TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE የውጭ ምንዛሬ ክፍፍል ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ የብሄራዊ ባንክ ቦርድ መወሰኑን " ካፒታል " ጋዜጣ ዘግቧል። በዚህም ውሳኔ መሰረት የውጭ ምንዛሬ ክፍፍሉ ቀደም ሲል ከነበረው 70/30 ወደ 50/50 እንዲስተካከል ተደርጓል። በውሳኔው መሰረት ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግኝታቸው 50 በመቶ ለብሄራዊ ባንክ 40 በመቶውን የውጭ ምነዛሬውን ላመነጨው አካል እንዲሁም ቀሪውን 10 በመቶ ለባንኮች እንዲከፋፈል…
#NBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፤ የዋጋ ንረትን ለማርገብ የሚያስችል የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ ወስኗል።

ይህ በተመለከተ የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫው ምን ምን ነጥቦችን አነሱ ?

- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እያየለ የመጣውን የዋጋ ንረት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቆጣጠር የብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ አሳልፏል።

- ከውሳኔዎቹ መካከል ለመንግስት የሚሰጠው የቀጥታ ብድር ባለፈው አመት ከተሰጠው ከ1/3ኛ እንዳይበልጥ ይደረጋል።

- መንግስት ቅድሚያ የግምጃ ቤት ሰነድ አማራጭን አሟጦ እንዲጠቀምና አማራጭ ሳይኖር ሲቀር ብቻ የቀጥታ ብድር ይጠቀማል።

- በ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ሰኔ መጨረሻ የሃገር ውስጥ ብድር ዕድገት በ14 በመቶ ጣሪያ ይገደባል። ሁሉም ንግድ ባንኮች የብድር ዕድገት ዕቅዳቸውን በዚህ የብድር ጣሪያ መሰረት እንዲያስተካክሉ ይደረጋል።

- ባንኮች የገንዘብ እጥረት ሲገጥማቸው ከብሄራዊ ባንክ ከሚወስዱት ብድር የብድር ፋሲሊቲ ላይ የሚከፍሉት ወለድ ከ16 በመቶ ወደ 18 በመቶ ከፍ እንዲል ይደረጋል።

- ቁልፍ የሆኑ የወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዘርፎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ላኪዎችን ለማበረታታት ከዚህ ቀደም የነበረው የውጭ ምንዛሬ የማስተላለፍ ግዴታ ከ70/30 ወደ 50/50 እንዲሻሻል ይደረጋል። ላኪዎች 50 በመቶውን ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስገቡ፣ 10 በመቶውን አብረው ለሚሰሩት ባንክ እንዲሰጡ እና 40 በመቶውን ለራሳቸው እንዲጠቀሙ ተወስኗል።

- በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ የዋጋ ንረቱ ከ20 በመቶ በታች እንዲሆንና በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ ከ10 በመቶ በታች ለማውረድ ይሰራል።

ህብረተሰቡ ውሳኔውን በመደገፍ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ ቀርቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ #ትግራይ ክልል ማስወጣቷን " ጄሩሳሌም ፖስት " ዘግቧል። እስራኤል በአማራ ክልል ውስጥ ያለውን ግጭትና የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቅርበት እየተከታተለችው መሆኑ ተነግሯል። ባለፈው ሰኞ ከአካባቢው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን ተጓዥ ዜጎቿን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ እንዲወጡ ማድረጓ ተገልጿል። ዘገባው ተካሂዷል ባለው የእስራኤል ዜጎችን ከግጭት ቀጠና…
#Update

እስራኤል ዜጎቿን ከአማራ ክልል አስወጣች።

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ትዕዛዝ ከ200 በላይ እስራኤላውያን ከባሕር ዳር እና ጎንደር መውጣታቸው ተዘግቧል።

በርካታ ቤተ እስራኤላውያን በሚገኙበት የአማራ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ ፦
- የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣
- በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ፣
- የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣
- የእስራኤል የደኅንነት ም/ቤት
- የአይሁዳውያን ተቋም በጋር ሆነው ዜጎቻቸው ከክልሉ እንዲወጡ አድርገዋል።

በዚህም ከጎንደር ከተማ 174 ከባሕር ዳር ደግሞ 30 ቤተ እስራኤላውያን ትላንት እንዲወጡ ተድረገዋል።

እስራኤላውያኑ እንዴት ወጡ ?

ረቡዕ ምሽት ላይ ካሉባቸው ከተሞች እንዲወጡ ለማስቻል በተመቻቹላቸው የመሰባሰቢያ ቦታዎች ላይ እንዲገኙ ከተደርገ በኋላ ወደ ጎንደር እና ባሕር ዳር አውሮፕላን ማረፊያዎች ተወስደዋል።

በአየር ማረፊያዎቹም ቀድመው በተዘጋጁ ልዩ በረራዎች አማካይነት እንዲጓጓዙ ተደርገው አዲስ አበባ ሐሙስ ዕለት ገብተዋል።

እስራኤላውያኑን ከአማራ ክልል የማስወጣት ተልዕኮ በእስራኤል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጥ ባለ የመከታተያ ክፍል (ሲችዌሽን ሩም) እገዛ የተደረገለት ሲሆን ዲፕሎማቶች፣ የአይሁዳውያን ተቋም ሠራተኞች እና አማርኛ የሚችሉ የእስራኤል ሠራዊት አባላት በቡድኑ ውስጥ ነበሩበት ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት እንዳለው ዜጎቹ ወደ አስራኤል ለመመለስ አስኪወስኑ ድረስ በአዲስ አበባ ውስጥ ይቆያሉ።

ኔትያንያሁ ምን አሉ ?

ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ " እስራኤል ዜጎቿን ባሉበት ቦታ ሁሉ ጥበቃ ታደርጋለች " ያሉ ሲሆን " ባለፉት ቀናት ግጭት ባለበት የኢትዮጵያ አካባቢ ዜጎቻቻን ነበሩ። ከዚያ እንዲወጡ እንዲደረግ አዝዣለሁ " ብለዋል። አገራቸው ዜጎቿን በደስታ እንደምትቀበልም መግለፃቸውን #ቢቢሲ_አማርኛ ዘግቧል።

እስራኤል ከቀናት በፊት ጥቂት ዜጎቿን ከአማራ ክልል ደባርቅ ወደ ትግራይ ሽረ ከተማ ማስወጣቷ ይወሳል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የእስራኤል ጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#Update

- የአውስትራሊያ ፣
- የጃፓን ፣
- የኒውዚላንድ፣
- የእንግሊዝ እና የዩናይትድ ስቴትስ መንግስታት በቅርቡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሰላማዊ ዜጎች ሞት እና አለመረጋጋት ያስከተለው ግጭት እንዳሳሰባቸው ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

ሀገራቱ ፤ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ እና የሚያጋጩ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተባብረው እንዲሰሩ አበረታተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፦
- የአውሮፓ ህብረት ልዑክ በኢትዮጵያ
- የኦስትሪያ ፣
- የቤልጂየም ፣
- የቼክ ሪፖብሊክ ፣
- የዴንማርክ ፣
- የፊንላንድ ፣
- የፈረንሳይ ፣
- የጀርመን ፣
- የሃንጋሪ ፣
- የአየርላንድ ፣
- የኢጣሊያ ፣
- የሉክሰምበርግ ፣
- የማልታ ፣
- የኔዘርላንድስ ፣
- የሮማኒያ ፣
- የፖላንድ ፣
- የፖርቹጋል ፣
- የስሎቬንያ ፣
- የስፔን እና የስዊድን ኤምባሲዎች በጋር ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ሁከትና የዜጎች ሞትና አለመረጋጋት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ሀገራቱ ፤ " ሁሉም ወገኖች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች የተሟላ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ፣ የውጭ ዜጎች ከግጭቱ አካባቢ ለቅቀው እንዲወጡ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲተላለፉ እንዲፈቀድ፤ የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም በሚቀጥልበት ጊዜ ውስብስብ ጉዳዮችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት በጋራ መስራት፣ እና ግጭቱ ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ተዛምቶ ብጥብጥ እንዳይፈጠር ተገቢው መከላከል እንዲደረግ እናበረታታለን " ብለዋን።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የረዥም ጊዜ የመረጋጋት ግብ ድጋፉን ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት አካውንትዎን ያለማንም እርዳታ በኢ-ኬር ድረ-ገጽ ያስተዳድሩ!

✔️ የአገልግሎት መረጃዎን ማየት እና ማስተዳደር
✔️ ወርሀዊ የድሕረ-ክፍያ ቢል እና የአጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት
✔️አገልግሎት መቋረጥ/ብልሽት ሪፖርት ለማድረግ እና ለመከታተል
✔️የአገልግሎት (የጥሪ፣ መልዕክት፣ ዳታ) አጠቃቀም ዝርዝር ለማግኘት
✔️ፒን እና ፒዩኬ ለማግኘት

እነዚህንና ሌሎች በርካታ እገልግሎቶችን በኢ-ኬር  ለማግኘት በቀጣዩ ሊንክ
https://www.ecare.ethiotelecom.et ይመዝገቡ፤ ይጠቀሙ!
#HamaqPLC
Car Hand Break And Gear Shift Lock -ለመኪናዎ የሚያገለግል አስተማማኝ መቆለፊያ  
-በአሁኑ ጊዜ እየተበራከተ ለመጣው የመኪና ስርቆት ሁነኛ መፍትሄ
-በኮንዶሚኒየም፣አፓርታማና በጋራ መኪና ማሳደሪያ ለሚጠቀሙ ተመራጭ
-የእጅ ፍሬንን ከማርሽ ጋር የሚቆልፍ    

ዋጋ =3000 ብር  ☎️ 0912917632 ከየማይቀረፅ ቁልፎች ጋር ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን::👉Free delivery

አድራሻ:- አቢሲኒያ ፕላዛ
በጋሞ አካባቢ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ?

አዲሱ የፌዴሬሽኑ 12ኛ ክልል " የደቡብ ኢትዮጵያ " በይፋ ከነባሩ ክልል ስልጣን ከተረከበ ኃላ በጋሞ አካባቢ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከመዋቅሩ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል።

ምንድነው ጥያቄው ?

አዲሱ አደረጃጀት ሕዝብ ሲያነሳ የነበረውን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ፤ መንግሥት የ " ጋሞ ክልላዊ መንግሥት " ምስረታን ጥያቄ ቸል በማለት የክላስተር አደረጃጀትን ተግባራዊ እያደረገ ነው በሚል ነው።

አንድ በአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ሰሞነኛውን ሁኔታ በተመለከተ ባላኩት መልዕክት ፤ መጀመሪያውንም ሲጠየቅ የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደር የክልልነት ጥያቄ ነበር ፤ ነገር ግን ያ ጥያቄ ተገቢው ምላሽ ሳያገኝ የክላስተር አደረጃጀት ተግባራዊ እየሆነ ነው ብለዋል።

የክልል ጥያቄው እንዳለ ሆኖ ከዚህ ቀደም የአዲሱ ክልል የርዕሰ መስተዳደር መቀመጫ ' አርባ ምንጭ ' ትሆናለች ተብሎ ሲነገር ቢቆይም አሁን ላይ ይህ አልሆነም ይህ ደግሞ በፖለቲካዊ አሰራር የተፈፀም የማታለል ተግባር ነው በሚል ከፍተኛ ቅሬታን አሳድሯል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን ላይ እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ጋሞ እራሱን ችሎ ክልል ይሁን የሚል ነው። ለዚህም ሃሳቡን የሚደግፉ በተለያየ መንገድ ሰላማዊ ተቃውሞ እያሰሙ ነው " ብለዋል።

ከዚሁ በ ' ጋሞ ዞን ' ካለው ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ " ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " ለትላንት ነሐሴ 4 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርብም ሰልፉ በመከልከሉ ሳይደረግ መቅረቱን ለማውቅ ተችሏል።

ፓርቲው ፤ መንግሥት የጋሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለማቋቋም የተጠየቀውን የህዝብ ጥያቄ በመቀልበስ በክላስተር ክልል ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊ እንቅስቃሴ በማቆም ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤን በሚል ነው የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው።

በሰልፉ ላይ የጋሞ ክልላዊ መንግስት ማቋቋምን በሚመለከት " ጋሞ ክልላችን አርባ ምንጭ ማዕከላችን ፤ የጋሞ ጥያቄ ክልል እንጂ ክላስተር አይደለም " የሚሉ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ታቅዶ ነበር።

የዞኑ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ግን ለህዝብ ሠላምና ደህንነት ሲባል የሰላማዊ ሰልፉ #እንዳልተፈቀደ ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ በማሳወቁ ሰልፉ ሳይደረግ ቀርቷል።

ፓርቲው ከሰሞኑን ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንግሥት ጥያቄ ለማፈን እየጣረ እንደሆነና አባላቱንም እንዳሰረበት ገልጿል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ስለ አዲሱ ክልል ምን ይላሉ ?

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከቀናት በፊት ከአርባ ምንጭ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት አዲሱ ክልል ከምስረታው ጀምሮ የዞኑን ህዝብ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲደራጅ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

" የተሰጠን ከፍላጎታችን ጋር የማይመጣጠን ነው "  አቶ ብርሃኑ " አብረውን ለተደራጁ ህዝቦች ፍላጎት አክብሮት ሲባል መቀበል ይኖርበናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የክልሉን ህግ አውጪ ጨምሮ ግዙፍ  እና ብዙ ተገልጋይ ያሉዋቸው ተቋማት መቀመጫቸውን አርባምንጭ ከተማ ማድረጋቸውን ያብራሩት አቶ ብርሃኑ ተቋማቱ የአከባቢውን የመልማት አቅም እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት  ያሳድጋሉ ብለዋል።

የዞኑ ነዋሪችም መቀመጫቸው አርባምንጭ ከተማ እንዲሆኑ የተመደቡ ቢሮዎችን ለመቀበል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከጋሞ ዞን ባገኘው መረጃ ዛሬ የዞኑ ምክር ቤት የአዲሱ ክልል " ረቂቅ ህገመንግስት " ላይ ሲመክር ውሏል። በተጨማሪ በከተማ እና በወረዳ ደረጃ ውይይቶች ሲደረጉ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ " ጉሎመኻዳ ወረዳ " አቅንቶ ነበር።

የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ በሰጡት ቃለመጠይቅ ፤ " የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ሊያዙ የተቻሉት በህዝብ የነቃ ተሳትፎ በመታገዝ ነው " ብለዋል።

አቶ ሃፍቶም ፤ የትግራይ ኢትዮጵያዋ የጉሎመኻዳ ወረዳ ሰፊ አከባቢ ከሃገረ ኤርትራ የሚዋሰን በመሆኑና በጦርነቱ ምክንያት በዛላኣንበሳ ከተማ የነበረው የቁጥጥር ኬላ በመፍረሱ የተለያዩ እቃዎች በኮንትሮባንድ መልክ ወደ ኤርትራ ይተላለፋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

" ዛላኣምበሳ ጨምሮ የወረዳው ስድስት ቀበሌዎች #በኤርትራ_መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ " ያሉት አቶ ሃፍቶም ፤ በዚሁ በኩል ወደ ኤርትራ ለማሸጋገር የሚድረግ ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርና ለመግታት እንዲቻል ህዝቡ ባለቤት በመደረጉ ምክንያት አመርቂ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ለቲክቫህ አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡት የዞኑ የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ኪዱ ገ/ፃድቃን በበኩላቸው ፤ ከግንቦት እስከ ሃምሌ 2015 ዓ.ም  የ4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ መሳሪዎች በህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ሲሉ ተይዘዋል ብለዋል።

የተያዙት ፦
- ጤፍ ፣
- የፊኖ ዱቄት ፣
- ቡና ፣
- የመብል ዘይት ፣
- ነዳጅ ፣
- የሞባይል ቆፎዎች ፣
- ጌሾ ፣
- በርበሬ ፣
- የቤት እቃዎች ፣
- ዘመናዊ ማዳበሪያ ፣
- ስሚንቶ ፣
- ቴንዲኖና የቤት ክዳን ቆርቆሮ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉሎመኸዳና ኢሮብ ከኤርትራ የሚዋሰኑ የምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች መሆናቸው የጠቀሱት አቶ ኪዱ ፤ ብዘት ዳሞ ፣ ፋፂ ዛላኣምበሳ ፣ ሰበያ፣ ደውሃን ዓይጋ የሚባሉት ቦታዎች ዋና የህገወጥ ኮንትሮባንድ መተላለፊያ መስመሮች መሆናቸው ገልፀዋል።

የፀጥታ ጉዳይ ሃላፊው ፤ ህዝቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ንብረቶች በመቆጣጠር ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ስፍራው ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኃላፊዎች ፦
-  የኮንትሮባንድ ዝውውር እንዴት እየተፈፀመ እንዳለ
- በኤርትራ ኃይል ስር ስላሉት አካባቢዎች
- በአካባቢው ስላለው የህገወጥ ሰዎች ዝውውር
- በጦርነት ምክንያት ስለወዳደቁ ብረቶች
- የኮንትሮባንድ ዝውውርን ለመከለከል ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተሰራ ስላለው የጋራ ስራ   የሰጡትን ቃል በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia