TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማስታወቂያ📌ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬇️

ቀን 05/13/2010 ዓ.ም

በ2010 ዓ/ም ሁለተኛው ወሰነ ትምህርት የ3ኛ ዓመት የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየተገበረ ባለው ስርዓተ ትምህርት መሰረት ‘Holistic‘ ፈተና አንፈተንም ማለታቸውን ተከትሎ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት ጥፋተኛ በመባላቸው በቴክኖሎጅ ተቋም ሴኔት ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ ከተማሪ ወላጆች እና ከተማሪዎች ህብረት ጋር በተደረገ ተከታታይ ውይይት መሰረት ተማሪዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ መነሻነት ዩኒቨርሲቲው የይግባኝ አቤቱታውን ተመልክቶ የሚከተሉትን ውሣኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታ መታገድ የሚለው #ቅጣት በመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ #ተሻሽሎ ተማሪዎች ወደ መደበኛ ትምህርታቸው እንዲመለሱ፣

2. በ2010 ዓ/ም የ2ኛው ወሰነ ትምህርት ያልተፈተኑትን #ማጠቃለያ ፈተና ተቋሙ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሠረት እንዲፈተኑ፣

3. በ2011 ዓ.ም የሚሰጠው ‘’Holistic‘’ ፈተና ተቋሙ ባፀደቀው ስርዓተ ትምህርት እና የአካዳሚክ ህግ መሠረት በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ እንዲፈተኑ፣

ስለሆነም የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የቴክኖሎጅ ተቋም ተማሪዎች ይህን ውሣኔ አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እየገለጽን የመግቢያ ጊዜውን በጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ደብዛው የጠፋው ጋዜጠኛ⬇️

የቱርክ ፕሬዚዳንት #ጣይብ_ኤርዶሃንና የሳዑዲው ንጉስ #ሳልማን_ቢን አብዱልአዚዝ ደብዛው በጠፋው ጋዜጠኛ ጉዳይ ላይ በስልክ #ተወያዩ

ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ከሁለት ሳምንት በፊት ቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ኮንስላ ጽህፈት ቤት ጉዳይ #ሊያስፈፅም እንደገባ ደብዛው ከጠፋ 13 ቀናት ተቆጥረዋል።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶሃንና የሳዑዲው ንጉስ ሳልማን ትናንት ሌሊት በስልክ ባደረጉት ውይይት የጋዜጠኛው መጥፋት ጉዳይ አጀንዳቸው ነበር ተብሏል።

ኤርዶሃን በጀማል ካሾጊ ጉዳይ ላይ ጥምር ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ እንዲካሄድ በአፅንኦት መናገራቸው ተሰምቷል።

ካሾጊ በሳዑዲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በነበረበት ወቅት 10 ሳዑዲዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት በሁለት አውሮፕላኖች ወደ ኢስታንቡል በማምራት ጽህፈት ቤቱን በተመሳሳይ ቀን መጎብኘታቸውን የቱርክ ፖሊስ መረጃዎች ያሳያሉ።

የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አምደኛ የሆነው የሳዑዲ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ የት እንደገባ አለመታወቁን ተከትሎ ቱርክ፣ አሜሪካ እና ብሪታኒያ ከሳዑዲ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቱርክ ጋዜጠኛው #መገደሉን የሚያሳዩ መረጃዎችን አግኝቻለሁ እያለች ነው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት ጋዜጠኛው በቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ውስጥ መገደሉ ከተረጋገጠ ሳዑዲ ከባድ #ቅጣት ይጠብቃታል ብለዋል።

ይህን ተከትሎም ሳዑዲ በሰጠችው ምላሽ ማንኛውም ሀገር በጀማል ካሾጊ ጉዳይ ሀሰተኛ ውንጀላ የሚያቀርብ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የሚያስብ ሀገር ካለ የአፀፋ ምላሽ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።

ምንጭ፦ አናዶሉና ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ‼️

ድሬዳዋ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት የተከሰተው የወጣቶች ጸብ ከኃይማኖት ጉዳይ ጋር የማይገናኝ መሆኑን የከተማዋ የኃይማኖት አባቶች ተናገሩ፤ ግጭቱን የፈጠሩ አካላትም ተገቢውን #ቅጣት እንዲያገኙ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

የክርስትናና የእስልምና ኃይማኖት አባቶች ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ የሁለቱ እምነት ተከታዮች ለበዓሉ ድምቀትና ማማር ተቀናጅተው የሚያኮራ ሥራ መስራታቸውን ገልፀዋል፡፡

የድሬዳዋ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ሊቀ-ብርሃናት ቀለመወርቅ ቢምረው ግጭቱን የፈጠሩት ድብቅ ፍላጎት ያላቸው አካላት እንጂ ከኃይማኖት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አስረድተዋል።

“ታቦቱ ከገባ በኋላ ታቦቱን ያጀበው ሰረገላና ወጣቶች ላይ ከድብቅ ስፍራ ድንጋይ ተወረወረ፤ ወጣቱ ድንጋይ ወደ ተወረወረበት በመሄድ ጸቡ ተፈጠረ” ብለዋል።

ያጠፋና አካል በሰማያዊም ሆኑ በምድራዊው ህግ እንደሚዳኝ ገልጸው በተከሰተው ግጭት በቤተክርስቲያናት ላይ ምንም አይነት ጥፋት አለመድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ኃላፊ ሼህ ኢብራሂም ኢማም አህመድ በበኩላቸው በከተማው የኃይማኖት ተቋማት ለሰላም መስፈን፤ ለኃይማኖታዊ በዓላት መድመቅና ማማር በጋራ የሚሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ቀናትም ተመሳሳይ ሥራ መስራቱን ተናግረው በዓሉ በደመቀ መንገድ በተጠናቀቀበት መጨረሻ ሰዓት የተፈጠረው ችግር የተደበቀ ዓላማ ያነገቡ አካላት የፈጠሩት ሴራ ያስከተለው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡  

ድርጊቱን አውግዘው ፣ የተፈጠረው ግጭት ከኃይማኖት ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር አለመኖሩን ሼህ ኢብራሂም ገልፀዋል፡፡

“በዚህ ጥፋት የተሳተፉ ሰዎች ታድነው ለህግ መቅረብ አለባቸው፤ በግርግር ውስጥ ዘረፋ የፈፀሙ ሰዎችም ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ይገባቸዋል”ብለዋል፡፡

“ከሁሉም በላይ ወጣቶች መቼም ቢሆን ባልተረጋገጠ አሉባልታ ከመመራት እራሳቸውን መጠበቅ አለባቸው” ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ባለፉት ሶስት ቀናት የከተራና የጥምቀት በዓል ፍፁም ሰላማዊና አስተማማኝ እንዲሆን የሁለቱ እምነት ተከታዮች ተቀናጅተው ሰርተዋል፡፡

“ትላንት ማምሻውን የእግዚአብሔር አብ ታቦት ወደ ማደሪያ ከገባ በኋላ ታቦቱን ባጀበው ሰረገላና ሰረገላውን ባጀቡት ወጣቶች ላይ ድንጋይ ተወርውሮ ችግሩ መቀስቀሱን ፖሊስ አረጋግጧል” ብለዋል፡፡

የተፈጠረው ትንኮሳ በአብዛኛው የኃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ቁጣ መፍጠሩንና አስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ድረስ ወጣቶች በድንጋይ ሲጣሉ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

በአሁን ሰዓት የፀጥታው ኃይል ችግሩን ተቆጣጥሮ የማረጋጋት ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጸው “በግጭቱ የሰው ህይወት አላለፈም፤ ከፍተኛ ጉዳት አልደረሰም፤ የተጎዳ አንድም ቤተክርስቲያን የለም”ብለዋል።

ግጭቱ እንዲቀሰቀስ ያደረጉና ጥፋት ያደረሱ አካላትን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ በፖሊስ የተቀናጀ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

መሰል ጥፋት ባነገቡ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በሚደርገው ጥረት ህብረተሰቡ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የሲቲ ዞን የበርበርታ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት ጣሂር ፋራህ ሰመሬ በበኩሉ በበዓሉ ላይ የተፈጠረው ድርጊት የሚወገዝና የድሬዳዋ መገለጫ አለመሆኑን ተናግሯል።

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia