TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ " ጉሎመኻዳ ወረዳ " አቅንቶ ነበር።

የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፤ " የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሊያዙ የተቻሉት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ በመታገዝ ነው " ብለዋል።

አቶ ሃፍቶም ፤ የትግራይ ኢትዮጵያዋ የጉሎመኻዳ ወረዳ ሰፊ አከባቢ ከሃገረ ኤርትራ የሚዋሰን በመሆኑና በጦርነቱ ምክንያት በዛላኣንበሳ ከተማ የነበረው የቁጥጥር ኬላ በመፍረሱ የተለያዩ እቃዎች በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ይተላለፋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

" ዛላኣምበሳ ጨምሮ የወረዳው ስድስት ቀበሌዎች #በኤርትራ_መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት አቶ ሃፍቶም ፤ በዚሁ በኩል ወደ ኤርትራ ለማሸጋገር የሚድረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመግታት እንዲቻል ህዝቡ ባለቤት በመደረጉ ምክንያት አመርቂ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የዞኑ የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኪዱ ገ/ፃድቃን በበኩላቸው ፤ ከግንቦት እስከ ሃምሌ 2015 ዓ.ም  የ4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ መሳሪዎች በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

የተያዙት ፦
- ጤፍ ፣
- የፊኖ ዱቄት ፣
- ቡና ፣
- የመብል ዘይት ፣
- ነዳጅ ፣
- የሞባይል ቆፎዎች ፣
- ጌሾ ፣
- በርበሬ ፣
- የቤት እቃዎች ፣
- ዘመናዊ ማዳበሪያ ፣
- ስሚንቶ ፣
- ቴንዲኖና የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉሎመኸዳና ኢሮብ ከኤርትራ የሚዋሰኑ የምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች መሆናቸው የጠቀሱት አቶ ኪዱ ፤ ብዘት ዳሞ ፣ ፋፂ ዛላኣምበሳ ፣ ሰበያ፣ ደውሃን ዓይጋ የሚባሉት ቦታዎች ዋና የህገወጥ ኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች መሆናቸው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊው ፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ንብረቶች በመቆጣጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስፍራው ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኃላፊዎች ፦
-  የኮንትሮባንድ ዝውውር እንዴት እየተፈፀመ እንዳለ
- በኤርትራ ኃይል ስር ስላሉት አካባቢዎች
- በአካባቢው ስላለው የህገወጥ ሰዎች ዝውውር
- በጦርነት ምክንያት ስለወዳደቁ ብረቶች
- የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመከለከል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ ስላለው የጋራ ስራ   የሰጡትን ቃል በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#ጥናት #ሞዴስ

በኢትዮጵያ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ለመግዛት ከሚያገኙት ገቢ አንጻር ከፍተኛ ወጪ እንደሚያወጡ " ቢቢሲ አፍሪካ ቪዡዋል ጆርናሊዝም " ባካሄደው ጥናት አመልክቷል።

ጥናቱ ፦ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ዋጋ ምን ያህል ተመጣጣኝ እንደሆነ ለማየት የተደረገ ነው። 9 የአፍሪካ ሀገራትንም ዳሷል።

ጥናቱ ፤ ዝቅተኛ ወርሃዊ ገቢን ከርካሽ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ዋጋ ጋር ያነጻጸረ ሲሆን በዚህም የምርቶቹ ዋጋ የበርካታ ሴቶችን አቅም ያገናዘቡ እንዳልሆኑ ደምድሟል።

ጥናቱ የተደረገባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው ?
- ጋና፣
- ኢትዮጵያ፣
- ሶማሊያ፣
- ኡጋንዳ ፣
- ናይጄሪያ፣
- ሩዋንዳ፣
- ታንዛኒያ፣
- ደቡብ አፍሪካ
- ኬንያ ናቸው።

በጋና ዝቅተኛ ደመወዝ ያላቸው ሴቶች ከሚያገኙት ገቢ #ከፍተኛ የተባለውን ወጪ የሚያወጡባት ሲሆን ኢትዮጵያ ከጋና ቀጥላ ተቀምጣለች ፤ ኬንያ በአንጻሩ ምርቶቹ ርካሽ የሆነባት አገር ናት።

ከ9ኙ አገራት መካከል በ6ቱ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሴቶች በየወሩ እያንዳንዳቸው 8 ነጠላ ሞዴሶችን የያዙ 2 እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለመግዛት ከደመወዛቸው ከ3 እስከ 13 በመቶ የሚሆነውን ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

በጋና አንዲት ሴት ከምታገኘው ዝቅተኛ ደመወዝ ተብሎ ከተቀመጠው 26 ዶላር ውስጥ ሦስቱን ዶላር ወይም ከሚያገኙት 7 ዶላር ውስጥ አንዱን፣ ሁለት እሽግ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት ታወጣለች።

ይህም አሜሪካ እና በዩኬ ካሉ ሴቶች ጋር ሲነጻጻር እጅግ ከፍተኛ ነው። በአሜሪካ ሴቶች ከሚያገኙት 1 ሺህ 200 ዶላር ዝቅተኛ ገቢ የንጽህና መጠበቂያ ምርት ለመግዛት የሚያወጡት 3 ዶላር ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ አንዲት ሴት ከምታገኘው ገንዘብ በአማካይ ስድስት በመቶውን ለሞዴስ ታወጣለች ብሏል ጥናቱ።

በኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በፊት በመሰረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ ማድረጓን የአገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቆ ነበር።

በዚህ ውሳኔ መሠረት እነዚህ የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን መደረጉን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም።

ጎረቤት አገር ኬንያ በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ከቀረጥ ነጻ በማድረግ ከዓለም የመጀመሪያዋ አገር የሆነችው እንደ አውሮፓውያኑ 2004 ነበር።

ከ2 ዓመት በኋላ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን ለማምረት የሚውሉ ጥሬ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ አድርጋለች።

በዚህ ምክንያት በኬንያ ያለው የንጽህና መጠበቂያ ዋጋ ቀንሷል። አሁን ላይ ርካሹ የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) በ35 የአሜሪካ ሳንቲም ይሸጣል።

ሆኖም ሴት ፖለቲከኞች እና ተሟጋቾች ምርቶቹ ከዚህ ያነሰ ዋጋ ለተገልጋዮች እንዲቀርቡ አሁንም እየጠየቁ ነው።

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢዝነሳችሁን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናችሁ?

ለVisa Everywhere Initiative 2015/16 E.C ልዩ የኢትዮጵያ ውድድር በመመዝገብ እውቅና ማግኘት፣ የቬንቸር ካፒታሊስቶችን ዐይን መሳብ ፣ ኢንቬስትመንት እና አጋሮችን
ማግኘት ይቻላል።

ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14 ድረስ ክፍት ነው።
https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-i
nitiative/initiative.html

#EverywhereInitiative
TIKVAH-ETHIOPIA
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ? በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች ምን አሉ ? #ባሕርዳር ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም። የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው…
#Amahra

በአማራ ክልል ከተሞች ላይ ያለው አንፃራዊ ሰላም አሁንም መቀጠሉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ፤ ከተማዋ ወደ ቀደመው መረጋጋት እየተመለሰች መሆኑን ገልጸዋል።

የሰዎች እንቅስቃሴም ካለፉት ቀናቶች በተሻለ መኖሩን ጠቁመው አሁንም አንዳንድ በትልልቅ ቋጥኞች የተዘጉ መንገዶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ፤ ካለፉት ቀናት ጀምሮ በከተማው የቱክስ ድምፅም ሆነ ግጭት እንደሌለ አመልክተዋል።

በጎንደርም አንፃራዊ ሰላም ያለ ሲሆን ታክሲዎች፣  የቤት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን ፤ ሱቆች እና አንዳንድ ተቋማት መከፈታቸውን ነዋሪዎች አመልከተዋል።

አንድ ነዋሪ ፤ ትላንት በርካታ የከተማው ነዋሪዎች በወፍጮ ቤት እህል ለማስፈጨት እና ሱቆች ላይ እቃ ለመሸመት ተሰልፈው መመልከቱን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ግጭቱትን ተከትሎ የሸቀጦች ዋጋ በመናሩ ህብረተሰቡ እየተቸገረ መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ ተቀስቅሶ የነበረውን ውጊያ ተከትሎ በሸቀጦች ላይ በእጥፍ ጭማሪ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

አንድ የደሴ ነዋሪ ፤ ውጊያ ከመቀስቀሱና መንገድ በመዘጋቱ በፊት 6,800 ብር ይገዛ የነበረው አንድ ኩንታል ነጭ የዳቦ ዱቄት 8,800 ብር መግባቱን ገልጸዋል። ውጊያው ከፈጠረብን ጭንቀት በላይ የተጋነነው የሸቀጦች ዋጋ ያሳስበናል ብለዋል።

እስከ 800 ብር ይገዛ የነበረ 5 ሊትር ዘይት 1150 ብር ፤ 50 ብር የነበረው አንድ ኪሎ ሽንኩርት እና ቲማቲም 100 ብር ፣ እስከ 90 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ ስኳር 120 ብር መግባቱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ ነጋዴ ከአዲስ አበባ ያመጣንበት ዋጋ ውድ በመሆኑ ጭማሪ ለማድረግ ተገድጃለሁ ያሉ ሲሆን ይህ የነጋዴው ምላሽ ግን ፍፁም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ከነዋሪዎች አስተያየት የሰጡ ገልጸዋል።

ውጊያ ከተነሳ በኃላ መንገድ ተዘግቶ ስለነበር ነጋዴ በውድ ዋጋ ሊያመጣ የሚችልበት መንገድ የለም ፤ ቀድሞ ከውጊያ በፊት የገባን ምርት ጨምሮ መሸጥ ሸማቹን ለችግር መዳረግ ነው ብለዋል።

እኚሁ አስተያየት ሰጪ ምርቶችን የመከዘን ሁኔታ መኖሩን ገልጸዋል።

በባህር ዳር በግጭቱ ሳቢያ ውሃ 1 ሳምንት መጥፋቱን አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ውሃ ፍለጋ ጉድጓድ ወዳለበት ጄሪካን ይዞ ለመሄድ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በጎንደር በግጭቱ ምክንያት ለ6 ቀን ውሃ ተቋርጦ መቆየቱን አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ክፍል ባልደረባ ገልጸዋል።

የውሃ አገልግሎት መቋረጡ በቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል አገልግሎቱን የሚያገኙ ወላድ እናቶች ላይ እንዲሁም በሌሎች ህሙማን ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን ጠቁመዋል።

ውሃ ባለመኖሩ ሃኪሞች የሚለብሱት ጋዋን ፣ ቀዶ ህክምና የሚደረግላቸው ህሙማን የሚለብሱት አልባሳት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሳይታትጠብ መቆየቱን ገልጸዋል። እንደ አማራጭ ከሌሎች ህክምና ተቋማት አልባሳትን መዋስ ፣ የዝናብ ውሃ እስከመጠቀም ተደርሶ ነበር ብለዋል።

ማክሰኞ እና ረቡዕ ችግሩ ተባብሶ ቀዶ ጥገና ተቋርጦ እንደነበር አስተውሰዋል። ከትላንት ጀምሮ ግን የተቋረጠው የሆስፒታሉ ውሃ መምጣቱን የህክምና ባልደረባው አመልክተዋል።

መረጃው ከቪኦኤ (መስፍን አራጌ) የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መታየት የጀመረው የአንበጣ መንጋ ብዛትና ስፍቱ እየጨመረ እንደሆነ የአይን እማኞች አረጋገጡ ።

ነሃሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ዞኖች በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የአንበጣ መንጋ ታይተዋል።

የአንበጣ መንጋው በምስራቃዊ ዞን ጉሎ መኸዳ ፣ ኢሮብ ፣ ፅራእ ወምበርታ ፣ ስቡሓ ሳዕስዕ ወረዳዎች ፤ በደቡባዊ ምስራቅ ዞን በእንደርታ ወረዳ ፣ በደቡባዊ ዞን አምባላጀ ወረዳ ታይተዋል።

የአንበጣ መንጋው ከዓፋር ክልል አቅጣጫ መምጣቱ የጠቆሙት ባለሞያዎች ፣ ህብረተሰቡ በየአከባቢው በባህላዊ መንገድ መከላከል እንዲቀጥልና ጊዚያዊ አስተዳደሩና የፌደራል መንግስትም ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አሳስበዋል።

መረጃው ከትግራይ መቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
                         
Photo Credit  : Ataklti Arefe / Tsegay Gebretekle

@tikvahethiopia
#COOP

የዓመቱ ትልልቅ ግጥሚያዎች እነሆ ጀምረዋል! ከመዝናኛው ዓለም አይራቁ !
የDSTV ክፍያዎን በኮፔይ ኢብር ይክፈሉ።
@coopbankoromia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፤ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሰብአዊ መብቶች ሊከበሩና ለግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ ለሰላማዊ ውይይት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ ፤ ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እየተባባሰ የመጣውን የአማራ ክልል የትጥቅ ግጭትና የጸጥታ ችግር እንዲሁም በሰብአዊ መብቶች ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ ሲከታተል መቆየቱንና ይህንኑም አስመልክቶ በነዋሪዎች እና…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰኮ) ፤ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ላይ ያዘጋጀውን ባለ 26 ገጽ የሰብአዊ መብቶች ትንታኔ እና ዝርዝር ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መላኩን አስታውቋል።

በመጪው ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዋጁ ላይ ለመምከርና ለመወሰን አስቸኳይ ስብሰባ የጠራው የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች በጥንቃቄ አጢኖ ተግባራዊ እንዲያደርጋቸው ኮሚሽኑ ጠይቋል፡፡

ኮሚሽኑ ለምክር ቤቱ በላከው የትንታኔ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተለይም ፦
- በአዋጁ የተመለከቱ ክልከላዎችና ግዴታዎች፣
- ለመንግሥት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣
- የአዋጁ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰን፣
- የሕዝብ ተወካዮች እና ዳኞችን ያለምክር ቤቱ ውሳኔ አለመያዝና መከሰስ ልዩ መብት (mmunity) ሌሎችም ሊገደቡ ስለማይችሉ መብቶች ጥበቃ፤
- በአጠቃላይ የአዋጁ እያንዳንዱ አንቀጾች ከጥብቅ አስፈላጊነት (Necessity) ተመጣጣኝነት (Proportionality) እና ሕጋዊነት (legality) አንጻር አንዲመረመሩ ይጠይቃል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በነበሩት ተከታታይ ቀኖች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ተከስቶ የነበረው የሰላምና ደህንነት ልዩ አደጋ በአሁኑ ወቅት ተወግዶና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ወደ ነበሩበት ሁኔታ መመለስ መጀመራቸው በመንግሥት በይፋ የተገለጸ በመሆኑ ምክር ቤቱ ፦ በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን አስፈላጊነት፣ ከባቢያዊና የጊዜ ተፈጻሚነት ወሰንን በተለይ በጥንቃቄ በማጤን ምክር ቤቱ አዋጁን የሚያጸድቀው ቢሆን ፦

👉 የጊዜ ተፈጻሚነቱ ከአንድ ወር ወይም የተወሰኑ ሳምንታት የበለጠ እንዳይሆን፤

👉 የከባቢያዊ ተፈጻሚነቱም ልዩ አደጋው ተከስቷል በተባለበት ቦታ ብቻ የተገደበ እንጂ በጠቅላላ ሀገሪቱ እንዳይደረግ ኮሚሽኑ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡

(ይህ የተመለከተ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ቁጥር_6_2015_በተመለከተ_ከኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን_ኢሰመኮ_የተሰጠ_ምክረ.pdf
916.4 KB
#EHRC

" የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 " በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የላከው ምክረ ሃሳብ በዚህ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቶ ነበር። አብን በዚህ መግለጫው ፤ በየትኛውም አሰላለፍ እና አግባብ ስለአማራ ህዝብ የተሰለፉ ሀይሎች #ጦርነት ዘላቂ ጥቅምን ለማረጋገጥ አስቻይ እንዳልሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ብሏል። ይልቁን ጦርነት ህዝብን ለተደራራቢ የማህበራዊ ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ስለሚዳርግ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄዎች ተገቢውን…
" በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ዘፈቀዳዊ የማንነት ተኮር ጅምላ እስራቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው " - አብን

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፤ በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ ከተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚፈፀም ማንነት ተኮር የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተስተዋለ መሆኑን አሳውቋል።

በዚህ ረገድ አዋጁን ተገን በማድረግ በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ዘፈቀዳዊ የማንነት ተኮር ጅምላ እስራቶች እየተፈፀሙ መሆኑን፣ በዚህ መልኩ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ ወዳልታወቁ ቦታዎች ተወስደው መታሰራቸውን እንዲሁም ዛቻዎች፣ የቤት ብርበራዎች፣ አካላዊ ጥቃቶች እና ማንነት ተኮር ዘለፋዎች እየተፈጸሙ መሆኑን ፓርቲው ገልጿል።

ከምንም በላይ ማንነት ተኮር ጅምላ እስር እና የመብት ጥሰት፤ ጽንፈኛ የፖለቲካ አተያይ ያላቸው የህግ አስፈጻሚ ግለሰቦች አዋጁን ተገን አድርገው አማራዊ ማንነትን ወንጀል የማድረግ አካሄድ በአስቸኳይ እርምት ካልተወሰደበት የሚያስከትለው ዳፋ ከባድ እንደሚሆን በጥብቅ ማስገንዘብ እንፈልጋለን ብሏል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን ገልጾ ፤ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን አጠቃላይ ስጋት በሚመለከት ክትትል እያደረገና ተጨባጭ መረጃዎችም እየደረሱት እንደሚገኙ አመልክቷል።

የደረሱትን ጥቆማዎች ተከትሎ ባደረገው ማጣራትም የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ምክንያት ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተዳረጉና በተለይም ለማንነት ተኮር እስራት እና ለቤት ውስጥ ፍተሻዎች መጋለጣቸውን ማረጋገጥ መቻሉልን በመግለጫው አሳውቋል።

በመሆኑም:-

የፌዴራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ጋር በተያያዘ በፀጥታ አካላቱ፣ በማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች፣ እንዲሁን በልዩ ልዩ አግባብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በተደራጁ ተቋማት ላይ ጥብቅ ክትትልና ምርመራ በማድረግ ከአሁን በፊት የተፈጸሙ ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲታረሙ እና ጥፋተኞችም ተጠያቂ እንዲሆኑ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

በቀጣይም አዋጁን ተገን በማድረግ ምንም እይነት ማንነት ተኮር የዘፈቀደ እስራቶች እና ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ የማድረግ ተጨባጭ ርምጃ እንዲወስዱ ፓርቲው አሳስቧል።

በተጨማሪ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎች እና አንድምታ ውጭ በማንነት ተኮር ጅምላ ፍረጃ ምክንያት የተያዙ እና በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሃን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ አሳስቧል።

የሀገር ውስጥና ዓለም-አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀሙትን ማንነት ተኮር ጥቃቶች በማጣራት ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርጉ እንዲሁም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መልኩ በጥፋት ተግባሩ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን በመለየትና ተጠያቂ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አብን ጠይቋል።

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌዎች እና አንድምታ ውጭ በማንነት ተኮር ጅምላ ፍረጃ ምክንያት የተያዙ እና በእስር ላይ የሚገኙ ንፁሃን በአስቸኳይ ይለቀቁ ዘንድ ጫና እንዲፈጥሩም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

(የፓርቲው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከምባታጠምባሮ

የዱራሜ ከተማ የምክር ቤት አባላት በሙሉ እየተደራጀ በሚገኘው ክልል ያለውን የቢሮ ክፍፍል ተቃወሙ።

አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል።

የምክር ቤት አባላቱ ጥያቄውን ያቀረቡት በ2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የምክር ቤት አባላት ምን አሉ ?

አዲስ እየተደራጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም ያለማግኘት እና ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል በመሆኑ በፍጹም መታረም ያለበት ነው ብለዋል።

እኩል የመልማት ፣ የመበልፀግና የማደግ መብት እንዲከበርም ጠይቀዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ  ክልል " የክላስተር አደረጃጀት ያለው ኢ-ፍትሃዊ አደረጃጀትን በሙሉ ድምፅ በመቃወም ፤ በቀጣይ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ በመጠየቅ አስቸኳይ ጉባኤያቸውን አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ በቢሮ ክፍልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ የዱራሜ ነዋሪዎች ሰኞ በሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሰልፉን የሚያስተባብረው አካልም ከከተማው ፍቃድ እንዳገኘ ተሰምቷል። በዚህም ሰኞ ጥዋት ከ3 እስከ 5 ድረስ በዱራሜ ኢፍትሃዊ ነው የተባለውም የተቋማት ክፍፍል የሚቃወም እና ማስተካከያ እንዲደረግበት የሚጠይቅ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia