TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በሚከበረው የደመራ በዓል ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ መስከረም 16/2016 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የደመራ በዓል ምክንያት ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን አሳውቋል።

ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ ፦

- ከኡራዐል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ፣

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ  አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም  ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናኩ።

አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ
መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ፦
በ011-1-26-43-59 ፣ 
በ011-5-52-63-02/03፣
በ011-5-52-40-77፣
በ011-5-54-36-78 ፣
በ011-5-54-36-81 እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመሮች  987፣  991 እና 816 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
የበዓል ኬኮች እና ጣፋጭ ምግቦችን ከኢትዮጵያ ስካይላይት፣ ሃያት ሬጀንሲ፣ ሸራተን አዲስ፣ ቢሎስ ፣ ካልዲስ፣ ኮባ፣ ኮንዲቶራይ፣ጫካ፣ ሴቨር፣ ቡናሞር (ኢሊ)፣ ቤስት ዌስተርን ፕላስ፣ ማሞካቻ፣ ኦኬዥን እና ዛዮንስ እስከ መስከረም 18 ድረስ በቴሌብር ሲገዙ ለበዓል የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ ያገኛሉ!

ተስተናግደው ሲጨርሱ በአስተናጋጁ መስተንግዶ ከተደሰቱ ደግሞ ቴሌብር የቲፕ መስጫም ዝግጁ ነው።

መልካም በዓል!
#ትግራይ

" 1,329 የሚደርሱ ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን አረጋግጠናል " - መቐለ ዩኒቨርሲቲ እና የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት

በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ግጭት ካበቃበት ካለፈው የጥቅምት ወር አንስቶ ‘ቁጥራቸው 1,329 የሚደርሱ ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን አረጋግጠናል’ ሲሉ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች አስታወቁ።

የአካባቢ የጤና ባለስልጣናት እና የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ባካሄዱት በዚህ ጥናት ረሃብ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ዋነኛው የሞት መንስኤ ሆኗል ብለዋል።

ጥናት ከተደረገባቸው ውስጥ ከ68 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሰዎች በረሃብ ሳቢያ ማለፋቸውንም አመልክተዋል።

ጥናቱ የጤና ባለሙያዎች ከነሀሴ 9 እስከ ነሃሴ 23 ዓም ትግራይ ውስጥ ባሉ ዘጠኝ ወረዳዎች እና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው 53 የመጠለያ ካምፖች ቤት-ለቤት በመሄድ ያካሄዱት መሆኑም ተገልጿል።

ጥናቱ የተካሄደው በክልሉ ካሉ ወረዳዎች እና የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች አነስተኛ ቁጥር ባለው ሕዝብ ላይ በመሆኑ በክልሉ በረሃብ ሳቢያ ለሞት የተዳረገው ሕዝብ ቁጥር ከዚህም የላቀ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

ለረሃቡ መጥናት ምክንያት ከሆኑት ነገሮች አንዱ በክልሉ ለሰብአዊ ረድኤት በሚላክ የምግብ ዕርዳታ ላይ የሚፈጸመው ግዙፍ የተቀነባበረ ዘረፋ ባለፈው የመጋቢት ወር ከተደረሰበት በኋላ የአሜሪካ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰጡትን የምግብ እርዳታ ማቋረጣቸውን ተከትሎ ነው።

የዕርዳታ እህል ስርቆቱ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችም እየተፈጸመ መሆኑ መታወቁን ተከትሎም የምግብ ዕደላው ካለፈው የሰኔ ወር አንስቶ በብሔራዊ ደረጃ እንዲቋረጥ መደረጉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እገዳው እንዲነሳ የሚሻ ቢሆንም፤ የአሜሪካ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩላቸው መንግስት ከምግብ ዕርዳታ አሰጣጥ ስርዓት ተቆጣጣሪነቱ ውጭ እንዲሆን ይፈልጋሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የክልሉ አጥኒዎች ጥናት አድርገው በመዘገቧቸው በሁሉም ዓይነት መንስኤዎች ለሕልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከእርዳታው መቋረጥ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተገልጧል።

በመጋቢት ወር 159 የነበረው የሟቾች ቁጥር በሃምሌ ወር በእጥፍ ከፍ ብሎ 305 መድረሱ ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ በትግራይ በ3 ዞኖች 27 ወረዳዎች እና ከ180 በላይ ቀበሌዎች የድርቅ አደጋ እንዳጋጠመ የትግራይ እርሻ እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው  ተፈጥሮኣዊ እና ሰው-ሰራሽ በሆኑ ምክንያቶች እና የአንበጣ መንጋ ወረርሺኝ ለድርቁ መንስኤ መሆናቸውን ጠቁሟል።

አደጋው ለመቀለበስ እንደ ቢሮ የተለያዩ መፍትሄዎች እየተጠቀመ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንፃር ግን የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና የፈደራል መንግስት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብሏል።

መረጃው የድምፂው ወያነ እና አሶሼትድ ፕሬስ / ቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

በኦሮሚያ ክልል የሚዋጉ አካላት " በኢሬቻ ሥርዓት ወቅት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱ " ሲሉ አባገዳዎች ጥሪ አስተላለፉ።

አባገዳዎቹ ጥሪውን ያስተላለፉት መስከረም 26 እና 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ ሥርዓት በማስመልከት ነው ።

የጉጂ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማንኦ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ " እኛ አባገዳዎች ሥራችን ሰላም ነው፡፡ በኦሮሚያ የሚዋጉ ሁለቱም አካላት በኢሬቻ ስርዓታችንም ምንም አይነት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱብን ጠይቀናል፡፡ " ብለዋል።

" በሁሉም አቅጣጫ ያለው ኦሮሞ ሰላምና መግባባት ሰፍኖለት አንድነቱን እንዲያጠናክር እንፈልጋለን፡፡ " ያሉት አባገዳ ጂሎ " አገር ውስጥም ሆነ ከውጪም ያለው ኦሮሞ እንዲግባባ ነው የኛ መሻታችን፡፡ የሰላምና አንድነት አርማ በሆነው እሬቻ ስምም መጎዳዳቱ ቆሞ መግባባቱ እንዲሰፍን ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ በዚህ በመጪው ኢሬቻችን ኦሮሞ በሙሉ ተስማምቶ በአንድ ሃሳብ እንዲግባባ ነው ፍላጎታችን። " ሲሉ ተናግረዋል።

አባገዳ ጂሎ ማንኦ ከኦሮሞም ባሻገር በመላው አገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ወንድማማቾች መካከል ደም መፋሰሱ እንዲቀር ለማሸማገል አባገዳዎች ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

" እኛ ያላደረግነው ጥረት የለም፡፡ ከዚህ በፊት በትግራይ ጦርነት ነበር፡፡ ያንንም ለማሸማገል ከጦርነት በፊትም ሆነ ከጦርነት በኋላ ጥረናል፡፡ " ያሉ ሲሆን " አሁንም በአማራ ክልል የሚደረገውን የወንድማማች ግጭት እንዲቆም ነውና ፍላጎታችን ለሰላሙ የምንችለውን እንጥራለን፡፡ " ብለዋል።

" ተፋላሚዎች ችግራቸው ላይ እንዲነጋገሩ ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ አሁንም በሰላሙ ጥረታችን ይቀጥላል፡፡ " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" ምዕመናን ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት ይኖርባቸዋል " - ቤተክርስቲያን

በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

የደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ከቀትር ቀኋላ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ሥራው የደረሰበትን ደረጃ ተዛውረው የጎበኙ ሲሆን አጠቃላይ የዝግጅት ሥራው በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይ የክብር እንግዶች የሚቀመጡበትን የመቀመጫ  መድረክ ከነ ሙሉ የድምፅ ግብዓቱ በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ትብብር ላደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን እና ለከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።

የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓትን በተመለከተ በተዘጋጀው መርሐ ግብር መሠረት በዓሉን ለማክበር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጡ ምዕመናንም ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን የመንግሥት የጸጥታ አካላት በዓሉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር ሲባል ለሚያደርጉት ፍተሻ ፍጹም ክርስቲያናዊ የሆነ ትብብር እንዲያደርጉ ቤተክርስቲያን አሳስባለች።

በአንዳንድ የመገናኛ አውታሮች የቤተክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት የሆኑ ከበሮ፣ ጸናጽልና መቋሚያ እንዳይገባ ተከልክሏል በማለት የሚናፈሰው ወሬም ፍጹም ሐሰት መሆኑን የገለፀችው ቅድስ ቤተክርስቲያን " በዓሉን በትርኢት ለማክበር የተፈቀደላቸው ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ኤነዚሁኑ ኔዋያተ ቅድሳት ይዘው ይገኛሉ " ብላለች።

በሌላ በኩል ፤ ወደ በዓሉ ማክበሪያ በሚደረግ ጉዞ ላይ በዓደባባዩ የሚገኙ የበዓሉ ታዳሚ ምዕመናን ያለምንም መግቢያ ባጅ ተፈትሸው ብቻ ወደ ዐደባባዩ መግባት የሚችሉ ሲሆን የመግቢያ ባጅ የሚጠየቁት የክብር እንግዶች፣ ጋዜጠኞችና ልዩልዩ የሚዲያ ተቋማት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
እንኳን ለመስቀል #ደመራ በዓል አደረሳችሁ !

መልካም በዓል !

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
" የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ጊዜ አይከበርም " - በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት የላሃ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት " በላሃ ከተማ " የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ጊዜ እንደማይከበር ተገልጸ።

ይህ የተገለፀው ፤ በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት የላሃ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ባወጣው መግለጫ ነው።

በዚሁ መግለጫ ፤ " በላሃ ከተማ የመስቀል ደመራ እና የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ቦታ በኃይል ከተነጠቀበት ቀን ጀምሮ ለ6ኛ ጊዜ አይከበርም " ብሏል።

ሀገረ ስብከቱ ላለው ጥያቄ ከፌዴራል እስከ ክልል መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ቢሰጥም በጎፋ ዞን እና በመሎ ኮዛ ወረዳ እንዲሁም የላሃ ከተማ አስተዳደር አመራር ትዕዛዙን ሳይቀበሉ በመቅረታቸው ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን አሳውቋል።

በዚህም ቤተክርስቲያኒቷ ለጥያቄዋ ምላሽ ባለማግኘቷ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል ለ6ኛ ዓመት ማክበር እንደማትችል ገልጿል።

መንግሥት የቤተክርስቲያኒቷን ጥያቄ በአንክሮ ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቆ ምዕመናን በጸሎት ፈጣሪን በመጠየቅ ዕለቱን እንዲያሳልፉ  ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕመናን ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ነጫጭ ልብስ በመልበስ ወደ በመስቀል አደባባይ መገኘት ይኖርባቸዋል " - ቤተክርስቲያን በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ዝግጅቱ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳውቃለች። የደመራ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ሥራን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ…
ፎቶ ፦ የመስቀል #ደመራ_በዓል በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ ፤ ብፁዓን አባቶች ፣ ምዕመናን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ እየተከበረ የሚገኘውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚያሳዩ ፎቶዎች / ቪድዮዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ የምንስቀምጥ ይሆናል።

የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን / ቪድዮዎችን በእጅ ስልካችሁ እያነሳችሁ የምትገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት @tikvah_eth_BOT ላይ ከስማችሁ ጋር መላክ ትችላላችሁ።

Photo Credit - EOTC TV

መልካም በዓል !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! #TikvahFamily @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል አከባበር በታላቁ አንዋር መስጊድ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች።

Photo Credit - ENA / DW

@tikvahethiopia