TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ…
#Mekelle

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልኡክ ዛሬ ከሰአት በተለምዶ " መቐለ 70 ካሬ " ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝቱ ተፈናቃዮች " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን በስፍራው የነበሩ የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ቅዱስ ፓትሪያርኩ ፤ " በውስጣችሁ የሚሰማችሁን እንኳን ተናገራችሁ " ካሉ በኋላ ፤ " ሰሚ ከተገኘ ወደ ቀያችሁ እንድትመለሱ ለሚመለከተው እንናገራለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አንድ የሬሜዲያል መርሀግብር ተማሪው በመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉን እና ሌሎች ተማሪዎቹም መጎዳታቸውን አሳወቀ።

" ተማሪ ዮሐንስ ፈቃዱ  የተባለ በዩኒቨርሲቲያችን በአቅም ማሻሻያ መርሃ ግብር (Remedial Program) በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ክፍል ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቶ ወደቤተሰቦቹ ሲመለስ በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ አልፏል " ሲል ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ምንም እንኳን ስለደረሰው አደጋ የት እና ስንት ሰዓት እንደሆነ ባይገልጽም ፥ " በተፈጠረው አሰቃቂ አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን  እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለቤተሰቦቹ (ለተማሪው) መፅናናትን እንመኛለን " ብሏል።

ሌሎች አደጋ የደረሰባቸው ተማሪዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል  ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

ትላንትና እሁድ ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረ ባስ ተገልብጦ የቦረና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉና ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሩት የሰላም ልዑክ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል ነበር ?

- ቀደም ብሎ በወጣ መርሀ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልዑክ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ በምዕመናን፣ ዘማርያን፣ በክልሉ ሃይማኖት አባቶች አቀባበል ይደረግለታል ቢባልም በስፍራው ከትግራይ አባቶች ፣ ዘማርያን የተገኘ አልነበረም። የተገኙት የመንግስት አመራሮች ነበሩ።

- በመቀጠል እዛው መቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ምዕመናን፣ ካህናት ፣ የትግራይ አባቶች አልተገኙም ነበር። ቅዱስነታቸው እና የመሩት ልዑክ የቤተክርስቲያኑ በር የዘግቶባቸው በር ላይ ፀሎት አድርሰው ለመውጣት ተገደዋል።

- በፕላንቴ ሆቴል በተካሄደ ስነስርዓት ልዑኩ የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ ስነስርዓት ላይ የትግራይ አባቶች #አልተገኙም። ተገኝተው የነበሩት የክልሉ መንግስት አመራሮች ነበሩ።

- ልዑኩ በመቀጠል በመቐለ 70 ካሬ ተፈናቃዮችን የተመለከተ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት ተፈናቃዮች በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- ከመቐለ 70 ካሬ የተፈናቃዮች መልከታ በኃላ የሰላም ልዑኩ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ጋር ይገናኛል ውይይትም ያደርጋል የሚል መርሀ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም ይህም አልተደረገም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያሉ ብፁዓን አባቶች ከጥዋት አንስቶ በነበሩ መርሀግብሮች ላይ ለምን አልተሳተፉም ? የሚለውን ለመጠየቅ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቅዱስ ፓትርያርኩ የመሩት የሰላም ልዑክ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል ነበር ? - ቀደም ብሎ በወጣ መርሀ ግብር በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልዑክ መቐለ አሉላ አባነጋ ኤርፖርት ሲደርስ በምዕመናን፣ ዘማርያን፣ በክልሉ ሃይማኖት አባቶች አቀባበል ይደረግለታል ቢባልም በስፍራው ከትግራይ አባቶች…
" ወደፊት ዕርቀ ሰላም እንዲፈጠር ተስፋችን ብርቱ ነው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በመቐለ ምን አሉ ?

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፦

" በትግራይ ላይ የተፈፀመው ፤ የወረደው መቅሰፍት አዲስ ነገር ነው የሆነብን ሁላችንም ፤ እንጃ በዓለም ተደርጓል፣ አልተደረገም እስከማለት ድረስ ነው የደረስነው።

የሆነው ሆኖ ሁኔታው እጅግ አስከፊ ቢሆንም መወያየት ፣ እኛ የመጣነው ስለ ሰላም ነው ፤ ሰላምን ፍለጋ ነው እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጉባኤው ይቅርታ ጠይቋል ባልፈው ችግር የተፈፀመውን ይቅርታ ጠይቋል።

እስቲ እንደዚህ ከሆነ ሄደን መወያየቱ ጥሩ ነው ብለን መጥተን ነበር ክቡርነትዎ ከስራ ባልደረቦቾ ጋራ ላደረጉልን አቀባበል እናመሰግናለን።

የሆነው ሆኖ መወያየት ክፉ አልነበረም ፣ ሰው ሃሳቡን ለመግለፅም ሆነ ለመስማማትም ሆነ ላለመስማማትም መገናኘት እና መወያየት ክፉ አልነበረም።

ብፁዓን አባቶች በምን ምክንያት እንደቀሩ እኛ የምናወቀው ነገር የለም ፤ በጤና ነው ወይስ አውቀው ነው ሳያውቁ ነው ወይስ አምነውበት ነው ወይስ ሳያምኑበት ነው የሚለውን እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

የሆነው ሆኖ መወያየት ጥሩ ነበር ፤ በመወያየት ሃሳብን መግለፅ ይቻላል፤ የደረሰውን ችግር መግለፁ እራሱ ማስረዳቱ ኣንድ ቁምነገር ነበር። ከዛም ይሁንም አይሁንም ለማለት ውይይት ጥሩ ነበር። ብንወያይ ክፉ አልነበረም። ኣጋጣሚ ሆኖ አልተገናኘንም ከብፁዓን አባቶች ጋር።

ያለውን ችግር ረስተነው አይደለም ፤ ይሄ ኮሚቴ (የልዑኩ አባላትን ማለታቸው ነው) ሁሉ ተረድቷል ፤ አብረውን ያሉት ወገኖቻችን ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ በትግራይ ላይ የደረሰውን መከራ የተረዳችሁት ይመስለኛል።

ያ ነገር ፤ ለመዓት የመጣ ነገር ስለሆነ ለጊዜው ጋብ ብሏል ፣ከነበረው ጭንቀት ከነበረው ጥበት ፣ መከራ ትንሽ ጋብ በማለቱ ደስ ብሎናል።

ክቡር አቶ ጌታቸው በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለተደረገው ስምምነት ብዙ እንደደከሙ እናውቃለን ያን ሰላም ስላገኘን ነው እዚህ ለመገናኘት የበቃነው፤ እዚህ የተገናኘነው በዛ ሰላም መሰረት ነውና ሰላሙ እንዲቀጥል የሁላችንም ፀሎትም ምኞትም ነው።

ያለፈው ይበቃል፣ ያለፈው መዓት ፣ውርጅብኝ ፣ እልቂት ይበቃል ከአሁን በኃላ ሰላሙን ፈጥረን በሰላም እንድንኖር የሁላችንም ፀሎት ነው።

እናተም ችግሩን የፈታችሁት በውይይት ነው ፤ ከማዕከላዊ መንግሥት ጋር የምትነጋገሩት በውይይት ነው ፤ ተነጋራችሁ ተስማምታችሁ ቅደም ተከተሉን እየተከተላችሁ እየሄዳችሁ ነውና ጥሩ ነው። ሁላችንም የምንደግፈው ነው።

በቤተክርስቲያን በኩል ያለውን ግን ሁላችንም ጥረት ብናደረግ ፤ ጥረት ማድረጉ አስፈላጊ ነው።

ፊት ለፊት ተገናኝንቶ መነጋገሩ አይከፋም ፤ ምን ችግር አለ ? መቼስ ሰው በግድ አልተስማማህም ተብሎ የሚያስረው የለ ፤ የሚፈልገውን ተናግሮ የሚፈልገውን ገለፃ ገልጾ ፣ ራሱ የፈቀደውን የሚሄድበትን መንገድ ለመሄድ የሚከለክል የለም ማን ይከለክለዋል ? እና ብፁዓን አባቶችን አላገኘናቸውም ፤ ወደፊት ተስፋ አለን። ተስፋችን አያልቅም። ወደፊት ተስፋ አለን እርቀ ሰላም እንዲፈጠር ተስፋችን ብርቱ ነው። የክልሉ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥበትና ውይይቱ ቢከፈት የሚል ነገር ለመግለፅ እፈልጋለሁ።

ስላደረጋችሁልን አቀባበል እናመሰግናለን ። እግዚአብሔር ይስጥልን ! "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ

ብልሆች ነገን ቀድመው ያያሉ። የታዳጊዎች እና የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ በርካታ ጥቅሞች የቀረቡበት የቁጠባ ሂሳብ ነው። አሁኑኑ ወደ አቢሲንያ ቅርንጫፎች ብቅ በሉ።

#BankofAbyssinia #BankingService #BanksinEthiopia #SavingAccount #EducationSaving #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan የጎረቤት ሀገር ሱዳን ጦርነት #ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ ኢጋድ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ  የሰላም ስምምነት እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በሱዳን ሚያዚያ ወር የጀመረው ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ህይወታቸውን እያጡ ፣ ከቤታቸው እየተፈናቀሉ፣ ንብረትም እየወደመ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚም እየወደቀ ይገኛል። ተፋላሚዎቹ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ (RSF) ካርቱም ላይ…
" ሱዳን ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት እየገባች ነው " - አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

በሱዳን ያለው ግጭት ሙሉ ለሙሉ ወደ የእርስ በእርስ ጦርነት እያመራ መሆኑ እና ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አስጠንቅቀዋል።

ዋና ጸሃፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ትናንት ማስጠንቀቂያውን የሰጡት ቅዳሜ ዕለት በተፈጸመ የአየር ጥቃት 22 ሲቪሎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ተከትሎ ነው።

ጥቃቱን ያወገዙት ጉተሬዝ ሱዳን ወደለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት እየገባች ነው መሆኗን እና ይህም ቀጠናውን ወደ ትርምስ ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በሌላ በኩል እስካሁ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጦርነት የሚቆምበትን መንግድ ለመፈለግ የኢጋድ አባላት የሆኑት የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎች፣ የልማት በይነ መንግስታቱ ጉዳዩን እንዲከታተሉ በሰጣቸው ሃላፊነት መሠረት በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ መክረዋል።

ሁለቱ ተፋላሚ ጄኔራሎች፣ የጦር ሠራዊቱ አዛዥ የሆኑት አብደል ፋታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ቢጋበዙም አልተገኙም።

ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ፤ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ጠይቋል።

በሱዳን ያለውን ችግር ወታደራዊ እርምጃ እንደማይፈታው እና የቡድኑ ጥረትም የሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች መሪዎችን ፊት ለፊት በማገናኘት ላይ የሚያተኩር እንደሚሆን አስታውቋል።

የኢጋድ ቡድን በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በአስቸኳይ እና ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈርሙ፣ የስምምነቱን ተግባራዊነትን በተመለከተም ቁጥጥር የሚደረግበት መንገድ እንዲበጅ ጥሪ አድርጓል።

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን በተመለከተ ጉባኤ እንዲደረግ እንደሚጠይቅና ሲቪሎችን ለመከላከል እና ሰብዓዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ኃይሉ እንዲሠማራ እንደሚሻም የቡድኑ የአቋም መግለጫ አመልክቷል።

ፍራንስ 24 በኢጋድ ስብሰባ ላይ  ፤ ተፋላሚ ሃይሎቹ እንደሚሳተፉ አረጋግጠው የነበረ ቢሆንም ተወካዩን የላከው የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ብቻ ነው ብሏል።

የሱዳን ጦር ተወካይ አዲስ አበባ ቢገቡም በምክክሩ ላይ  " አልሳተፍም " ብለዋል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአራትዮሽ (ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ጂቡቲ) ስብሰባውን የሚመሩት የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያን ሩቶ በሌላ ካልተተኩ ጦሩ በስብስባው ላይ እንደማይሳተፍ ነው ያስታወቀው።

ፕሬዝዳንቱ ለፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ያደላሉ የሚል ወቀሳ ከሱዳን ጦር ተደጋግሞ ተሰምቷል።

የፖለቲካ አማካሪያቸውን ወደ አዲስ አበባ የላኩት ጀነራል መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጦሩ በስብሰባው ላይ አለመሳተፉን " ሃላፊነት የጎደለው ባህሪ " ነው ብለውታል።

(ቪኦኤ ፣ ፍራንስ 24)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደፊት ዕርቀ ሰላም እንዲፈጠር ተስፋችን ብርቱ ነው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በመቐለ ምን አሉ ? ቅዱስ ፓትርያርኩ ፦ " በትግራይ ላይ የተፈፀመው ፤ የወረደው መቅሰፍት አዲስ ነገር ነው የሆነብን ሁላችንም ፤ እንጃ በዓለም ተደርጓል፣ አልተደረገም እስከማለት ድረስ ነው…
ፎቶ፦ በትላንትናው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተመርቶ ወደ መቐለ ያቀናው የሰላም ልኡክ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ልኡኩ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተከህነትና ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የመምሪያ ሓላፊዎች ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ካህናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢኦቴቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት እንደዘገበው ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ክልሉ ሲደርሱ በትግራይ ክልል በሚገኙ ብፁዓን አባቶች፣ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ምንም ዓይነት መንፈሳዊ የአቀባበልም ይሁን የሽኝት ሥነ ሥርዓት እንዳልተደረገላቸው ጠቅሷል።

ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ጭምር የኪዳን ጸሎትን በተዘጋ የቤተክርስቲያኒቱ ደጅ ላይ ለማድረግ ተገደዋል ሲል በዘገባው ጠቅሷል።

በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራው ልዑክ ፥ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን እንዲሁም አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች አባላትን አካቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት በጦርነት ምክንያት ለተፈናቃሉ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግና በክልሉ ከሚገኙ የሃይማኖቱ መሪዎች ጋር ለመወያየት ወደ ትግራይ ክልል መቐሌ ያቀናው በትላንትናው ዕለት እንደነበር ይታወሳል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia