TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። ጀግናዋ አትሌት አማኔ በሪሶ #ወርቅ ፤ ጀግናዋ አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር ለሀገራቸው አስገኝተዋል። ከውድድሩ መጠናቀቅ በኃላ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የተወሰዱ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ። https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x ፎቶ፦ Tikvah Ethiopia Sport (Hungary , Budapest)…
#ኢትዮጵያ
" ሶስቱንም ሜዳሊያ ለማሸነፍ ነበር የፈለግነው " - አትሌት አማኔ በሪሶ
በሴቶች ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ ያስመዘገበችው አትሌት አማኔ በሪሶ በውድድሩ ወቅት የተሰራው የቡድን ስራ ድንቅ መሆኑን ተናግራለች።
" ዛሬ እንደ ቡድን የሰራነው ድንቅ ስራ ነው " ያለችው አማኔ በሪሶ " በጋራ ከሰራን እንደምናሸንፍ እናውቅ ነበር የመሪዎቹን ቡድን ወደ ስድስት ዝቅ አድርገን በመቀጠልም በዕቅዳችን መሰረት አራታችን ብቻ መውጣት ችለናል" ብላለች።
" ሌሎቹን አትሌቶች ከፉክክር ውጪ ካደረግን በኋላ ከጠንካሮቹ የሀገሬ ልጆች ጋር እርስበርስ ነው የተፎካከርነው ጎተይቶም ጠንካራ አትሌት ነች ሻምፒዮንነቷን ማስጠበቅ ፈልጋ ነበር " ስትል ገልጻለች።
" እንደ ቡድን ሶስቱንም ሜዳልያ ለማሸነፍ ነበር የፈለግነው ነገር ግን በመጨረሻ እንደ እቅዳችን አልሄደልንም ፣ ቢሆንም ባገኘነው ድል እጅግ ደስተኞች ነን ሙቀት እንደሚኖር እናውቅ ነበር ነገር ግን እኔን ሙቀቱ ብዙም አልከበደኝም " ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች።
🇪🇹
አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ምን አለች ?
የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ ኢትዮጵያ ያስገኘችው አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ፤ " ዋናው ግባችን ወርቁን ወደ ሀገራችን ይዞ መሄድ ነበር። " ብላለች።
አትሌቷ ፤ " እኛ ኢትዮጵያውያን አሸናፊነታችንን በማስቀጠላችን እኮራለሁ። " ስትል ገልጻለች።
" በአማኔ ብሪሶ ኮርቻለሁ ፤ እንዲሁም በግሌ በዓለም ሻምፒዮናው ሌላ ሜዳሊያ በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ " ብላለች።
" ባለፈው ዓመት በኦሪገን እና ዘንድሮ በቡዳፔስት መካከል ያለው ዋና ልዩነት የአየር ሁኔታ ነው " ያለችው አትሌቷ ፤ ኦሪገን በጣም ቀዝቃዛ ነበር፣ ቡዳፔስት ዳግሞ በጣም ሞቃት ነው ሁኔታው ሊከብድ እንደሚችል ቀድመን አውቀን ነበር ፤ ምንም ይሁን ግን የዓለም ሻምፒዮና ነው በዙ ፈተናዎች የተሞላ ነው ፤ ለዚህ በቂ የሆነ ዝግጅት አድርገን ነው የመጣነው ስልት ተናግራለች።
ቀጣይ ግባችን ለኦሎምፒክ ማለፍ ነው ስትልም አክላለች።
🇪🇹
" አትሌቶቻችን ደም ነው የሰጡት " ረ/ ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
ኢትዮጵያ በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ እና ብር ሜዳልያዎችን ማስመዝገቧ የተጠበቀ ውጤት እንደነበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለልዩ ስፖርት ተናግራለች።
" እኔ በጣም ደስ ብሎኛል ፈጣሪ ይመስገን እናንተም እንኳን ደስ አላችሁ ሁላችሁም " ስትል መልዕክት ያስተላለፈችው ደራርቱ ቱሉ " የተመዘገበው የጠበቅነው ውጤት ነው" ብላለች።
" የአየር ሁኔታው አትሌቶቻችን ላይ ተፅዕኖ ባያደርግ ከአንድ እስከ ሶስት ይወጡ ነበር ፀሀይ ገመቹም ከድል ያልተናነሰ የቡድን ስራ ሰርታለች ሁሉንም እናመሰግናለን፤ ዛሬ ደም ነው የሰጡት " ስትል ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ ተናግራለች።
በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ክፍል የተነሱ ተጨማሪ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopia

#Mekelle በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ትላንት ለሊት " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ለጉዳት የዳረገው ተጠርጣሪ ግለሰብ ስሙ ሙሉጌታ እንደሚባል ታውቋል። ፖሊስ ግለሰቡ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና " በቁጥጥር ስር ለማዋል " ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጾ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል። ተጠርጣሪው በመቐለ…
#Update
በመቐለ ከተማ ቀዳማይ ወያነ ክ/ከተማ በሚገኝ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት ያጠፋውና ጉዳት ያደረሰው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።
የቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል በቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ጣብያ በአካል ሄዶ እንዳረጋገጠው ተጠራርጣሪው ሙሉጌታ ካልኣዩ ዛሬ በህዝብና ፓሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።
የፓሊስ ጣብያው አዛዥ ህዝብ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
በመቐለ ከተማ ቀዳማይ ወያነ ክ/ከተማ በሚገኝ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት ያጠፋውና ጉዳት ያደረሰው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ።
የቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ አባል በቀዳማይ ወያነ ፓሊስ ጣብያ በአካል ሄዶ እንዳረጋገጠው ተጠራርጣሪው ሙሉጌታ ካልኣዩ ዛሬ በህዝብና ፓሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።
የፓሊስ ጣብያው አዛዥ ህዝብ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በዛሬው ዕለት በሴቶች የማራቶን ውድድር #የወርቅ እና #የብር ሜዳልያዎችን ለሀገራቸው ኢትዮጵያ ያመጡት አትሌት አማኔ በሪሶ እና አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ ሜዳልያቸውን ተረክበዋል።
Via @tikvahethsport (ሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት)
@tikvahethiopia
Via @tikvahethsport (ሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት)
@tikvahethiopia
በሻራ የሆነው ምንድነው ? ነዋሪዎች ምን አሉ ? መንግሥትስ ምን አለ ?
በጋሞ ዞን አርባምጭ ዙርያ ወረዳ፣ ሻራ ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት ከትናንት ጀምሮ 18 ሰዎች መገደላቸውን እና 20 ሰዎች መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
የጋሞ ዞን የፀጥታ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ ፤ ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ለማፍረስና የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ የታጠቀውን ኃይል በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲባል በተወሰደው እርምጃ "መጠነኛ" ያለው የሰው ህይወት ማለፉንና ንብረት መውደሙን አስታውቋል።
የአከባባው ነዋሪዎች ግን መንግሥት ራሱ አሰልጥኖ መሳሪያ የሰጣቸው የቀበሌ ታጣቂዎች እንጂ ሌላ የታጠቀ ቡድን የለም ብለዋል።
የግጭቱ መንስኤ የሻራ ቀበሌን ከአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ተነጥሎ ወደ አርባምንጭ ከተማ እንዲካለል በመወሰኑ ነው ሲሉ አንድ የዓይን እማኝና የዛው የቀበሌው ነዋሪ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
እኚኹ አስተያየት ሰጪ ውሳኔው ከተላለፈ በኋላ በተፈጠረው አለመግባባት ቀበሌው ለወራት ከመንግሥታዊ አገልግሎት ውጭ ኾኖ መቆየቱንም ገልፀዋል።
የሰው ህይወት ወደጠፋበት ግጭት ያመራው ግን ቀበሌውን ወደ ስራ ለማስገባት የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር እና የአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ የፀጥታ ሃይሎች ወደ ቀበሌው በመግባታቸው እና የሻራ ቀበሌ ሚሊሻዎች፣ ወጣቶች እና የቀበሌው ነዋሪዎች ጋር ምክክር አድርገው በመተማመን ላይ ሳይደረስ በመቅረቱ ነው ብለዋል።
ነዋሪው " የኛ ቀበሌ ወደ አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አይካለልም " ማለቱንም አመልክተዋል።
ማንነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሆስፒታል ሐኪም ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ 12 ሰዎች በጦር መሳሪያ መገደላቸውን እና በልዩ ልዩ አካላቸው ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው የመጡ 15 ቁስለኞች እየታከሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምን አሉ ?
አንድ ስለጉዳዩ እንደሚያውቁ የገለፁ በአርባምጭ የሚኖሩ ነዋሪ ፤ ከትላንት በስቲያ አመሻሽ ጀምሮ የቀበሌው ነዋሪ በተለይ ወጣቶች ከመንግስት አካላት ጋር ከባድ ሰጣ ገባ ዉስጥ ገብተው እንደነበርና ብዙ ወጣቶችም በጥይት መመታታቸውን አስረድተዋል።
እኚሁ ነዋሪ ትላንት መንገድ ዘግ እንደነበር ፤ አምቡላንስ ወደ ከተማው ሆስፒታል ሲመላለሱ እንደዋሉ ጠቁመዋል።
ሌላ ነዋሪ ደግሞ ፤ በመንግስት ፀጥታ አካላት በተወሰደ እርምጃ ከአሥር በላይ ሰዎች ሞተዋል ሌሎች ደግሞ በካድ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት አስተናግደዋል ሲሉ ገልጸዋል።
እንደምክንያት የሚያነሳው ሻራን ወደከተማ ይዞታ ለማካለል የተወሰነ ውሳኔ ነው ብለዋል።
" ከሕዝቡ ጋር፣ ከአባቶች ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በመምከር፣ በመወያየት እንጂ ከቶ ሰው በመግደል የሚመጣ ለውጥ እና ዕድገት የለም " ሲሉ አክለዋል።
የዞኑ የፀጥታ ግብረ ኃይል ግን በሻራ ጫኖ ቀበሌ ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እና የአካባቢውን ሰላም እና ፀጥታ ለማደፍረስ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል።
ግብረኃይሉ የታጠቁት ኃይሎች ማንነታቸው የማይታወቅ ፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያ የታጠቁ፣ ድብቅ አላማ ያላቸው፣ በድብቕ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የከረሙ ናቸው ብሏል።
ይህ ህገወጥ የታጠቀ ቡድን የቀበሌ አስተዳደርን ለወራት ያህል ተቆጣጥሮ ቆይቷል ያለ ሲሆን በተካሄደው ኦፕሬሽን ትጥቅ የማስፈታት ስራ ተሰርቷል። ይኸው ቡድን በተከፈተው የተኩስ ልውውጥ " መጠነኛ ጉዳት ደርሷል " ብሏል።

እጅግ ተጠባቂው የ5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ተጀመረ።
ሀገራችን #ኢትዮጵያ በውድድሩ ፦
- በጉዳፍ ፀጋይ፣
- በእጅጋየሁ ታዬ፣
- በመዲና ኢሳ፣
- በፍሬወይኒ ኃይሉ ተወክላለች።
በዚሁ ፤ የ5000 ሜትር ውድድር ላይ የኔዘርላንዷ ሯጭ ሲፋን ሀሰን ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።
ድል ለሀገራችን አትሌቶች !