TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#udate ኦፌኮ እና ሰማያዊ ፓርቲ⬇️

ሰሞኑን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በአርማ እየተመካኘ እየተፈጠረ ያለው አምባጓሮ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖው ወደ ሁከትና ብጥብጥ ከማምራቱ በፊት መንግሥት #አፋጣኝ #እርምጃ እንዲወስድ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ።

ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ "ትናንት አስከፊውን አገዛዝ ከጫንቃችን አሽቀንጥረን ለመጣል ያደረግነው ብርቱ ተጋድሎ በጎመራ ማግሥት የለውጡን ሂደት መደገፍና አገሪቱን እንደ አገር የማስቀጠሉ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ሲገባ በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ የሚታዩት ግጭቶችና ሥርዓት አልበኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በተለይ ሰሞኑን በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ከሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው እሰጣገባ በብርቱ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። ቢዚህም ሳቢያ በተፈጠረ ፉክክር "ትውልዱን ለግጭት ማነሳሳት ፍፁም ሊወገዝ የሚገባው እኩይ ተግባር ነው" ሲሉ አውግዘዋል።

ኦፌኮና ሰማያዊ በመግለጫቸው ላይ ጨምረውም "እያንዳንዳችን ፍላጎታችንንና ድጋፋችንን ለምንሻው አካል እየሰጠን አንዳችን የአንዳችንን ሃሳብም ሆነ መልካም ድርጊትን እያከበርን የተጀመረውን ለውጥና ሽግግር መደገፍ ወሳኝ ነው" ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በአርማ እየተመካኘ የሚፈጠር አምባጓሮ ባስቸኳይ እንዲቆምና ወጣቱ ትውልድ በፍቅርና በመቻቻል ዘመኑን እንዲዋጅ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የአገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአባገዳ መሪዎች ወጣቶችን #እንዲያረጋጉ ጥሪ አቅርበዋል።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ት.ዲ.ት.ፓ.‼️

መንግስት የራያ ህዝብ እያቀረበ ያለውን የማንነት ጥያቄ ህገመንግስቱን ማዕከል በማድረግ #አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ ጠየቀ፡፡ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ኢንጅነር ግደይ ዘርዓፅዮን እንደተናገሩት፤ በትግራይና በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ አንዳንድ የፖለቲካ አመራሮች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በሚነዙት የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ምክንያት የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ምላሽ አጥቷል፡፡

በዚህም የህዝቡ ደህንነት አደጋ ላይ የወደቀ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል፡፡ በህዝቡ የተነሳውን ጥያቄ ሁለቱ ክልሎች ተመካክረው ሊፈቱት ይገባ የነበረ ቢሆንም ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ባለመስጠታቸው ምክንያት አንዱ ክልል በሌላው ላይ መንገድ እስከመዝጋት
የሚደርስ ተግባር የሚፈፀምበት ሁኔታ መኖሩን ምክትል ሊቀመንበሩ አመልክተዋል፡፡

"ፓርቲያችን በሁለቱም ክልሎች በየጎዳናው የሚደረገው ዛቻና ፉከራ ለማንም ይጠቅማል ብሎ አያምንም" ያሉት ምክትል ሊቀመንበሩ የራያ ህዝብ ጥያቄ በህገመንግስቱ መሰረት ወደ ፈዴሬሽን ምክር ቤት መጥቶ በህግ አግባብ ውሳኔ መሰጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡ "እኛ አሁን የምንጠይቀውና ጫና የምናደርገው የትግራይ ክልል መንግስትን ነው" ያሉት ምክትል ሊቀ መንበሩ ጉዳዩ በሌላ አካል ባይቀርብም እንኳ የክልሉ መንግስት ራሱ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ በማቅረብ እልባት እንዲያገኝ ማድረግ የሚጠበቅበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክትል ሊቀ መንበሩ የሁለቱም ክልል አመራሮች በህዝቦች መካከል ቅራኔ የሚፈጥሩ ትንኮሳዎችን በመከላከል የአገር ሰላምና ደህንነትን የማስጠበቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተመራቂዎቹ ጥያቄ....

"ሰላም ፀግሽ ...ዶክተር ሳ__ እንባላለሁ ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 16 ነበር የተመረቅኩት እስካሁን ስራ አልመደቡንም፤ ከዚህ በፊት ከሁለት ሳምንት በኃላ ነበር የሚመድቡት #FOMH አናግረን ነበር እናም ሁሉም ክልል ለሀኪም የሚሆን #በጀት_የለንም ብለዋል፤ ጠብቁ የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን። 7 አመታትን በአድካሚ የትምህርት ስርዓት አልፈን ይህ መሆኑ አሳዝኖኛል።"

ይህን መሰሉ በርካታ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየመጡ ናቸው፤ ተመራቂ ዶክተሮቹ መንግስት #አፋጣኝ_ምላሽ እና #መፍትሄ እንዲፈልግላቸው እየጠየቁ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ…
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ!

የአማራ ክልል 'የምዕራብ ጎንደር ዞን' ማህበራዊ ልማት መምሪያ በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር #አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ቫይረስ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችል አስታውቋል።

የአማራ ክልል ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100 እስከ 150 ሰዎች ድንበር #አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።

ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም።

የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል።

በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ችግሩ 'ከአቅም በላይ' እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ #ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ከሱዳንና ከጅቡቲ አካባቢዎች ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከፌደራል መንግስት ጋር በጋራ የምንፈታው ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት - የአማራ ክልል ባለስልጣናት - የህወሓት አመራሮች - የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ…
#US : አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ወደተኩስ አቁም ስምምነት የሚመጡ ከሆነ ለመጣል ያቀደችውን ማዕቀብ ልታዘገየው እንደምትችል ገለፀች።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት "በመካሔድ ላይ ያለውን ግጭት አቁመው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ በአፋጣኝ ድርድር የሚጀምሩ ከሆነ" ማዕቀቡ ሊዘገይ እንደሚችል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዘግይተው በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ፥ " ሁለቱ ወገኖች በዚህ ረገድ #አፋጣኝ_እርምጃ የሚወስዱ ከሆነ አሜሪካ ማዕቀቡን ለማዘግየት እና የድርድር ሒደቱን ለመደገፍ ዝግጁ ነች" ማለታቸውን ሮይተርስን ዋቢ በማድርግ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ? " የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ  ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል…
#Update

በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ#ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማኅብረቅዱሳን በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እና የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ መምህር ዋሲሁን በላይ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤታቸው በጸጥታ አካላት መወሰዳቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል። የሁለቱም አገልጋዮች የመኖሪያ ቤት መፈተሹም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት ሜክሲኮ ፌዴራል…
#Update

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ ትላንት በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ ተገልጾ ነበር።

ዛሬ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን አሳውቋል።

ምንም እንኳን አመራሮቹ በምን ምክንያት ተይዘው እነደነበር  ያብራራው ነገር ባይኖርም ፥ " በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት #አፋጣኝ_ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን " ብሏል።

@tikvahethiopia