TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚከናወን ተገለፀ። ቋሚ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ተፈፅሟል ባለው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንደሚካሄድ አመልክቷል። " በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን…
ፎቶ፦ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፍቷል።

" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን በጸሎት ጀምሯል " ሲል የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል የተጠራውና ዛሬ በፀሎት የጀመረው አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ነገ ጠዋት በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የቤተክርስቲያኗን ቀኖናትና ሕግጋት የሚያስከብሩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሏል።

መረጃ እና ፎቶ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
#Tigray

" ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ " በትግራይ ትምህርት ቤቶች ያላውን የጥቁር ሰሌዳ ችግር ለመፍታት አበረታች ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፋብሪካው ያለበት የጥሬ እቃ ግብአት እጥረት ሳይገድበው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለክልሉ ትምህርት ቤቶች የሚሆን ጥቁር ሰሌዳ በመስራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

ፋብሪካው የኬሚካልና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች እጥረት ቢኖርበትም 50 በመቶ የማምረት አቅሙ ችፑድ ላይ በማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የእቅድና ማህበራዊ ልማት ካብኔ ሴክሬታሪያት ፕ/ር ክንደያ ገ/ሂወት ገልፀዋል፡፡

የ " ማይጨው ችፑድ ፋብሪካ " ባዮማስን የሐይል ምንጭ አድርጐ ለመጠቀም እያደረገ ያለው ጥረትን ጨምሮ ወደ ነበረበት የማምረት አቅም ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረትና ተነሳሽነት የሚመሰገን መሆኑንም ፕ/ር ክንደያ በትዊተር ገፃቸው አስነብበዋል፡፡

በትግራይ በአስከፊው ጦርነት ምክንያት እጅግ በርካታ የትምህርት ተቋማት መውደማቸው ይወሳል። በርካታ ትምህርት ቤቶች በግብአት እጥረት የመማር ማስተማር ፈተና እንደሆነባቸው ይገኛል።

#ትግራይ_ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
#MoE

በ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም እንደማይኖር ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ዛሬ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ፤ የ2015 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ፕሮግራም እንደማይኖር ገልጿል።

"በተለያዩ ምክንያቶች ባለፉት ዓመታት የተዛነፈውን የትምህርት ካሌንደር ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማስተካከል እየሠራ እንደሚገኝ" ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በዚህም በቀሪው አንድ ወር የክረምት ትምህርትን ማስቀጠል የማይቻል መሆኑን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤ ጠቁሟል።

በመሆኑም ጊዜውን ማራዘም እንዲስተካከል እየተሠራ ያለውን የትምህርት ካሌንደር መልሶ የሚያዛባ በመሆኑ የ2015 የክረምት ትምህርት የማይኖር መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

(ደብዳቤው ከላይ ተያይዟል።)

More : @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የሬሜዲያል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም በኦንላይን እንደሚወስዱ አሳውቋል።

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ (50%) ሳያመጡ የቀሩ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው የማካካሻ ትምህርት ፈተናን ከሰኔ 26-30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከተፈታኝ ተማሪዎች እና የማካካሽ ትምህርቱን ከሚሰጡ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቁጥር አንፃር እንዲሁም በወቅቱ በተከሰተው ችግር ምክንያት በሁለት የመንግስት እና በ143 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ተማሪዎች የሪሜዲያል ፈተናውን ለመስጠት ባለመቻሉ በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ፈተናውን እንዲወስዱ ተወስኖ ነበር፡፡

ሚኒስቴሩ በቅርቡ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቦርድ አባላት ጋር ጉዳዩን አስመልክቶ ባደረገው ውይይት እና በተደረሰው ስምምነት መሰረት ፈተናው ከነሐሴ 23 – 26 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ተወስኗል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፦

- ፈተናው #በበይነ_መረብ እንዲሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ አብዛኞቹ ተማሪዎች ግን የኮምፒዩተር ክህሎት ስለሚያንሳቸው እያንዳንዱ ተቋም ከወዲሁ ተማሪዎቹን በማሰልጠን የማብቃት ስራ እንዲሰራ፣

- ተፈታኞች የ #ፊዚክስ እና የ #ታሪክ ኮርሶች በሪሜዲያል ፈተና ውስጥ እንደማይካተቱ አውቀው በሌሎች ትምህርት ዓይነቶች ላይ አተኩረው ዝግጅት እንዲያደርጉ እንዲደረግ፤

- ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ፈተናውን የሚወስዱበት ተቋም ወይም ቦታ በመለየት ከተፈታኝ ተማሪ ቁጥር ጋር በቶሎ እንዲያሳውቁና ተማሪዎቹ ከዋናው ፈተና በፊት ልምምድና ከፈተና ሶፍትዌር ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ ሞዴል ፈተናዎችን እንዲፈትኑ ፤ ፈተናው የሚሰጥባቸው ከየመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችም ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተሮችን ለዚህ ስራ ዝግጁ በማድረግ ጠንካራ ክትትል እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

(በዶ/ር ኤባ ሚጄና - የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ተፈርሞ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ ለሐረር መምህራን ኮሌጅ የተላከው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

More : @tikvahuniversity

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል ሁለተኛው ቀን መርኃግብር ዛሬም ይቀጥላል!

ዛሬ በሚኖረን መርኃግብር፦

#በአዳማ ፦ "Hade Sinquee
📍በኦሊያድ ሲኒማ 🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።

#በባህርዳር ፦ " I Love You Too ብለው በሳቅ ገደሉኝ" እና "የእኔን ልጅ ሊገል አስቦ ስላልወጣ የልጄ ምትክ አድርጌዋለሁ"
📍በሙሉዓለም አዳራሽ 🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።

#በአዲስ አበባ ፦  "አንድ ሰው" ፤ "ተላላፊ" ፤ "ወሬ ነው" እና "እሱ ለራሱ ነው እንጂ ለኢትዮጵያ አስቦ አይደለም" የተሰኙ 4 ዶክመንተሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።
📍በጣሊያን ባህል ማዕከል 🕒 ከ 11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በአካል ቀርበው ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቀረበ። ዩኒቨርሲቲው በጦርነት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል። በዚህም መሰረት ፦ - በ2013 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች - የድህረ ምረቃ ተማሪዎች - የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች - የሕክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች…
ፎቶ፦ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው እየተቀበለ የሚገኘው በ2013 ዓ/ም መመርቀ የነበረባችው ሆኖም በትግራይ ጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉ ተማሪዎቹን ነው።

ተቋሙ ተማሪዎችን እየተቀበለ የሚገኘው በዓይደር፣ አሪድ እና ቀላሚኖ ግቢዎች ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ቅበላው ይቀጥላል።

የተቀሩ ተማሪዎች በመጪው መስከረም 4 እና 5 /2016 ዓ/ም ወደ ተቋማቸው ይገባሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። የሐምሌ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከሰኔ 23 / 2015 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባለበት እንደሚቀጥል አስታውቋል። በዚሁ መሠረት ፦ 1. ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም 2. ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር…
የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሀምሌ ወር ሲሸጥ በነበረው ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት ፦

1. ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ52 ሳንቲም

2. ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር

3. ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ15 ሳንቲም

4. የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 65 ብር ከ35 ሳንቲም

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ97 ሳንቲም

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ63 ሳንቲም ይሸጣል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በመጪዎቹ ጊዜያት የአለም የነዳጅ ገበያን መነሻ በማድረግ አስፈላጊው #ማሻሻያ የሚደረግ መሆኑን አመልክቷል።

@tikvahethiopia
" ርዕደ መሬቱ በተከሰተባቸው አከባቢዎች እስከ አሁን ያጋጠመ አደጋ የለም " - አስተዳዳሪዎች

ከባድ ርእደ መሬት በኤርትራ ፣ ሱዳን እንዲሁም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ማጋጠሙ የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል።

ሃምሌ 25 /2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:15 ገደማ በእንዳስላሰ ሽረ ፣ ሰለኽለኻ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ውቕሮ ፣ ሓውዜንና አከባቢው ፣ ኣፅቢ ፣ መቐለና ሌሎች አከባቢዎች ከባድና ቀላል ርእደ መሬት ተከስተዋል።

የርእደ መሬቱ ዋና መነሻ (Epicenter) ከምፅዋ ወደብ በ43 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው አካባቢ ሆኖ ፤ ከባድና 5.6 ሬክተር ስኬል የሚለካ ነው።

ይህንን ከባድ ርእደ መሬት ደግሞ እስከ ዓዲግራት ፣ ዓድዋ ፣ ውቕሮ ፣ መቐለና ሌሎች አከባቢዎች ድረስ ተከስቷል

ርዕደ መሬቱ በተከሰተባቸው አከባቢዎች እስከ አሁን ያጋጠመ አደጋ እንደሌለ የትግራይ ቴሌቪዥን ያነጋገራቸው የክልሉ የሰሜን ምዕራብ ፣ ማእከላዊና ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪዎች ገልፀዋል።

የመረጃው ምንጭ ትግራይ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia