TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹 ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የላብና ደም አሻራ ያረፈበት የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የአይን ብሌኑም ጭምር ነው። ተማሪው ፣ ሰራተኛው ፣ ወጣቱ ፣ አዛውንቱ ለዚህ ግድብ ካለው ላይ ፤ ከሚበለው ቀንሶ ሰጥቶ ያሰራው ለትውልድ የሚያወርሰው ሀብቱና ቅርሱ ነው። ይህ ግድብ ሀገር ውስጥ በየጊዜው በሚፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት ሀዘን፣ መከፋት፣ መበደል ሲመጣ እንኳን ሁሉም…
#ETHIOPIA🇪🇹

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" ሱዳን እና ግብፅ በጣም መደገፍ ያለባቸው ግድብ ነው።

ሰሞኑን በቀን እስከ 900 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ በየቀኑ ይይዛል። ምን ማለት ነው በየቀኑ አንድ አንድ ቢሊዮን ከያዘ ይሄ አጠቃላይ አቅሙ 74 ቢሊዮን ስለሆነ በ74 ቀን ውስጥ ሙሉ ግድቡን መያዝ እንችላለን።

አንዳንዴ ሽርፍራፊ ስላለ በ100 ቀን ውስጥ ይሄ ግድብ ከ0 ተነስቶ ሙሉ መሆን ይችላል ፤ ያው በ100 ቀን ያን ያህል ውሃ አይገኝም ጊዜው ስለሚወጣ ስለሚወርድ ሃሳቡን ለመጨበጥ እንዲመቸን ነው።

በ100 ቀን እንደዚህ አይነት 10 እና 15 ግድቦች ኖረውን ውሃ ብንይዝ በማንኛውም ሰዓት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ውሃ ቢያስፈልጋቸው ' ወንድሞቻችን ሆይ ለዚህ ለዚህ ጉዳይ እንደዚህ ፈልገናልና #እርዱን ' ብለው በቀላሉ መጠቀም ይችላሉ ፤ ምን ከሆነ ካለን ከያዝነው።

ዛሬ 4 ተርባይን ኢነርጂ እያመረተ ነው። ባለፈው ሁለት ነበር አሁን ሁለት ተጨምሮ እየሰራ ነው። ምናልባት በ3 ቢበዛ 4 ወር ዲሰምበር ላይ ተጨማሪ 3 ተርባይኖች ስራ ይጀምራሉ። ዲሰምበር ላይ፦
- 7 ተርባይን ኢነርጂ ያመርታል።
- በትንሹ 70 ወይም 71 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ እንይዛለን።
- አንድ የማለቅ ማይልስቶን ያሳያል።

እስከ ሚቀጥለው ክረምት ድረስ ተጨማሪ የማጥራት ስራዎች ይኖራሉ አጠቃላይ ስራው ያልቃል ተብሎ የሚታሰበው የዛሬ ዓመት ክረምቱ ካለፈ በኃላ ሊሆን ይችላል።

ዲሰምበር ላይ አለቀ ብንልም ችግር የለውም የቀረው የብሪጁ ብቻ ነው ፤ ለብሪጁ ምሰሶ ቆሟል ብረቱን እየበየዱ ማሻገር ነው የቀረው ስራ። ያ ሲያልቅ የሲቪል ስራው 100% ይደርሳል።

የኤሌክትሮ መካኒካል ፔንስቶኩ ተገጥሟል፣ ታች ያለው አብዛኛው ስራ አልቋል ፤ ጄኔሬተሩን እያመጡ የመግጠም ስራ በገባባት ጊዜ ደረጃ ስለሚሄድ በሚቀጥሉት 6 ወራት አብዛኛው ነገር መልክ እየያዘ ይሄዳል።

ህዳሴን ከሞላ ጎደል ጨርሰነዋል። ከእንግዲህ በኃላ ህዳሴ ላይ ስጋት የለንም። ፋይናሻልም ሆነ ቴክኒካሊም ስጋት የለም።

ሊያደናቅፉን የሞከሩ ኃይሎች ገድለውን ሊሆን ይችላል፣ ሰዎችን አፈነውብን ሊሆን ይችላል፣ አንዳንድ መኪና ጎድተውብን ሊሆን ይችላል ግን አላቆሙንም ስራውን ጨርሰነዋል። ያሁሉ ጉልበት፣ ያሁሉ ገንዘብ፣ ያሁሉ ድካም ከንቱ ሆነ ማለት ነው።

ያ ገንዘብ እኛን ለመደገፍ አውለውት ቢሆን ኖሮ በተሻለ ቀና ትብብር ብዙ ነገር ጥቅም ላይ ሊውል ይችል ነበር። እኛ ለማደናቀፍ ገንዘብ መውጣቱ ተጨማሪ ሃብትና ጊዜ አባከኑ እንጂ አጠቃላይ ስራው እንዲቆም አላደረገውም።  "

https://youtu.be/8R7B3qPEB9U?feature=shared

#ETHIOPIA
#GERD🇪🇹

@tikvahethiopia