#SUDAN
ዛሬም ድረስ አሸናፊም ሆነ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ያልተገኘለት የጎረቤት ሀገር ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት አራት ወራት ሊያስቆጥር ተቃርቧል።
በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ24 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህ ማለት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዜጎች ውስጥ ግማሹ ያህሉ የምግብ እና ሌሎች ዕርዳታ እንዲፈልጉ አድርጓቸዋል።
ነገር ግን በአሰቃቂው ጦርነት እና የገንዘብ ድጋፍ እጦት ምክንያት 2.5 ሚሊዮን ዜጎች ብቻ ናቸው ድጋፍ ያገኙት ተብሏል።
እንደ ተመድ መረጃ ድጋፍ ከሚፈልጉ ዜጎች 14 ሚሊዮኑ ህፃናት ናቸው።
በአጠቃላይ እስካሁን በጦርነቱ ከ3000 የሚልቁ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ6000 በላይ ተጎድተዋል ፤ ሚሊዮኖችም ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚም ክፉኛ ተጎድቷል፣ የዜጎች ደህንነትም ጠፍቷል።
ተመድ ፤ በጦርነቱ ምክንያት በሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም ከአጠቃላይ ድጋፍ ፈላጊው መድረስ የቻለው ለ2.5 ሚሊዮኑ ብቻ ነው ፤ አሁን ላይ ሱዳን እጅግ አደገኛ ከሚባሉ ቦታዎች መካከልም መድቧታል።
በሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አልቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሽ በሚባለው ኃይል መሪ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰው ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ነበር ዛሬም ድረስ አንዱ አሸናፊ ሳይሆን የሰላም መፍትሄም ሳይገኝ ሀገሪቱ የከፋ ውድቀት ውስጥ እንደገባች ቀጥላለች።
@tikvahethiopia

#ኢትዮጵያ
" ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ይቁሙ "
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚታዩ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ።
ይህን ጥሪ ያቀረበው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው።
ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በንግግርና በምክክር መፍታት ሲገባ በተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ ወገኖች እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች የሀገራችን ኢትዮጵያን ደህንነትና ህልውና በመፈታተን ላይ መጥተዋል ሲል አሳውቋል።
ኮሚሽኑ " የተቋቋምኩበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረኩ ባለሁበት በዚህ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሥራዬን አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ " ብሏል።
የኮሚሽኑ ምክር ቤት ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ባደረገው ልዩ ስብሰባ በመላው ሀገራችን የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆመው የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አሉን የሚሏቸውን ልዩነቶች ወይም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ አቅርቧል።
ለዚህም ተግባራዊነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለድርሻ አካላትን በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየትና ለማመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን ያ
አሳውቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" ዳግም #ሞት እና #ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " - የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ተማጸነ።
" ዳግም ሞት እና ውድመት ውስጥ መግባቱ ይቅርብን " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
ጉባኤው በላከልን መግለጫ ጦርነት ለየትኛውም አይነት የፖለቲካዊ ችግር መፍትሔ ሆኖ አያውቅም ብሏል።
" ፖለቲካዊ ችግር መፈታት ያለበት መከባበር ባለበት የጋራ ጥቅም በሚያስቀድም ሁኔታ በሚደረግ የፖለቲካ ውይይት ነው " ያለው ጉባኤው ፤ " ውይይቱ ፦
- ብሶት የወለዳቸውን ምሁራንን፣
- የሀገር ሽማግሌዎችን፣
- የሃይማኖት አባቶችን፣
- ወጣቶችን እና ሴቶችን ጭምር ያካተተ ቢሆን የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ሙሉ እምነታችን ነው " ሲል ገልጿል።
ይህ እንዲሆን የመንግሥት #የፖለቲካ_ፈቃደኝነት በጣም አስፈላጊ እንደሚሆን አመልክቷል።
ምክንያቱም " መንግስት ከሁሉም በላይ እኛ በብዙ መልኩ ወንድማማችና እህትማማች የሆነውን ኢትዮጵያውያንን በጋራ የማምጣት አቅም አለው ብለን ስለምናምን ነው " ሲል ገልጿል።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚሁ መግለጫው ፤ በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ጦርነት ባስቸኳይ እንዲቆምና በውይይት ችግሮች እንዲፈቱ መንግስትንና ተፋላሚ ወገኖችን አጥብቆ ተማጽኗል።
" በዚህ በፍልሰታ ጾም ጸሎት ወቅት ልቦናችንን ወደ እግዚአብሔር እንድንመልስ ፤ ስለ ሰላም ፣ ፍትህ፣ ውይይት እንድንጸልይ ለምዕመኖቻችንና በጎ ፊቃድ ላላቸው ወገኖቻችን ሁሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደሴ ፣ ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርገው የቅዳሜ እና እሁድ በረራዎች የተሰረዙ መሆኑን አሳውቋል። ወደተጠቀሱት አካባቢዎች ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ በረራዎቹ እንደተመለሱ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። @tikvahethiopia
#Update
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ፦
- ደሴ (ኮምቦልቻ)
- ጎንደር
- ላሊበላ
- ባህርዳር የሚደረጉ በረራዎች #የተሰረዙ መሆናቸውን አሳውቋል።
ወደሥፍራው ለመጓዝ ትኬት የቆረጡ ደንበኞቹ ትኬታቸው ለአንድ (1) ዓመት ያህል የሚያገለግል መሆኑን አውቀው ወደፊት በፈለጉበት ቀን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ መቀየር የሚችሉ መሆኑን ገልጿል።
ነገር ግን ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉ ደንበኞቹ አቅራቢያቸው ወዳሉ የአየር መንገዱ የትኬት መሻጫ ቢሮዎች ወይንም የጉዞ ወኪሎቻቸው በመቅረብ መስተናገድ እንደሚችሉ አሳውቋል።
አየር መንገዱ በዚህ ረገድ ለሚፈጠረው መጉላላት ይቅርታውን አቅርቧል።

Aspiring women entrepreneurs, this is your golden moment to realize your entrepreneurial dreams! Apply for the Jasiri Talent Investor Cohort 5 at https://jasiri.org/application to find your co-founder and build the business venture you've been dreaming of. #Jasiri4Africa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቴሌብር ስኩልፔይ
በአዲሱ የትምህርት ዘመን፤ ለትምሕርት ተቋማት፣ ለተማሪዎች እና ለወላጆች የቀረበ ልዩ መላ!
ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#WFP
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው እርዳታ በተወሰነ መልኩ ማቅረብ መጀመሩ ተገለፀ።
በተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ ኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ እርዳታ ከአምስት ወራት ብኋላ እጅግ አነስተኛ በሚባል መልኩ እርዳታ መላክ መጀመሩን " አሶሸትድ ፕሬስ " ገልጿል።
ድርጅቱ ለአሶሸትድ ፕሬስ እንደገለፀው ፤ በትግራይ 4 አካባቢዎች በመቶ ሺህ እርደታ ፈላጊ ዜጎች ላይ አዲሱ የተቋሙ አሰራር ትግበራ ሙከራ በሐምለ መጨረሻ መጀመሩን አሳወቋል።
የተለያዩ ተቋማት ፣ ሃይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ አካላት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለተቸገሩ ወገኖች ሲያቀርብ የነበረው እርዳታ ማቋረጡን ተገቢ አለመሆኑ እና ከሞራል አንፃር ኢሞራላዊ ነው ብለው ሲተቹት እንደነበር ያወሳው ዘገባው በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ በምግብ እጦት ምክንያት በትግራይ የሞት አደጋ ማጋጠሙን አስታውሷል።
የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት / USAID ኃላፊ የሆኑት ሳማንታ ፓወር በበኩላቸው ፤ " ተፈጠሩ የተባሉ ችግሮችን በማጣራት እንዲሁም እርዳታው ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በትክክል መድረሱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው " ያሉ ሲሆን የሰብአዊ እርዳታው በአጭር ግዜ ለማስጀመር ጥረት ይደረጋል ማለታቸው ተዘግቧል።
ከአምስት ወራት በፊት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለኢትዮጵያ ሲያቀርበው የነበረው የሰብአዊ ድጋፍ ስርቆትና ላልተገባ ተግባር ውሏል በመባሉ እንዲቆም መደረጉን የሚታወስ ነው።
መረጃው የድምፂ ወያነ ነው።

Photo
#AddisAbaba
" ግለሰቡ ህፃናቱን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የ ' ግብረሰዶም ወንጀል ' የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገለፀ።
የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው በክ/ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5 ፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል።
ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
ይህንን ተከትሎ ሌሎቹ 2 ህፃናትም ተመሳሳይ ድርጊት እንደፈፀመባቸው በመግለፃቸው በ3 የምርመራ መዝገቦች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡
መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በሰው እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ በ19 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
ህብረተሰቡ ከህግ እና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
#ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፁም የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት ይችላል ሲል ፖሊስ ገልጿል።

(ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ) " የስራ ሀላፊነትን በፈቃድ ስለመልቀቅ ! በ2011 ዓ.ም ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ስራዬን ስጀመር ተቋማችንን ተአማኒ እና ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ በማለም ነበር። ባለፉት አራት አመት ከስድስት ወራት ሶስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ሃላፊነቶች…
ወ/ሪት ብርቱካን ሽኝት ተደረገላቸው።
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ያሳወቁት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ሽኝት ተደረገላቸው።
ወ/ሪት ብርቱካን ፤ ጤናቸውን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ከነሀሴ 1/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ለተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ማሳወቃቸው አይዘነጋም።
ፎቶ፦ NEBE

Audio
#Gondar
የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል።
የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል።
በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ መድሃኒት ቤት ከመድሃኒት ውጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጿል።
" የከባባድ መሳሪያ ድምጾች ከሆስፒታሉ ውስጥ ሆነን ይሰማን ነበር " ያለው ዶክተሩ ላለፉት ቀናት ከተማዋ በተኩስ ስትናጥ መቆየቷን አመልክቷል።
እስከ ትላንት ሰኞ ከሰዓት ድረስ በግጭቱ ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ወደ ሆስፒታል የሚያመላልስ እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ አንድ አምቡላንስ ብቻ እንደነበር እሱም በሚያስዝን ሁኔታ ዒላማ መደረጉን የጎንደር ሆስፒታል ዶ/ር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።
የንፁሃን ነዋሪዎች ጉዳይ ትኩረት የሚሻው መሆኑን አስገንዝቧል።
(ድምፅ ዛሬ ጥዋት ላይ የተቀዳ)