TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከ5 ብር ጀምሮ ስንሞላ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ዕለታዊ እና ሳምንታዊ ጥሪ ማድረግ እንችላለን። ያለሃሳብ ከምንወዳቸው ጋር አብሮነታችንን እናጠንክር!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
" አርሶ አደሩ መሬት የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው " ለማድረግ ማቀዱን ትንሣኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ገለጸ።

የምሥረታ ጉባኤውን ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ  በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄደው የ " ትንሣኤ 70 እንደርታ " ፓርቲ (ትሰእፓ) ሊቀ መንበር ሆነው የተሾሙት አቶ ከበደ አሰፋ ፤ " አርሶ አደሩ መሬቱን የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው ይደረጋል " ብለዋል።

ሊቀ መንበሩ፤ "መሬት የሕዝብ እንጂ የመንግሥት መሆን የለበትም " ያሉ ሲሆን፣ ትሰእፓ " በመሆኑም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሀብት በወጉና በሥርዓቱ እንዲሁም ሕዝብንና አገርን ጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፓሊሲ ያዘጋጃል " ሲሉ አስረድተዋል።

አቶ ከበደ አክለውም፣ "መንግሥት አርሶ አደሩን የማይረባ ዋጋ እየሰጠ በማፈናቀል፣ መንግሥት ራሱ መሬቱን በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ የሚነግድበት ሥርዓት መወገድ አለበት" ብለዋል።

" እስከ  ዛሬ ድረስ 'መሬት የሕዝብም የመንግሥትም ነው' ተብሎ ግን መንግሥት በካሬ 40 ሺህ እና 50 ሺህ በሊዝ ስም የሚሽጥበት እውነታ ስለሆነ ያለው፣ መሸጥም ካለበት መንግሥት ሳይሆን ራሱ ሕብረተሰቡ ይሽጠው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፓርቲው በተጨማሪም፣ "ታላላቅ ኢንዱስትሪዎች ሲቋቋሙ አገሬውን ተጠቃሚ በሚያደርግና በማያፈናቅል መንገድ፣ ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሰፋፊ መሬቶች አርሶ አደሩን በማማከር እና የልማቱን ባለድርሻ በማድረግ ይከናወናል " ብሏል።

በምስረታ ጉባኤው የታደሙ የፓርቲው ደጋፊዎች በበኩላቸው የፓርቲውን የእንደርታ ሕዝብ በሕወሓት አመራሮች ጫና፣ መገለል እንደተፈጸመበት በምሬት ተናግረዋል።

አክለውም ትሰእፓ ከሕወሓት ጋር ምንም አይነት ቁርኝት እንዳይኖረው ጠይቀዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ከበደ በበኩላቸው ፓርቲው ከሕወሓት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደማይችል አስረድተዋል።

ትሰእፓ የምስረታ ጉባኤውን ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን፣ በጉባኤው የተሳተፉ አባላቱ የማዕከላዊ ኮሚቴዎች፣ የኦዲትና ሥራ አስፈጻሚዎችን መርጠዋል።

አቶ ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " 15 የማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ሦስት የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ተመርጠዋል። እኔ አቶ ከበደ አሰፋ ሊቀመንበር ሆኘ ተመርጫለሁ " ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም 15ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶችም ባከናወኑት ምርጫ 14 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቶችን መርጠዋል፤ አቶ ጊደና መድህን ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል" ብለዋል።

ትሰእፓ በትግራይ ክልል “የተንሰራፋውን ጭቆና እና የአንድ ፓርቲ ስርዓት” መታገል ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታውቋል።

መረጃውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#5G_AddisAbaba

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሩን ዛሬ ቅዳሜ ጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓታት በኋላ በይፋ ያበስራል፡፡

በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖረናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#5G_AddisAbaba ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ መጀመሩን ዛሬ ቅዳሜ ጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓታት በኋላ በይፋ ያበስራል፡፡ በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ይኖረናል። @tikvahethiopia
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር። በቀጣይም በሙከራ ደረጃ በአዳማ ከተማ አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ተደራሽነቱን አስፍቶ ለተጠቃሚዎች መቅረቡን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በነበረው ይፋዊ የማብሰሪያ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ በኢትዮጵያ ይህንን አገልግሎት በአዲስ አበባ 145 ሳይቶች ላይ የ5G ኔትዎርክ ማስፋፊያ የተደረገ ሲሆን 630 ሺ ደንበኞቹ ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ቀፎ (Device) መኖሩን አስታውቀዋል።

ይህ አገልግሎት ከተዘረጋባቸው ቦታዎች መካከል ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ኤርፖርት፤ ከመስቀል አደባባይ መገናኛ CMC እንዲሁም ወደ ሰሚት የሚወስደው መንገድ፤ ከመስቀል አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ድረስ፤ ከመስቀል አደባባይ ሜክሲኮ ሳር ቤት እንዲሁም ልደታ ከመስቀል አደባባይ ለገሀር ቸርቸል ጎዳና ይህ መሰረተ ልማት የተዘረጋላቸው አከባቢዎች ናቸው ተብሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው ተቋሙ በቀን በአማካይ ወደ 2,087 GB የዳታ ትራፊክ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የ4G አገልግሎቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል።

በአለማችን ወደ 110  ሀገረት በአፍሪካ ደግሞ 16 ሀገራት ይህንን አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ 1.3 ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን የ5G ኔትዎርክ ተጠቃሚ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል። ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ…
የ5G ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ዋጋ ስንት ነው ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 81.8 ሚሊዮን ከኔትዎርክ የተገናኙ መሳሪያዎች መኖራቸውን ያሳወቀ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 42 በመቶ የሚሆነው ስማርት ስልኮች (Smart Phones) መሆናቸውን ገልጿል።

በተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ 34.4 ሚሊዮን ሰዎች የኢንተርኔት ዳታ ተጠቃሚ ናቸው ያለው ተቋሙ፥ እነዚህ ደንበኞቹ በአማካይ በቀን 2,087 GB ዳታ ዝውውር (Average Daily data traffic) የሚፈጽሙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የ4G ተጠቃሚዎቹ 66 በመቶ የሚሆነውን እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

አዲሱ የኢትዮ ቴሌኮም የ5G ኔትዎርክ በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰነ ክልል ለተጠቃሚዎች የቀረበ ሲሆን የራሱ የክፍያ ፖኬጆችም ተዘጋጅተውለታል።

ይህ የክፍያ ፖኬጅ ከዚህ በፊት ከነበሩት የኔትወርክ አገልግሎቶች (4G, 3G, 2G) የዋጋ #ጭማሪ ያለው ነው።

በዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ወርኃዊ ያልተገደበ የ5G አገልግሎቱን በ1,199 ብር እና በ300 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) እንዲሁም ፕሪሚየም የተሰኘውን ወርኃዊ ያልተገደበ ጥቅሉን በ1,299 ብር በ400 GB ፍትሃዊ የአጠቃቀም ፖሊሲ ባለው (FUP) ለተጠቃሚዎች አድርሷል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ያልተገደበ 150 GB የ5G ኢንተርኔት በ929 ብር እንዲሁም 250 GB ደግሞ 979 በር ለተጠቃሚዎች አቅርቧል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም በነበረው ኔትዎርክ ወርኃዊ ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት በ999 ብር ለተጠቃሚዎች እንደሚያቀርብ ይታወሳል።

የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት ለመጠቀም ምን ላድርግ ?

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ 5G ኔትዎርክ መቀበል የሚችሉ መሳሪያዎችን የያዙ ደንበኞችን ልየታ አጠናቆ ወደ ኔቶርኩ እያስገባ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጸ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት ይህ ሥራ እንደሚጠናቀቅም አሳውቋል።

በመሆኑም ደንበኞች ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት ሳይሄዱ አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጹሑፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል ተብሏል።

ደንበኞች በራሳቸው ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም መጀመሪያ የያዙት ስልክ ወይም ኢንተርኔት ማስጠቀም የሚችል ቁስ (Device) የ5G ኔትዎርክ መቀበል እንደሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ።

NB : የፍትሃዊ አጠቃቀም ፖሊሲ (FUP) ማለት ኢንተርኔት አቅራቢዎች ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን አላግባብ የመጠቀምን ወይም የመተላለፊያ ይዘትን (Bandwidth) ከመጠን በላይ መጠቀምን ለመከላከል የሚያስችላቸውና ፍጥነትን የሚቀንሱበት አሰራር ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ይህንን ፖሊሲ ከዚህ ቀደም የሰዓት እና የቀን ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ አድርጓል።

ፎቶ 1 ፦ ለተጠቃሚዎች የቀረበውን የዳታ ጥቅል የሚያሳይ

ፎቶ 2፦ የ5G አገልግሎት የተዘረጋባቸው አከባቢዎች የሚያሳይ

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#ሞሮኮ

እጅግ አስደንጋጭ ነው በተባለው የሞሮኮ መሬት መንቀጥቀጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሞቱ።

በሞሮኮ በመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን  ባለው 1,305 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ቢቢሲ ኒውስ ፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የተከሰተው 6.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚህም እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በዋነኛነት የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው በአትላስ ተራራ አካባቢ ነው ተብሏል።

ይህም ከማራኬሽ በደቡብ ምዕራብ 71 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። ጥልቀቱም 18.5 ኪሎ ሜትር ነው። በማራኬሽና በሌሎችም ደቡባዊ አካባቢዎች ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።

አል-ሀውዝ፣ ማራኬሽ፣ ኦራዛቴ፣ አዚል፣ ክሪቾዋ እና ታራውዳንት በተባሉት አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ሕንጻዎችና ጎዳናዎች ሲናዱ ታይተዋል።

ሞሮኮ በደረሰው አደጋ የ3 ቀን ሀዘን አውጃለች።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ መሪን ጨምሮ የሀገራትና ተቋማት መሪዎች ሀዘናቸውን እና ለሞሮኮ ህዝብ ያላቸውን አጋርነት እየገለፁ ይገኛሉ።

NB. የሟቾች ቁጥር አሁን ካለውም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#CBE

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቸሁ!
===========

የበዓል ሸመታዎን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ POS ማሽኖች ይፈፅሙ!

መልካም በአል ይሁንላችሁ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#commercialbankofethiopia #digitalbanking #Ethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#GERD🇪🇹

" በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

ኢትዮጵያ ዛሬ 4ኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ (የአባይ ግድብ) የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ አብስራለች።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይኸኛው 4ኛ ዙር ሙሌት የመጨረሻው ስለመሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሙሌቱ በስኬት በመጠናቀቁ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ፣ በጉልበታቸው ፣ በፀሎታቸው በስራው ለተሳተፉ ምስጋና አቅርበው " እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

ለኢዜአ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዳግሞ ፤ ባለፉት 4 ዓመታት የውሃ ሙሌት ስራውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ የዝናብ መጠን መገኘቱን አስረድተዋል።

የውሃ ሙሌት ስራው በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት በማያደርስ መልኩ መከናወኑን ገልጸዋል።

ለአብነትም በዘንድሮው ክረምት በግብጽ የሚገኘው የአሰዋን ግድብ ከበቂ በላይ ውሃ በመያዙ ምክንያት በግድቡ ማስተንፈሻ አማካኝነት ውሃ የማፋሰስ ስራ ሲያከናወን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስቱ አገራት የትብብር ምንጭ ከመሆን ባሻገር በታችኛው ተፋሰስ አገራት የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ በተግባር ያመላከተ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

አሁን ላይ ኃይል ማመንጨት የጀመሩት ሁለቱ ተርባይኖች በስራ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ እንደሚገቡ አሳውቀዋል።

4ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ በግድቡ ግንባታ ሂደት ሌላኛውን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ የሚኖሩት ስራዎች ከዚህ ቀደም ከተለፈባቸው የተሻሉ እንደሚሆኑ የጠቀሱት ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ ፤ " ይህ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ስኬት ነው " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia