተናል። ቅጣቱ ያበሳጫቸውም ብዙ ናቸው።

Photo
#Update
የእስራኤልና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ዛሬም መቀጠሉ ተነግሯል። ጦርነቱ ሰፍቶ ሌሎች ኃይሎችም እንዳይጨመሩ ስጋቶች ከቀን ወደ ቀን እያየሉ ነው።
ጥቂት አጭር መረጃዎች ፦
- እስራኤል የሰብዓዊ እርዳታ በግብፅ እና ጋዛ ድንበር በኩል ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዲገባ ፈቅዳለች ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ቢዘገብም የእስራኤል ጦር " የተኩስ አቁም የሚባል ነገር የለም ፤ መሻገሪያዎቹም እንደተዘጉ ናቸው ከወንጀለኛው ሃማስ ጋር መዋጋታችንን እና ማጥቃታችንን እንቀጥላለን። ጋዛ የትግላችን ማዕከል ናት የታገቱ እስራኤላውያንን ይዛለች " ብሏል።
- " ሃማስ የፍልጤምን ህዝብ አይወክልም " ያሉት የፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ " በሁለቱም በኩል በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈፀመውን ግድያ እቃወማለሁ ፤ በሁለቱም በኩል የታገቱ እና የታሰሩ እስረኞች ሊለቀቁ ይገባል " ብለዋል።
- ኢራን በጋዛ ውስጥ ላለው ጦርነት የፖለቲካ መፍትሄዎች የሚያገኝበት ጊዜ እያለቀ ነው ስትል አስጠንቅቃለች። ኢራን የጦርነቱ መስፋፋት ወደማይቀርበት ደረጃ መቃረቡን አመልክታለች።
- የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ " ግባችን ድል ማድረግና እና ሀማስን ማስወገድ ነው " ብለዋል። " ኢራንን እና ለሂዝቦላህን ተጠንቀቁ " ብለዋቸዋል። " ለቤተሰቦቻችን ግዴታ አለብን " ያሉት ኔታንያሁ " የታገቱትን ሰዎችን እስክንመልስ ድረስ አንታክትም።" ብለዋል።
- ሃማስ ያገታቸውን ሰዎች ለመልቀቅ እስራኤል ውስጥ የታሰሩ 6000 እስረኞች እንዲለቀቁ መጠየቁ ተዘግቧል። ሃማስ አሁን ላይ ከ200 - 250 የሚደርሱ ታጋቾችን መያዙን አመልክቷል። 22 የእስራኤል ታጋቾች በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል ሲል ገልጿል።
- የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ለተወሰኑ የአሜሪካ ወታደሮች እስራኤል በምትፈልጋቸው ጊዜ " ለመሰማራት ዝግጁ ሁኑ " የሚል ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፎክስ ኒውስ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው ወደ 2,000 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች ተመርጠዋል ፤ ነገር ግን ይህ ቁጥር አልተረጋገጠም ተብሏል።
ተጨማሪ መረጃዎች፦ https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
Via @BirlikEthiopia

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
ስልክዎን በመጠቀም ብቻ እንዴት የአፖሎ ዲጂታል አካውንት መክፈት እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth/1018
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #howto #howtovideo #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#ኢትዮጵያ #ቻይና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው። ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል። ከሁለትዮሽ…
#UPDATE
ቻይና የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር በመሆን ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ ፤ በኢትዮጵያ #ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩን " እንኳን ደስ ያለዎ " ብለዋቸዋል።
የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል ተብሏል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፤ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በ5ቱ ቁልፍ ምሰሶዎች፦
- በግብርና
- ማኑፋክቸሪንግ
- አይሲቲ
- ማእድን ልማት እና ቱሪዝም #ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ ያሳያል።