TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢህአዴግ ጉባኤ ሀዋሳ⬇️

የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች በድርጅቱ ስራ አስፈፃሚና ምክር ቤት ውስጥ እንዲሳተፉ በ11ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ላይ ተወሰነ።

የአጋር ድርጅቶች ሊቀመናብርትና ምክትል ሊቀመናብርት በቀጥታ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲሳተፉ ተወስኗል።

እንዲሁም የአጋር ድርጅቶቹ አምስት የስራ አስፈፃሚ አባላት በኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲሳተፉም ነው ጉባዔው #ውሳኔ ያስተላለፈው።

የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት አቶ ፍቃዱ ተሰማ፥ የአጋር ድርጅቶቹ የሚሳተፉት #ያለድምፅ መሆኑን ተናግረዋል።

አጋር ድርጅቶቹን ወደ ሀገራዊ መድረክ ለማምጣትና አንድ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት በጥናትና እውቀት ላይ ተመስርቶ ውይይት በማድረግ ወደ ኢህአዴግ የመቀላቀሉ ሂደት እንዲጠናቀቅ ጉባዔው ለኢህአዴግ ምክር ቤት ውክልና ሰጥቷል።

ጉባዔው በህግ የበላይነት መከበር ፣ በልማት ስራዎች፣ በወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚነት ላይም ከመቼውም ጊዜ በተሻለ እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጡ ተገልጿል።

ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተጀመረው የዲፕሎማሲ ስራም ብሄራዊ ጥቅምን በሚያስጠብቅ መልኩ ተጠናከሮ ይቀጥላል ተብሏል።

በየአካባቢው አየተስተዋለ ያለው መፈናቀልና ሰብዓዊ መብት ጥሰት በምንም መልኩ ድርጀቱ እንደማይታገስም አቶ ፍቃዱ በመግለጫቸው አመልክተዋል።

ለዚህም የፀጥታ አካላት ተገቢውን #እርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ እንደተቀመጠም ነው የጠቆሙት።

የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ለማስቀጠል የመንግስት ተቋማት ሪፎርም እንዲደረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል።

በተለይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚያሰፉ ገለልተኛና ወገንተኝነታቸው ለህዝብ የሆኑ ተቋማት ለመገንባት የሪፎርም ስራዎች በአፋጣኝ
ተግባራዊ እንዲሆኑ ጉባዔው አሳስቧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia