TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
«የሀገረ ሰላም ተፈናቃዮች #በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ተጠልለዋል፤ ቤተርስትያናቸዉ የተቃጠለባቸዉ ዲያቆናትም ይገኙበታል»

በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን የተከሰተዉን ግጭት ተከትሎ ከ 470 በላይ ተፈናቃዮች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ቦሬ ከተማ ተጠልለዉ እንደሚገኙ ተፈናቃዮች እና የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/HG-07-22-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች የቀረበ ጥሪ !

የ " ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር " በድርቅ ምክንያት ለጉዳት የተጋላጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ከቅርብ አመታት ወዲህ በደቡባዊና ደቡብ ምስራቃዊ አካባቢዎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰውና በእንስሶች ላይ ያስከተለውና እያስከተለ ያለው ጉዳት #እጅግ_አስከፊ መሆኑን ገልጿል።

ማኅበሩ እ.አ.አ በ2022 ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባባር ፦
- በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮና ጋሞ ዞኖች፣
- በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምስራቅ ጉጂ ዞኖች፣
- በሶማሌ ክልል ሸበሌ፣ ፋፈን እና አፍዴር ዞኖች ከዚህ በተጨማሪ ሞያሌ አካባቢ በድርቅ አደጋ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ 14,530 አባዎራዎችን ህይወት ለመታደግ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በተለይም #በኦሮሚያ እና #ሶማሌ ክልሎች እንዲሁም ሞያሌ አካባቢ በ206.3 ሚሊዮን ብር መሰል ድጋፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው።

ድርቁ በሰውም ሆነ በእንስሶች ላይ እያስከተለ ካለው ጉዳት አንፃር እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ማህበሩ የተጎጂዎችን ህይወት ለመታደግ እያደረገ ያለውን ጥረት መላው ኢትዮጵያውያን በአይነትም ሆነ በገንዘብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።

እንዴት ድጋፍ ማድረግ ይቻላል ?

1ኛ. #የአይነት_ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አዲስ አበባ ስቴዲየም አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ዋና መ/ ቤት ግቢ ድረስ በማምጣት መለገስ ይችላሉ።

2ኛ. የገንዘብ ልገሳ ማድረግ የሚፈልጉ በ #ቴሌ_ብር ሂሳብ ቁጥር 0907 ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ።

3ኛ. ለቦረና ድርቅ ምላሽ ተብሎ በተከፈት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 👉 1000529766916 እንዲሁም 907 አጭር የሂሳብ ቁጥርን በመጠቀም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በዳሽን ባንክ፤ በአቢሲኒያ ባንክ፤ በአዋሽ ባንክ እና በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

4ኛ. የእጅ ስልክ በመጠቀም በ9400 ላይ OK ብሎ በመላክ 1 ብር መለገስ ይቻላል።

#EthiopianRedCrossSociety
#ETHIOPIA🇪🇹

@tikvahethiopia