TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የቤት አከራዮች የተከራዮቻቸውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ በደንብ ማረጋገጥ አለባቸው " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ሀሰተኛ የውጪ ሀገራትና የኢትዮጵያን ገንዘብ በማተም የተጠረጠሩ የውጪ ሀገር ዜጎች መያዙን አሳወቀ።

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መደረጉንም ገልጿል።

ሀሰተኛ ገንዘብ በማዘጋጀት ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች የተያዙት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው " ቦሌ አዲስ ትምህርት ቤት " አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አመልክቷል።

የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው 3 ግለሰቦች #ሙሉ_ግቢ የመኖሪያ ቤት በመከራየት  ሀሰተኛ ብር እና የውጭ ሀገር  ገንዘቦችን በማተም  እንደሚያሰራጩ እና የከበሩ ማዕድናትን በህገ-ወጥ መንገድ እንደሚያዘዋውሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ባሰባሰበው ማስረጃ ያረጋግጣል።

ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ በተደረገ ብርበራም ተጠርጣሪዎቹ ፦
- ሀሰተኛ ገንዘቦችን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን መሳሪያዎች ፣
- ልዩ ልዩ ኬሚካሎችን  ፣
- በሀሰተኛ መንገድ የታተሙ ገንዘቦች ፣
- በገንዘብ ልክ ተቆራርጠው የተዘጋጁ ወረቀቶች
- የዘንዶ ቆዳዎችን በኤግዚቢትነት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ሀሰተኛ ገንዘብ ከማዘጋጀት በተጨማሪ የፀና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው እየኖሩ ያሉና በህገ-ወጥ መንገድ የከበሩ ማእድናትን እንደሚዘዋውሩ በምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ ተመስርቶባቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ክ/ከተሞች ውስጥ በተመሳሳይ መንገድ ሀሰተኛ ገንዘቦችን ሲያትሙ የተገኙ ግለሰቦች እንደተያዙ አስታውሷል።

" መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው " ያለው ፖሊስ መኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ለወንጀሉ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ መሆናቸውን በመረዳት  የተከራዮቻችውን ማንነነት እና የሚሰሩትን ስራ የማረጋገጥ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia