TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ። የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ። በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር…
#ኢትዮጵያ

መንግሥት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ የነእፓ ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም አዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ጠይቀዋል።

" ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር " በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ መንግስት በሆደ ሰፊነት ዳግም የሰላም እጁን በመዘርጋት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ " ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላው ሊቀመንበሩ ህዝብን እየፈተነ ላለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መንግሥት መፍትሄ እንዲያበጅ ጠየቀዋል።

" የዜጎቻችንን ህይወት እጅግ ከባድ ያደረገው የኑሮ ውድነት ቀንሶ፣ ዜጎች ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ተሟልተው መኖር ይችሉ ዘንድ፦
- የመንግስት የወጪ ቅደም ተከተል የሀገርን እና የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች ያማከሉ እንዲሆን፤
- የመንግስት የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲዎች የዜጎችን የኑሮ ሸክም ለማቅለል በሚያስችል መልኩ እንዲከለሱ " ጥያቄ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ሊቀመንበሩ በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች " መንግስታዊ ይቅርታ " እንዲደረግ ጠይቀዋል።

" ሀገር የሚቆመው በመተዛዘን፣ በፍቅር እና በይቅርታ ነው። " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር ፤ " በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች መንግስታዊ ይቅርታ በማድረግ፣ እጅግ የተካረረው የሀገራችን ፖለቲካ እንዲረግብ፣ ህዝባችንም የእርቅ እና የሰላም አየር እንዲተነፍስ መንግስት የይቅርታ እጁን እንዲዘረጋ " ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሀገር እና ህዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት በመካድ እና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ፣ በብልሹ አሰራር በዜጎች ላይ የከፋ አስተዳደራዊ በደል በሚፈጽሙ፣ የሀገርን ሀብት እና ንብረት በሚመዘብሩ፣ #የመንግስት_ሹመኞች እና ግበረ አበሮቻቸው ላይ ስር ነቀል እና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ሀገርን እና ዜጎችን እንዲታደጉ ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia