TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ መሰረትም ፦ - ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣ - የተማሪዎች ምረቃ…
" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት
' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ።
መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል።
አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል።
የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል።
ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ መቀመጡንም አሳውቋል።
ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል።
የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት / የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የትምህርት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን ህብረቱ ጠቁሟል።
በሌላ በኩል ዕጩ ተመራቂ ተፈታኞች በመውጫ ፈተና ወቅት ተከታዮቹን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ አሳስቧል።
- የሚፈተኑበትን ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሸው እንዲጠቀሙ።
- ፈተናውን በሚሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታቸውም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ።
- ወደ መፈተኛ ክፍሎች ሲገቡና እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንዲያከብሩ።
- ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማቸው በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የICT ባለሙያዎች በፍጥነት እንዲያሳውቁ፤
- የሚያጋጥሟቸው የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቸው ላለው ህብረት በማመልከት ከግቢው አቅም በላይ ከሆነ በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝቧል።
More : @tikvahuniversity
@tikvahethiopia