TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

" ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር በበረካታ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል "  - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

በኃይል ማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።

ደንበኞች ችግሩ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተቀርፎ አገልግሎቱ ወደነበረበት እስኪመለስ ድረስ በትግዕስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@tikvahethiopia
#MyWish

አስተማማኝ የሆነውንና ቱርክ ሰራሹን ኢሳን ሲልድ ባትሪን በተለያዩ አማራጮች ማለትም በ12V35AH፣ በ12V45AH፣ በ12V55AH፣ በ12V60AH፣ በ12V70AH፣ በ12V90AH፣ በ12V100AH፣በ12V120AH እና በ12V150AH በጅምላና በችርቻሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
0910041280  0911135133  0921612272  0911159234   0984733988  0941473413
ዋና መስሪያ ቤት፡ ሀይሌ ጋርመንት ወደለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ ቅርንጫፍ፡ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ አጠገብ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ 
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.iss.one/MYWISHENT
#ምርጥ_ዕቃ

እነዚህ ዕቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በሱቃችን እየተሸጡ ነው።  ዋጋ ለማየት ይሄንን👉 t.iss.one/MerttEka ይጫኑ

🎯 አድራሻችን፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ተኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ 376 ይጎብኙን
🎯 አዲስ አበባ ውስጥ ባሉበት እናመጣለን
👉 ተጨማሪ መረጃ ለማየት👉 t.iss.one/MerttEka
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት " ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር በበረካታ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል "  - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ አካባቢዎች የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡ በኃይል ማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል።…
#Update

ትናንት ምሽት በሃገሪቱ  በረካታ  አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት መመለሱ ተገለፀ።

በጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በበረካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦቱ ወደነበረበት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

ተቋሙ ፤ ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደነበረበት የተመለሰው በማመንጫ ጣቢያው ላይ ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር ለማስተካከል በተደረገ  ከፍተኛ ጥረት መሆኑን ገልጿል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በትግዕስት ለተጠባበቁ ደንበኞቹ ምስጋና አቅርቧል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሱዳን ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት እየገባች ነው " - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሱዳን ያለው ግጭት ሙሉ ለሙሉ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እያመራ መሆኑ እና ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አስጠንቅቀዋል። ዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትናንት ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመ የአየር ጥቃት 22 ሲቪሎች መገደላቸውን እና በርካቶች…
#Update

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ንግግር ለማስጀመር በግብፅ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ካይሮ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አል-ሲሲ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት የሱዳን ጎረቤት አገራት መሪዎች በሚያደርጉት ውይይት ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ ረፋድ ወደ ካይሮ መጓዛቸው ተገልጿል።

የሱዳን ጎረቤት የሆነችው ግብፅ ሁለቱን የጦር ጄኔራሎችን ሐሙስ ሐምሌ 06/2015 ዓ.ም. ለማደራደር ማቀዷ ተነግሯል።

በሌላ በኩል፥ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የውጭ ኃይሎችን " ወደ ሱዳን የመላክን ጥሪ እንደማይቀበለው አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ሱዳን ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት(ኢጋድ) ልትወጣ እንደምትችልም አስጠንቅቋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን መግለጫ ያወጣው ኢጋድ በትናንትናው እለት በሱዳን ጉዳይ በአዲስ አበባ መምከሩን ተከትሎ ነው።

ሚኒስቴሩ እንደገጸው የሱዳን ልኡካን ቡድን በአዲስ አበባ መገኘት ፣ ሱዳን ለሰላማዊ መፍትሄ ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብሏል።

በሱዳን ጦር መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሐን እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ መካከል የተፈጠረው የሥልጣን ሹክቻ በሱዳን ሉዓላዊ እና እንድነት ላይ አደጋ ከመጋረጡ በላይ በቀጠናው ላሉ አገራት የደኅንነት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሱዳን ወደለየለት የዕርስ በዕርስ እየገባች ነው ፤ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ ይችላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

Via BBC

@tikvahethiopia
#Tecno_Camon20
በአዲሱ ቴክኖ ካሞን 20 ካሜራ እያንዳንዱ ፎቶ ልዩ ነው !

እጅግ የላቀ እና የዘመነ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ካሞን 20 አስደናቂ በሆነ መልኩ ማንኛውንም አይነት ፎቶ በየትኛውም ጊዜ ማንሳት የሚያስችል ብቃት ያለው ድንቅ ስልክ ሲሆን ዋናው የኃላ ካሜራ 108 ሜጋ ፒክስል እና ተጨማሪ ሁለት ባለ 50 ሜጋ ፒክስል ሌንስ ያካተተ ነው ። ካሞን 20  የሚያስደንቁ ፎቶዎችን ከየትኛውም ርቅት በጥራት እና ቀለማትን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል አቅም አለው ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Camon20Series #TecnoMobile #TecnoEthiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለማንኛውም አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ በባንካችን የደንበኞች አገልግሎት መስመር #8292 ላይ ይደውሉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
TIKVAH-ETHIOPIA
" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ”…
" የምርቃት መርሀ-ግብር ተሳትፎን በተመለከተ በተቋማት ሴኔት ብቻ ነው የሚወሰነው " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ከዚህ ቀደም ያወጣው መግለጫ ላይ ማስተካከያ ማደረጉን አስታወቀ።

ከምርቃት እና የምረቃ መርሀግብር ተሳትፎ ጋር በተገናኘ በቅርቡ የኢት/ከፍ/ት/ተቋ/ተ/ህብረት መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል።

በዚህም መግለጫ ከምርቃት ፕሮግራም ጋር በተያያዘ የተነሳውን ሀሳብ በተመለከተ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል።

በዚህም ሁሉም ተማሪ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃውን ከማግኘቱ አስቀድሞ የመውጫ ፈተናን ማለፍ የሚጠበቅበት ሲሆን የምርቃት መርሀ-ግብር ተሳትፎን በተመለከተ በተቋማት ሴኔት ብቻ የሚወሰን መሆኑን አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል። ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ዕጩ ምሩቃን ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የመውጫ ፈተና ከቀናት በፊት ለጤና ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዕጩ ምሩቃን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ። የመውጫ ፈተናው እስከ ሐምሌ 8 /2015 ድረስ መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የፈተናው ውጤት በአጭር ጊዜ…
#ExitExam

በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙና የመውጫ ፈተና የወሰዱ የ " መካኒካል ምህንድስና " የትምህርት ዘርፍ ተማሪዎች በተፈተኑት የፈተና ይዘት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልእክት አሳውቁ።

ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን ለየሚማሩበት ተቋማት የሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ጥያቄ እና ቅሬታ የተቀበለ ሲሆን ተማሪዎቹ ምንም እንኳን የትምህርት ሚኒስቴር ብቁ ዜጋን ከማፍራት አንጻር እና የት/ት ጥራትን ለማሻሻል እየተገበረ ያለውን የመውጫ ፈተና የሚደግፉት ቢሆን የተፈተኑት የፈተና ይዘት ከተነገራቸው መመዘኛ ነው ተብሎ ከቀረበው ሀሳብ ጋር የማይገጥም መሆኑን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ ለመመዘኛ የቀረበው የፈተናው ክብደት እና ብሉ ፕሪርት ተብሎ ከተሰጣቸው ጋር እንዳልተጣጣመ ፤ ለፈተናው የተሰጣቸው ሰዓትም ከጥያቄው አንፃር እዚህ ግባ የማይባል መሆኑ በማስረዳት ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ የወጡ ፈተናው ጥያቄዎች ተከልሰው እንዲታዩ የጠየቁ ሲሆን በተማሪዎች ዘንድ ያሉ ጥያቄዎች የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ በማጤን የፈተናው ውጤት ከመገለፁ በፊት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን ጥያቄ በተመለከተ የሚመለከተውን አካል ለማነጋገር ጥረት ያደርጋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጉዳዮችን በ @tikvahUniversity ይከታተሉ።

@tikvahethiopia
" ልዩነቱ በእርቅ ተፈቷል "

የኢትዯጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት በመካከላቸው የተፈጠረውን ልዩነት በእርቅ ፈቱ።

- የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፥
- የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፥
- የኢትዮጵያ ሙሉወንጌል ቤተ ክርስቲያን ፥
- የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፥
- የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያናና
- የኢትዮጵያ ገነት ቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረው አለመግባባት በእርቅ መፍታታቸውን አስታውቀዋል።

ዕርቁን አስመልክቶ በደረሰን መግለጫ እነኝህ የቤተ እምነት ህብረቶችና የቤተ ክርስቲያን አጋዥ ድርጅቶች ቀደም ባሉት ዓመታት በወንጌል ስርጭት በኩል ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡና ፍሬያቸውም ጎልቶ የሚታይ ሆኖ በተደራጀ መንገድ ተቀራርበው ይሰሩ እንደነበር ተመላክቷል።

ሆኖም ግን ለልዩነታቸው ምክንያት የሆኑ ቤተ እምነቶቹ በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው ፥ በተለይም ካውንስሉ ክተመሰረተ በኋላ በቀላሉ ወደ አንድ አሠራር ማምጣትና መግባባት ሳይቻል እንደቆየ ተገልጿል።

በተለይም ካውንስሉ በአዋጅ ከተቋቋመበት ጊዜ ወዲህ የነበሩ ልዩነቶችን ለመፍታት ሰፊ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ጠለቅ ያለ ውይይትና እና ምክክር የሚፈልጉ ፦
- ከውክልና፥
- ከአደረጃጀት፥
- ከደንብና አሠራር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ስምምነት መድረስ ሳይቻል ቆይቶ እንደነበር ተገልጿል።

ቤተ እምነቶች በጋራ ለልዩነታቸው ምክንያት የሆኑ ተግዳሮቶችን በስፋት ከመከሩ በኋላ ካውንስሉ የተቋቋመበትን ዓላማ መፈጸምና ሀገራዊ ተልዕኮዎችን መወጣት የሚያስችል አቋም እንዲኖረው ለማድረግ የልዩነት ነጥቦችን በመለየት እና የመፍትሔ ሀሳቦችን በማስቀመጥ እንደ እግዚአብሔር ቃል በመቀባበልና በመካከር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

ወደፊት በሚደረገው የጋራ እንቅስቃሴ የወንጌል አማኞች ሁሉ ስለተደረገው እርቅ እግዚአብሔርን በማመስገን በጸሎትና በምክር ከካውንስሉ ጎን እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia