TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አማራ ክልል‼️

በአማራ ክልል የትራፊክ ደህንነት መቆጣጠሪያ ህግን #በመቃወም የትራንስፖርት አገልግሎት #ተስተጓጉሏል፡፡

የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ውቤ አጥናፉ ለኢዜአ እንደገለጹት የትራንስፖርት አገልግሎቱ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ተስተጓጉሏል።

በተለይም ከባህር ዳር አዊ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃምና በእነዚህ መስመሮች ያሉ የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ ህዝቡ መጉላላት እየደረሰበት መሆኑን ተናግረዋል።

ለአገልግሎቱ መቋረጥም ከጥር 1/2011 ዓ.ም. ጀምሮ ይተገበራል የተባለውን የ "ኤስ ኤም ኤስ" የትራፊክ ደህንነት መጠበቂያ ህግ በመቃወም እንደሆነ አመልክተዋል።

ሆኖም የቅድመ ዝግጅትና የስልጠና ስራዎች #ባለመጠናቀቃቸው ህጉን ተግባራዊ ማድረግ #እንዳልተጀመረ ጠቁመው፥ "ይህን #ሰበብ አድርጎ አገልግሎት ማቋረጥ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።

በህጉ ዙሪያ ለአስፈፃሚ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠት መጀመሩን አመልክተው በቀጣይ ለአሽከርካሪዎች፣ ለባለሃብቶችና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠርና የማሳወቅ ስራ በማከናወን እንደሚተገበር አስታውቀዋል።

ህግ የሚወጣው የአብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ደህንነት ለመጠበቅ እንጂ የተወሰኑ ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት እንዳልሆነ ተናግረው ህጉ አሁን በሰው ህይወት እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመቀነስ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

አሁን ችግሩን ለመፍታትና አገልግሎቱን ለማስጀመር ከአሽከርካሪ ማህበራትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የዓባይ መደበኛ ደረጃ አንድ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዓባይነህ ማህሪ በበኩላቸው ለትራንስፖርት አገልግሎቱ መቋረጥ ማህበሩ እውቅና እንደሌለው ገልጸዋል።

የ"ኤስ ኤም ኤስ" ህግን በሚመለከት ቀደም ሲል ውይይት ማድረጋቸውን አስታውሰው፤ ሆኖም ይተገባራል የሚል መረጃ እንደሌላቸውና ሙሉ እውቅና ያልተፈጠረበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

አሽከርካሪዎቹ አገልግሎት እንደማይሰጡ ያሳወቀ አካል እንደሌለ የገለጹት ደግሞ የዘንባባ ደረጃ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ አፈወርቅ ናቸው።

"ገና ይተገባራል የሚባለውን የኤስ ኤም ኤስ የቅጣት ሪከርድ ህግ ቀድሞ በመፍራት የስራ ማቆማ ተገቢ አይደለም ፤በዚህ የተነሳም ህዝብ መጉላላት የለበትም" ብለዋል።

በአማራ ክልል 61 የአሽከርካሪ ማህበራት ያሉ ሲሆን ሰባት ሺህ 300 አገልግሎት የሚሰጡ መለስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች እንዳሉም ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia