#ሩስያ #አፍሪካ
ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለሁለት ቀናት ጉባኤ ተቀምጠው የነበሩት የአፍሪካ መሪዎች፣ ከዩክሬን ለዓለም ገበያ እህል መቅረብ እንዲቀጥል ያቀረቡትን ጥያቄ በተመለከተ እንዲሁም በዩክሬን በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ አንዳች መፍትሄ ላይ ሳይደርሱ መበተናቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ቭላድሚር ፑቲን ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ ከዩክሬን እህል ወደ ዓለም ገበያ የሚቀርብበትን ስምምነት በዚህ ወር ማቋረጣቸው፣ የእህል ዋጋ እንዲጨምር አድርጎ የሩሲያ ኩባንያዎችን ተጠቃሚ አድርጓል ብለዋል።
ሞስኮ የተወሰነውን ትርፍ ከድሃ ሀገራት ጋር እንደምትጋራ ፑቲን ጨምረው ገልጸዋል።
ፑቲን በተጨማሪ ሩሲያ በአፍሪካ መሪዎች የቀረበውን የሰላም ሃሳብ ታጤነዋለች ብለዋል።
ከ25 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ቶን እህል ለስድስት አፍሪካ ሀገራት በነጻ እንደሚሰጥ ፑቲን ቀደም ብለው አስታውቀው ነበር። እነዚህም፤ ቡርኪና ፋሶ፣ ዚምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ናቸው።
ፑቲን ቃል የገቡት እህል መጠን የተመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም እህል ከዩክሬን በሚወጣበት ስምም ነት መሠረት ገዝቶ ረሃብ ለተጋረጠባቸው ሀገራት ካሰራጨው 725 ሺሕ ቶን እህል ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው ተብሏል።
54 ከሚሆኑት የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ውስጥ በጉባኤው የተሳተፉት 17 ብቻ ናቸው ፤ እ.አ.አ በ2019 በተደረገው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ 43 የአፍሪካ መሪዎች ተገኝተው ነበር።
የአሁኑ የተሳታፊዎች ቁጥር መቀነስ " በምዕራባውያን ግፊት የመጣ ነው " ስትል ሞስኮ እንደምትከስ ቪኦኤ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
" በተጠራው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የማይገኙ አባቶች ካሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በእነሱ ላይ የሚወስነውን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ ይኖርባቸዋል " - የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ሁሉም ብፁዓን አባቶች ሐምሌ 25 /2015 ዓ/ም ለተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በድጋሜ ጥሪውን አስተላለፈ። ቅዱስ ሲኖዶስ ፅ/ቤት ፤ በትግራይ ክልል በአክሱም ርእሰ አድባራት ወገዳማት…
#Update
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚከናወን ተገለፀ።
ቋሚ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ተፈፅሟል ባለው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንደሚካሄድ አመልክቷል።
" በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ተፈጽሞ በመገኘቱ አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲጠራ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል።
በዚህም ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ለሁሉም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጥሪ እንዲተላለፍ፣ 2ኛ የመክፈቻ ጸሎቱ ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በ10፡00 ሰዓት እንዲከናወን 3ኛ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲካሄድ ቋሚ ሲኖዶስ ወስናል።
በክልል ትግራይ ሚገኙ ብፁዓን አባቶች ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል በመነጠል የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት በሚል አቋቁመው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ማከናወናቸው ፤ ሃምሌ 15 እና 16 /2015 ዓ.ም እንዲሁም ሐምሌ 23 ደግሞ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ከዚህም በተጨማሪ፤ ዛሬ የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት በመቐለ ህዝባዊ አቀባበል እንደተደረገላቸው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ፤ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳዩ #ምስሎች ከላይ ተያይዘዋል።

#Jasiri
Are these statements resonating with you?
✅ I have an entrepreneurial spirit.
✅ I am skilled at identifying opportunities.
✅ I believe that, with the right support - a program tailored for me at the pre-idea stage, access to a pool of co-founders, a network of mentors, industry experts, and financial backing - I can focus my energy on building a venture from scratch to solve a pressing problem in our society.
However, despite this passion and belief, I'm unsure of where to start. 🤔
That's where the Jasiri Talent Investor comes in! If you're seeking the resources and guidance to turn your ideas into reality, apply today at https://jasiri.org/application

#ጥምረት
በጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በነገው ዕለት ለዕይታ የሚቀርበው ምንድን ነው ?
የተለያዩ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ለማሳይት የተዘጋጀው ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል በነገው ዕለት በይፋ ይከፈታል።
እርሶም ከሐምሌ 25 እስከ 28 ድረስ ለዕይታ በሚቀርበው የፊልም ፌስቲቫል በመረጡት ቀን ተገኝተው መታደም ይችላሉ።
ነገ የሚኖረን መርሐግብር ቻናላችንን በመቀላቀል ይመልከቱ 👉 https://t.iss.one/TimretEth
በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል።
#USAID #Prologue #bcw

ኤፈርት ላይ የተጣለው እግድ ተነሳ።
በትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) ስር የሚገኙ 21 ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ እንዲነሳ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መወሰኑን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።
ድርጅቶቹን በጊዜያዊነት ሲያስተዳድር የቆየው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ኃላፊነትም እንዲሻር ፍርድ ቤቱ አዝዟል።
እነዚህን ተደራራቢ ትዕዛዞች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 21፤ 2015 የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት ነው።
የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ትዕዛዞቹን ያስተላለፈው፤ ፍትሕ ሚኒስቴር በኤፈርት ስር ያሉ ድርጅቶች ላይ የተሰጠው ዕግድ እና በጊዜያዊነት የማስተዳደር ኃላፊነት እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው።
በጦርነት እና በድርቅ የተጎዳውን የትግራይ ክልል ኢኮኖሚ መልሶ የማሻሻል ዓላማን ይዞ በ1987 ዓ.ም የተመሰረተው ኤፈርት፤ በኮንስትራክሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግብርና፣ ማዕድን እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን በስሩ ሲያስተዳድር ቆይቷል።
ሱር ኮንስትራክሽን፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ፣ ጉና ትሬዲንግ፣ መሰቦ ሲሚንቶ እና አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ በኤፈርት ስር ከሚተዳደሩ ግዙፍ ድርጅቶች መካከል ይጠቀሳሉ።
በኤፈርት ስር ያሉ 34 ድርጅቶች የባንክ ሂሳብ እንዲታገድ የተደረገው፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በይፋ ከተቀሰቀሰ ሁለት ሳምንት በኋላ ህዳር 7፤ 2013 ነበር።
የፌደራል ጠ/ዐቃቤ ህግ እግዱን ያስተላለፈው፤ ድርጅቶቹ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ " ሽብርተኝነትን በገንዘብ በመደገፍ " ወንጀል በመጠርጠራቸው ምክንያት መሆኑ በወቅቱ ተገልጸ ነበር።
Credit : Ethiopian Insider

Photo
" ፈተናው ከ #ብሉፕሪንቱ_ውጭ የሚሆንበት እድል በጣም በጣም አነስተኛ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር በመውጫ ፈተና ላይ ስለቀረቡት ቅሬታዎች ምን ምላሽ ሰጠ ?
የመውጫ ፈተና የወሰዱ ፦
- የመካኒካል ምህንድስና
- የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ
- የኢንሮሜሽን ቴክኖሎጂ ... ተማሪዎች ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በተለይም ፤ ተማሪዎቹ ፈተናቸው ከብሉፕሪንት ውጭ መሆኑን ፤ የተዘጋጀው ፈተና በእነሱ ደረጃ ያለን የዲግሪ ተማሪ ለመለካት የማይሆን፣ (የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ተማሪዎች) የተዘጋጀው ፈተና እና የተመደበው ሰዓት የሚመጣጠን እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ቅሬታዎቹን በዚህ ያገኛሉ (የተወሰኑ) ፦
https://t.iss.one/tikvahethiopia/79840?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/79739?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/79870?single
https://t.iss.one/TikvahUniversity/7740?single
ለቅሬታዎቹ ትምህርት ሚኒስቴር ምን ምላሽ ሰጠ ?
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ሚኒስትር ዴኤታ) ለፋና ቲቪ ከተናገሩት ፦
" የተማሪዎች ጥያቄ ደርሶናል ፤ አዎ!
አንዳንዶቹ ቅሬታዎች እና ጥያቄዎች የተነሱት ገና ፈተና እየፈተንን ስለሆነ፤ የተጠቀምነው ቴክኖሎጂ በየዕለቱ የፈተናቸው ፕሮግራሞች አማካይ የተመዘገበውን ለማየት ፤ በአማካይ የሚያልፈውን ተማሪ ለማየት ውስን ሰዎች ሁለት ሶስት ሰዎች የማናልፍ መረጃውን እናገኝ ነበር። ቅሬታዎቹ በልኩ መያዝ እንዳለባቸው እናውቃለን። ከቅሬታ አንፃር በየቀኑ እንቀበል ነበር።
ሁለተኛ ፈተናው ከብዷል ፤ ቀሏል ለማለት ደግሞ ፈተናው እንዴት እንደወጣ ላስረዳ።
አንድ የአግሪካልቸር ወይም የአካውንቲንግ ተማሪ በ4 / 5 አመት ቆይታው የመጀመሪያ ዲግሪ በአካውንቲንግ ሲይዝ ምን እውቀቶችን ፣ክህሎቶችንና ስነምግባሮችን መጨበጥ አለበት የሚል መለኪያ ተዘጋጅቷል / ለሁሉም 215 ፕሬጋራሞች / ።
እነኚህ ብቃቶች በምንድነው የሚለኩት ተብሎ ብሉፕሪንት ተዘጋጅቷል።
ብሉፕሪንቱን ተከትሎ ፈተና ተዘጋጅቷል። የተዘጋጀውን ፈተና ሌላ አካል ገምግሟቸዋል።
የብቃት አሃዶችን ማውጣት ፣ብሉፕሪንቱን ማውጣት በዛ መሰረት ፈተና ማዘጋጀት ፈተናው በብቃት አሃዱ በብሉፕሪንቱ መሰረት የተዘጋጀ ነው ብሎ ገምግሞ መልስ የሚሰራ ሶስት ሌላ አካል አለ።
በዚህ ሂደት ነው ያለፈው፣ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተና የማቅለልም ሆነ የማክበድ ሚና የለውም። ሚናው ለእያንዳንዱ ፕሮግራም 5ና 6 , 7 ፈተናዎች እንዲኖሩት ይፈልጋል። ከተዘጋጁት ፈተናዎች አንዱን ለሞዴል እኩሌታውን ደግሞ ለዋናው ፈተና ይጠቀማል። ፈተናው ከብሉፕሪንቱ ውጭ የሚሆንበት እድል የለውም።
ለእያንዳንዱ ፕሮግራም (215) ቢያንስ ሁለት ሁለት ፈተና ያወጣ ሰው አለ። ቢያንስ አንድ ሰው ፈተናውን ገምግሞ ለዚህ መቶ ጥያቄ መልሱ ይሄ ነው ብሎ የሰጠን መምህር አለ። ይሄን በስም የምናውቃቸው ፣ በስልክ ቁጥር ፣ በኮሌጅ ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስም እናውቃቸዋለን።
ከብሉፕሪንት ውጭ ፈተና ሊመጣ የሚችልበት እድል የለውም። እንደዛ ሊሆን የሚችለው ብሉፕሪንቱን ትቶ ፈተና ያዘጋጀ አካል ካለ ነው። ፈተናውን የሚረከበው ደግሞ ማሽን አይደለም ሰው ነው ፤ ብሉፕሪንቱን የያዘ ሰው የኛ ባለሞያዎች አሉ፣ የኛ የስራ ኃላፊዎች አሉ፣ እነሱ በብሉፕሪንቱ መሰረት የተዘጋጀ መሆኑን ተጨማሪ ውይይት ከተደረገ በኃላ ነው ፈተናውን የሚረከቧቸው።
ገምጋሚዎችም አሉ፣ ቢያንስ እያንዳንዱ ፈተና አንድ ገምጋሚ አለው ፤ 215 ፕሮግራሞች ፈተና ስንፈትን ወደ 430 ፈተና ያዘጋጁ መምህራን ነበሩ ከዩኒቨርሲቲ የመጡ፣ 215 ገምጋሚዎች ነበሩ። ከብሉፕሪንት ውጭ የመሆን እድሉ በጣም በጣም አነስተኛ ነው 0 ነው እያልኩ አይደለም ለእድልም እድል መስጠት ስለሚያስፈልግ።
ሌላው የቀላል ጥያቄ ፣ የመካከለኛ ጥያቄ እና የከባድ ጥያቄ ምጥጥን በብሉፕሪንቱ ላይ ተቀምጧል። በዚህ መሰረት መሆኑንም ገምጋሚው ቼክ ያደርጋል፤ እገሌ የሚባል መምህር ፈተና አዘጋጅቶ ሄደ ብቻ ሳይሆን ፈተናው የተዘጋጀው በብሉፕሪንቱ የቀላል፣ መካከለኛና ከባድ ጥያቄ ምጥጥን በስርዓቱ ተቀምጧል የሚል ግምገማ ያደርጋል።
ከዚህ አንፃር የተነሱ ፕሮግራሞች ነበሩ፣ መልሰን ያየናቸው ፕሮግራሞች አሉ። መልሰን ያየናቸው እንዲሁ እኛ አይደለንም መምህራኑን ጠርተን ቁጭ ብለን ፦
- የእርማት ችግር አለበት ወይ ? ሲስተሙ ተሳስቶ ነው ወይ ? የሚለውን ስናይ 0 ነው ለሁሉም ፕሮግራሞች 0 ነው ምንም እድል አላገኘንም።
- በብሉፕሪንት መሰረት ተዘጋጅቷል ወይ ? ለሚለው አዎ!
- የተባለው ጥያቄ ነው ወይ የመጣው ? በትክክል ምርጫ ነበረው ወይ ? እዚህ ላይ የተወሰኑ ጥያቄዎች ላይ መልሱ ይሄ መሆን ሲገባው ይሄ ተብሎ ተሰጥቷል ተብሎ በገምጋሚው ክርክር የተደረገባቸው ነበሩ እሱ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። ውጤቱን በጣም ኢምንት በሆነ ደረጃ ነው ሊቀይር የሚችለው።
የፈተና መክበድ እና መቅለል ከብሉፕሪንቱ ውጭ የመሆን እድል አነስተኛ ነው ፤ የለም እያልኩ አይደለም ። ቅሬታዎች ቀርበዋል አይተነዋል።
የተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ እኔ እራሴ በተገኘሁበት መምህራኑን አግኝተን የቀረበውን ቅሬታ አንስቼላቸው ይሄ ምን ሊሆን ይችላል ? መላምቱ ምን ሊሆን ይችላል ? ሲስተሙ በትክክል አላረመው ይሆን ? ጥያቄው በትክክል መልስ አልተሠጠ ይሆን ወይ ? ጥያቄው ከብሉፕሪንት አንፃር የተዘጋጀ ነው ወይ ? የሚለውን በዝርዝር አይተን አንድ ሁሉት ፕሮግራሞች ግማሽ ቀን የወሰደ ጊዜ ተሰርቶባቸው ሄዷል።
ትምህርት ሚኒስቴር መምህራኑን ያዘጋጁትን ፈተና ተገቢ ነው ብሎ ስለሚያምን ሞያተኛው የሰራውን ስራ መነካካት ተገቢ ነው ብሎ ስለማይቀበል በዛ መልኩ ሄደናል። "
#TikvahEthiopia

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 28 ድረስ በመረጡት ቀን ጥምረት የፊልም ፌስቲቫልን መሳተፍ ይችላሉ።
#በባህርዳር: 📍በሙሉዓለም አዳራሽ🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።
#በአዳማ: 📍በኦሊያድ ሲኒማ🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።
#በአዲስአበባ: 📍በጣሊያን ባህል ማዕከል🕒 ከ 11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።
በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል።
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 https://t.iss.one/TimretEth
ዛሬ የሚኖረን መርሐግብር ቻናላችንን በመቀላቀል ይመልከቱ 👉 https://t.iss.one/TimretEth
በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል።
#USAID #Prologue|bcw
#በባህርዳር: 📍በሙሉዓለም አዳራሽ
#በአዳማ: 📍በኦሊያድ ሲኒማ
#በአዲስአበባ: 📍በጣሊያን ባህል ማዕከል
በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል።
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉 https://t.iss.one/TimretEth
ዛሬ የሚኖረን መርሐግብር ቻናላችንን በመቀላቀል ይመልከቱ 👉 https://t.iss.one/TimretEth
በዚህ ዝግጅት ለሚሳትፉ #ሰርተፊኬት ይሰጣል።
#USAID #Prologue|bcw
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአቢሲንያ ባንክ ደሞዝ ለሚከፈላቸው ሰራተኞች ደሞዝ ባይደርስም ደሞዛቸውን ቀድመው መበደር የሚችሉበት አስደሳች ዕድል ከአቢሲንያ ባንክ! የአፖሎ የሞባይል መተግበርያን አሁኑኑ ያውርዱ!
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalbank
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#እገታ ከሰሞኑን ጎንደር ላይ አንድ እስራኤላዊ ዜጋ ታግቷል ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር። ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግሥት ዜጋውን ለማስለቀቅ ፍለጋ ጀምሮ ነበር። ነገር ግን ጎንደር ላይ ታግቷል ተብሎ የተነገረው ኤስራኤላዊ ጉዳይ ውሸት ሆኖ በመገኘቱ የእስራኤል ባለስልጣናት ፍለጋቸውን እንዳቋረጡ የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል። ጋዜጦቹ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ሀገራቸው…
#Update
የ79 ዓመቱ እስራኤላዊ ዜጋ በጸጥታ ኃይሎች ጥረት ከታገቱበት ተለቀቁ።
ከሦስት ሳምንታት በፊት አንድ እስራኤላዊ ዜጋ በኢትዮጵያ ታፍኖ እንደነበረ መረጃዎች ሲወጡ ቆይተዋል። ግለሰቡ ታግቷል በተባለበት ወቅት የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምንም የቀረበለት አቤቱታ አለመኖሩን አሳዉቆ ነበር።
የ 79 አመት አዛዉንት የሆኑት አቶ ውዱ አደባባይ መታፈናቸው ከተሰማ በኋላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግለሰቡ ሳይታገት ታግቻለው ስለማለቱ አረጋግጫለው ብሎ ከእገታ ለማስለቀቅ የሚያደርገውን ጥረት ማቆሙንም አስታውቆ ነበር።
ሆኖም አዛውንቱ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ማሬ መኳንንት የተባለ ግለሰብና ግብረ አበሮቹ ከሻሁራ ከተማ ወደ ፍንጅት ቀበሌ ጫካ ውስጥ በመውሰድ አግተው 1.5 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ድርድር ሲያደርጉ መቆየታቸውን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር ፈንታሁን አስፋው እንዳስታወቁት፥ ከአለፋ ወረዳ የፖሊስ አባላትና ከዞኑ የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በተደረገው የተቀናጀ ኦፕሬሽን የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነውን ማሬ መኳንንት በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንና 2 ግብረ አበሮቹ ለጊዜው ማምለጣቸውን አስታውቀዋል፡፡
የእስራኤል የዜና ምንጮች ደግሞ አጋቾቹ እስራኤላዊውን ዜጋ አግተው ወደ 2.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ($45,000) መጠየቃቸውን ጠቅሰዋል። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገታው የውሸት መሆኑ መግለጹም ስህተት እንደነበር ነው ያስነበቡት።
ሰኞ ዕለት ከእገታ የተለቀቁት አቶ ውዱ አደባባይ በአሁኑ ወቅት በጎንደር ከተማ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ጋር የተገናኙ ሲሆን ግለሰቡ ዛሬ ማክሰኞ ወደ እስራኤል ይበራል ተብሎ ይጠበቃል።
Via @tikvahethmagazine

" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa6.ministry.et/#/result ወይም በ @G6MinistryResultQMTBot " መመልከት ይችላሉ " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የተሰጠው የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።
ከ28 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቻ የተሰጠው ከተማ አቀፉ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።
ዘንድሮ ፈተናውን 73,667 ተማሪዎች የወሰዱ ሲሆን 50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ 7ኛ ክፍል እንዲዘዋወሩ ተወስኗል።
የተለያየ የአካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 80.2% ያህሉ 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸው ተነግሯል።
67,939 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 56,842 የሚሆኑት ማለትም 83.6 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።
ከ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሀገሪቱን ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ የማያደርጉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች(international school) የሚማሩ ተማሪዎች የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል መልቀቂያን ጨምሮ የ12ኛ ክፍል ፈተና መፈተን እንደማይችሉ ቢሮው አሳውቋል።
ወላጆች ከወዲሁ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ በመወሰን ልጆቻቸውን ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት ተለልፏል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን ተከታዮቹን ሊንኮች በመጫን መመልከት ይችላሉ።
https://aa6.ministry.et/#/result
Telegram bot: @G6MinistryResultQMTBot

የድርጅትዎን መልዕክት በስልክ ጥሪ መለያ (Call signature) ያስተላልፉ!
የድርጅትዎ ሞባይል ስልኮች ላይ ጥሪ በሚቀበሉበት ወይም በሚደውሉበት ወቅት ለደዋዮች ቀድሞ በሚደርስ መልዕክት መልዕክት ወይም ማስታወቂያዎን ያኑሩ!
አገልግሎቱን ቸርችል ጎዳና ከሊሴ ገብረማርያም ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው ፕሪሚየም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ያገኙ!
ለበለጠ መረጃ https://bit.ly/3K803qo ይጎብኙ
(ኢትዮ ቴሌኮም)

#Update የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም እንደሚከናወን ተገለፀ። ቋሚ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ተፈፅሟል ባለው ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ጉዳይ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ እንደሚካሄድ አመልክቷል። " በክልል ትግራይ በማእከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን…
ፎቶ፦ ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ በጸሎት ተከፍቷል።
" የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በክልል ትግራይ ባሉ አህጉረ ስብከት ለመንፈሳዊ አገልግሎት ተመድበው የነበሩ አራት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በፈጸሟቸው የቀኖና ቤተክርስቲያን እና የሕግጋተ ቤተክርስቲያን ጥሰቶች ዙሪያ ለመወያየትና ሕግጋተ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ጉባኤውን በጸሎት ጀምሯል " ሲል የቤተክርስቲያኗ ሕዝብ ግንኙነት አሳውቋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በኩል የተጠራውና ዛሬ በፀሎት የጀመረው አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ነገ ጠዋት በተያዙት አጀንዳዎች ላይ በመወያየት የቤተክርስቲያኗን ቀኖናትና ሕግጋት የሚያስከብሩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሏል።
መረጃ እና ፎቶ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት