TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BekeleGerba #USA🇺🇸

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር #ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።

አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም "  በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

More - https://telegra.ph/BBC-08-28-2

@tikvahethiopia
Jasiri is a regional hub, dedicated to driving development in the wider East African area.

We carefully select candidates from Ethiopia, Rwanda, and Kenya to take part in our programs, which are designed to make a meaningful contribution to the African Union's vision of a progressive, dynamic, and united Africa.

Application to join our Cohort 5 is ongoing, apply today at https://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
በኮፔይ ኢብር ይክፈሉ!
የነዳጅ ክፍያዎን
ቀላል እና ፈጣን ያድርጉ!
@coopbankoromia
" ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቼ ጥራት ያለውን ትምህርት እንድሰጥ እውቅና አግኝቻለሁ " - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ግንባር ቀደሙ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው ዓመት ከዚህ ቀደም ይሰጥ የነበረውን የማህበረሰብ አገልግሎት አድማስ እንደሚያሰፋ ዛሬ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በትምህርት ኮሌጁ አስተባባሪነት ከKG-12 ክፍል የያዘ ሞዴል ትምህርት ቤት ከፍቶ ጥራት ያለውን ትምህርት ለመስጠት ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ት/ቢሮ እውቅና ማግኘቱን አሳውቋል።

በ2016 ዓ.ም. የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፀው ተቋሙ የመመዝገቢያ ጊዜና መስፈርቶቹን በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ስለሚደረግ የተወሰኑ መንገዶች ይዘጋሉ ብሏል።

ቡድኑ ነገ ነሀሴ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ እስከሚያርፉበት ሂልተን ሆቴል ድረስ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግለት ተገልጿል።

በዚህም ነገ ከጠዋቱ 1፡00 ሠዓት ጀምሮ፡-

👉 ከኤርፖርት በቅዱስ እስጢፋኖስ ወደ አራት ኪሎ

👉 ከራስ መኮንን ድልድይ በደጎል አደባባይ ወደ ቸርችል ጎዳና

👉 ከድላችን ሀውልት በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ከዚያም በሚያርፉበት ሂልተን ሆቴል አካባቢ ለተወሰነ ሰዓት መንገዱ ይዘጋል ተብሏል።

አሽከርካሪዎች ይህን በመገንዘብ በቦታው የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላትን መረጃ በመጠየቅና ተባባሪ በመሆን  ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒና ውድድር ላይ የተካፈለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን ከዓለም 6ኛ ከአፍሪካ ከኬንያ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የዓረና ሊቀመንበር ሆኑ።

የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ (ዓረና) ባካሄደው  5ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴን ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

አቶ ካሕሳይ ዘገየ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሁነው እንዲያገለግሉ መመረጣቸው ተነግሯል።

Via Abrha Desta

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ለምን ተቋረጠ ? የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 /2015 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ መቋረጡ ተገልጿል። ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሰረት አገልግሎቱ የተቋረጠው በመኾኒ ባጋጠመ የመስመር መቋረጥ ነው። ችግሩን ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ለመፍታት አስቀደመው ወደ ተላኩ ባለሙያዎች ተጨማሪ የሰው ኃይል መላኩን…
#Update

መቐለ ጨምሮ በመላ ትግራይ ከነሃሴ 21 ሌሊት ጀምሮ  የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል።

በመቐለ ከተማ ዛሬ ነሃሴ 22/ 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መሰጠት ጀምሮ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ከፊሉ የከተማው አከባቢ ጠፍቶ ከፊሉ አገልግሎቱ በማግኘት ላይ መሆኑ የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ መረጃ አድርሶናል።

የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ የተቋረጠው መኾኒ ላይ ባጋጠመ የመስመር ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ ማሳወቁ ይታወቃል።

ችግሩን ለመፍታት ርብርብር እየተደረገ እንደሆነ ተነግሯል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ነው በሚል በአዋጁ የተቀመጡ ዝርዝር መስፈርቶችን ማለትም ፦
- 3ኛ ወገን፣
- መድን ሽፋን ሰሌዳ፣
- ለተሽከርካሪው የሚመጥን መንጃ ፍቃድና
- ሌሎች በተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 681/2002 የተዘረዘሩ አስፈላጊ መረጃዎች ሳያሟሉና የቴክኒክ ብቃታቸው ሳይረጋገጥ በከተማዋ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል።

ከዛሬ ጀምሮ ግን በከተማዋ ያሉ የኤሌክተሪክ ሞተር ሳይክሎች በተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያና መመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 681/2002 ላይ በተቀመጠው መሰረት በሰዓት ከ20 ኪ.ሜ በላይ የሚንቀሳቀሱ ማንኛውም ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎች ላይ ይህንን አሰራር እንዲተገብሩ ሲል ቢሮው አሳስቧል።

ይህንን በማይፈፅሙና መስፈርቱን ሳያሟሉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች ላይ ቢሮው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑሮውን አልቻለነውም " እጅግ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በየአካባቢያቸው የዳቦና የእንጀራ ዋጋ አሁን ላይ የደረሰበትን ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች አንድ ትንሽ ተብሎ የሚታሰበው ዳቦ ከ5 ብር - 9 ብር ድረስ እንደየአካባቢው የሚሸጥ ሲሆን እንጀራ ከ15-20 ብር ድረስ ይሸጣል ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው ቀጠናዎች ዋጋው እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻችን…
#ኢትዮጵያ

ዛሬ ጥዋት ከ #ዳቦ እና #እንጀራ ዋጋ በየጊዜው መጨመር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በአጠቃላይ የኑሮው ሁኔታ ምን ያህል እየከበደ እንደሄደ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ሃሳብ ሲያጋሩ ነበር።

ከእነዚህም ቤተሰቦች መካከል በጤና ባለሞያነት የምታገለግል የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እኔ የምናገርበትን አጥቻለሁ ፤ የቲክቫህ ቤተሰቦች እየገፋው ያለሁትን ኑሮ ይስሙኝ ስትል መልዕክቷን እንዲህ ስትል ልካለች።

የጤና ባለሞያዋ የቲክቫህ አባል ፦

" እውነቱን ለመናገር ኑሮ ጫናዉ እኛ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እጅጉን ብሷል።

ለምሳሌ ፦ እኔ በአንድ ትልቅ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እሰራሁ ደሞዜ 6193 ብር  የግብር ተቀንሶበት 4776 ብር ይደሳል።

Duty ተብሎ ሌሊቱን ሙሉ ከፅኑ ታካሚ ጋር ስለፋ አድሬ ጠዋት የታካሚውን የአዳር ሁኔታ የሚረከበኝ የቀን ተረኛ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አስረድቼና አስረክቤ ፤ ታዲያ የአደሩን ነገር አትጠይቁኝ መድሀኒት መስጠቱ ፣ በየ1 ሰዓቱ Vital ማንሳቱ ዳይፐር አንሶላ እንዲሁም ቁስል ማጠቡ እሄን ሁሉ አስረክቤ በከተማ አውቶብስ ድፍን ሁለት ሰዓት ወደሚፈጀው የተከራየሁት ቤት እጓዛለሁ።

የምስራበት አካባቢ ላይ እንዳልከራይ የደመወዜን እጥፍ ከየት አምጥቼ እከፍላለሁ ፤ ለዚህ ነው ከከተማ ወጥቼ የተከራየሁት እናማ ከመድከሜ የተነሳ አውቶብስ ላይ ማንቀላፉቱ የማይቀር ነው ፤ ቤት እደርስና የሚበላ ስለማይኖር ከምስራ ብተኛ ብዬ እተኛለሁ። 

እደዛ ወገቤ ተሰብሮ ዝዬ ፤ ሌላ ተጨማሪ ስራ እንዳልሰራ ደካክሜ ብቻ ምን አለፋችሁ ፤ ለዚህ ሁሉ ድካም ያቺ ደሞዝ ናት ያለችኝ  የDuty ክፍያ ተጨምራ እጄ ላይ የምትደርሰውን ብር ለቤት ክራይ ከፍዬ፣  የትራንስፖርት እና አስቤዛ አውጥቼ የት ትድረስና ? የኑሮው ጫና እኛ ላይ የባሰ ነው። "
.
.

ዛሬ አስተያየታቸውን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የላኩ ዜጎች በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተፈተኑ መሆኑን በመግለፅ ፤ ገበያው በየጊዜው እየናረ ከዘላቂ መፍትሄ ይልቅ ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ እያለፈ ነው ብለዋል።

ሚዲያዎችም ትኩረት የሚስብላቸው እና ገንዘብ የሚሰሩበት የፖለቲካ ፍጅትና ጦርነት ፣ ግጭት ስለሆነ ዜጎች እየተፈተኑበት ስላለው የኑሮ ውድነት ጉዳይ አድምተው ለመስራትና የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ እንዲሁም መፍትሄ እንዲሰጥ ለመጋፈጥ ፍላጎት የላቸውም በማለት ወቅሰዋል።

ከድሃ ጎሮሮ ላይ እየነጠቁ የሚበለፅጉ አካላትም ፣ የራሳቸውን የኑሮ ምቾት ብቻ እያሰቡ የሚሯሯጡ ነጋዴዎችም ለአፍታ ለታችኛውና ኑሮ እየፈተነው ላለው ማህበረሰብ እንዲያስቡ ጠየቀዋል።

መንግሥትም ጆሮ ሰጥቶ የሚሰማ ከሆነ ዜጎች በኑሮ ውድነት በተለይም ደግሞ በምግብ ነክ ነገሮች ላይ በየጊዜው በሚደረገው ጭማሪ ዜጎች እየተሰቃዩነውና መፍትሄ ይፈልግ ብለዋል።

Via @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia
Jasiri is a regional hub, dedicated to driving development in the wider East African area.

We carefully select candidates from Ethiopia, Rwanda, and Kenya to take part in our programs, which are designed to make a meaningful contribution to the African Union's vision of a progressive, dynamic, and united Africa.

Application to join our Cohort 5 is ongoing, apply today at https://jasiri.org/application

#Jasiri4Africa
ወደ *777# በመደወል የሳፋሪኮምን ዕለታዊ የዩቲዩብ ጥቅሎች እንግዛ ፣ አዳዲስ ዕውቀቶችን እንቅሰም!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
ብቋንቋ ትግርኛ ሓበሬታታት : ጥቆማን ሓሳባትን ንለዋወጠሉ መድረኽ ተኸፊቱ ኣሎ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ / ትግርኛ https://t.iss.one/TikvahEthiopiaTigrigna

ምክትታልኩምን ሓበሬታኹምን ኣይፈለየና።