TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በጋሞ አካባቢ የተነሳው ጥያቄ ምንድነው ?

አዲሱ የፌዴሬሽኑ 12ኛ ክልል " የደቡብ ኢትዮጵያ " በይፋ ከነባሩ ክልል ስልጣን ከተረከበ ኃላ በጋሞ አካባቢ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ከመዋቅሩ ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል።

ምንድነው ጥያቄው ?

አዲሱ አደረጃጀት ሕዝብ ሲያነሳ የነበረውን ጥያቄ የሚመልስ አይደለም ፤ መንግሥት የ " ጋሞ ክልላዊ መንግሥት " ምስረታን ጥያቄ ቸል በማለት የክላስተር አደረጃጀትን ተግባራዊ እያደረገ ነው በሚል ነው።

አንድ በአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ሰሞነኛውን ሁኔታ በተመለከተ ባላኩት መልዕክት ፤ መጀመሪያውንም ሲጠየቅ የነበረው ራስን በራስ የማስተዳደር የክልልነት ጥያቄ ነበር ፤ ነገር ግን ያ ጥያቄ ተገቢው ምላሽ ሳያገኝ የክላስተር አደረጃጀት ተግባራዊ እየሆነ ነው ብለዋል።

የክልል ጥያቄው እንዳለ ሆኖ ከዚህ ቀደም የአዲሱ ክልል የርዕሰ መስተዳደር መቀመጫ ' አርባ ምንጭ ' ትሆናለች ተብሎ ሲነገር ቢቆይም አሁን ላይ ይህ አልሆነም ይህ ደግሞ በፖለቲካዊ አሰራር የተፈፀም የማታለል ተግባር ነው በሚል ከፍተኛ ቅሬታን አሳድሯል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን ላይ እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ጋሞ እራሱን ችሎ ክልል ይሁን የሚል ነው። ለዚህም ሃሳቡን የሚደግፉ በተለያየ መንገድ ሰላማዊ ተቃውሞ እያሰሙ ነው " ብለዋል።

ከዚሁ በ ' ጋሞ ዞን ' ካለው ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ " ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ " ለትላንት ነሐሴ 4 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርብም ሰልፉ በመከልከሉ ሳይደረግ መቅረቱን ለማውቅ ተችሏል።

ፓርቲው ፤ መንግሥት የጋሞ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለማቋቋም የተጠየቀውን የህዝብ ጥያቄ በመቀልበስ በክላስተር ክልል ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊ እንቅስቃሴ በማቆም ውሳኔውን መልሶ እንዲያጤን በሚል ነው የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው።

በሰልፉ ላይ የጋሞ ክልላዊ መንግስት ማቋቋምን በሚመለከት " ጋሞ ክልላችን አርባ ምንጭ ማዕከላችን ፤ የጋሞ ጥያቄ ክልል እንጂ ክላስተር አይደለም " የሚሉ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ታቅዶ ነበር።

የዞኑ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ግን ለህዝብ ሠላምና ደህንነት ሲባል የሰላማዊ ሰልፉ #እንዳልተፈቀደ ለፓርቲው በፃፈው ደብዳቤ በማሳወቁ ሰልፉ ሳይደረግ ቀርቷል።

ፓርቲው ከሰሞኑን ሁኔታ ጋር በተያያዘ መንግሥት ጥያቄ ለማፈን እየጣረ እንደሆነና አባላቱንም እንዳሰረበት ገልጿል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ስለ አዲሱ ክልል ምን ይላሉ ?

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ከቀናት በፊት ከአርባ ምንጭ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት አዲሱ ክልል ከምስረታው ጀምሮ የዞኑን ህዝብ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲደራጅ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

" የተሰጠን ከፍላጎታችን ጋር የማይመጣጠን ነው "  አቶ ብርሃኑ " አብረውን ለተደራጁ ህዝቦች ፍላጎት አክብሮት ሲባል መቀበል ይኖርበናል " ሲሉ ገልጸዋል።

የክልሉን ህግ አውጪ ጨምሮ ግዙፍ  እና ብዙ ተገልጋይ ያሉዋቸው ተቋማት መቀመጫቸውን አርባምንጭ ከተማ ማድረጋቸውን ያብራሩት አቶ ብርሃኑ ተቋማቱ የአከባቢውን የመልማት አቅም እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት  ያሳድጋሉ ብለዋል።

የዞኑ ነዋሪችም መቀመጫቸው አርባምንጭ ከተማ እንዲሆኑ የተመደቡ ቢሮዎችን ለመቀበል ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከጋሞ ዞን ባገኘው መረጃ ዛሬ የዞኑ ምክር ቤት የአዲሱ ክልል " ረቂቅ ህገመንግስት " ላይ ሲመክር ውሏል። በተጨማሪ በከተማ እና በወረዳ ደረጃ ውይይቶች ሲደረጉ መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia