#AddiAbaba
" ነዋሪዎች በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በ54 የመኖሪያ ቤት የሕብረት ስራ ማሕብራት ከ4 ሺህ በላይ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ ዛሬ መጀመሩን የአ/አ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል።
ስራው ያስጀመሩት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ " የነዋሪው ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጭ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንገኛለን " ብለዋል።
" የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን ይችላሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በበኩሉ ፤ የቤት ልማት አማራጮች ላይ ትኩረት በማድረግ የከተማውን የቤት ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቢሮው ፍላጎት እና አቅሙ ያላቸውን የ20/80 እና የ40/60 ቤት ልማት ኘሮግራም ተመዝጋቢ የነበሩትን በ54 በጋራ ህንፃ ህብረት ስራ ማህበር በማደራጀት ወደስራ ለማስገባት ሲሰራ የቆየውን ስራ አጠናቆ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እንደተጣለ ገልጿል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ቪድዮ ፦ በፈረንሳይ ሀገር ፤ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መገደለን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመፅ አሁንም ቀጥሏል።
በዚሁ አመፅ በርካታ ተቋማት ተዘርፈዋል።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በታዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የአፕል፣ ዛራ፣ ናይክ የመሳሰሉ ትልልቅ ድርጅቶች ዘረፋ ሲፈፀምባቸው ታይቷል።
በተጨማሪም በማርሴ ከተማ አንድ የ " ቮልስ ዋገን " ተሽከርካሪ መሸጫ በአመፀኞች ሲዘረፍ ታይቷል።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ የመኪና መሸጫ ውስጥ የገቡ አመፀኞች አዳዲስ መኪናዎችን እያሽከረከሩ ሲወጡ ይታያል።
ከዚህ ባለፈ በፈረንሳይ አመፀኞች የቤት አስቤዛ በሚሸጥባቸው መደብሮች እየገቡ ዘይትን እና ሌሎች አስቤዛዎችን ዘርፈው ሲወጡ ታይተዋል።
የፈረንሳይ መንግሥት ፤ በሀገሪቱ ያለውን ቀውስ ለመቆጣጠር እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል አሰማርቷል።

#Update በኦሮሚያ ክልል፣ " አሊ ዶሮ " ላይ ከታገቱት ሹፌሮች እና ረዳቶች መካከል በአጋቾች የተጠየቀውን ብር ከፍለው የተለቀቁ ስለመኖራቸው ቪኦኤ ሬድዮ ቤተሰቦቻቸውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ቃላቸውን የሰጡ አንድ ወላጅ ፤ ልጃቸውን 1 ሚሊዮን ብር ከፍለው ከእገታው እንዳስለቀቁ አመልክተዋል። ከታገቱት አሽከርካሪዎች ውስጥ ሰባቱ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ዐማኑኤል ከተማ ወጣቶች እንደሆኑ…
ልጃቸውን ከእገታ ለማስለቀቅ አንድ ሚሊዮን ብር የተጠየቁት መምህር ብዙ ዋጋ ከፍለው ልጃቸውን በህይወት አግኝተውታል።
ቅዳሜ ሰኔ 10/2015 ወደ ጎጃም ሲሄዱ ከታገቱት ወደ 30 ሹፌሮችና ረዳቶች መካከል አንደኛው የአማኑኤል ከተማው መምህር አንለይ መኩሪያ ልጅ ነው።
መምህሩ ለልጃቸው የተጠየቁት አንድ ሚሊዮን ብር ነው።
ይህን ያህል ገንዘብ በ40 ዓመታት የማስተማር ስራቸው አግኝተው እና ኖሯቸው እንደማያውቅ ፤ በደሞዝ በቀጥታ እጃቸው የገባው ገንዘብ ቢታሰብም አንድ ሚሊዮን ሊደርስ ስለመቻሉ እርግጠኛ አይደሉም።
አይደለም አንድ ሚሊዮን ብር ሊኖራቸው እሳቸውን እራሱ የሚደጉመው ይኸው የታገተባቸው ልጃቸው ነው።
ግን ልጅ ነውና ከዚህ የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ መከፈል ያለበት ዋጋ መከፈል ስለነበረበት ልጃቸውን ለማስለቀቅ በአጋቾ የተጠየቁትን ገንዘብ ማፈላለግ ጀመሩ።
ከተጠየቀው የማስለቀቂያ ገንዘብ ውስጥ እዚህ ግባ የሚባል ብር እጃቸው ላይ የሌላቸው መምህር አንለይ በእርዳታ መቶ ሺህ ብር ብቻ አገኙ ፤ ቀሪው 900 ሺህ ብር ለማግኘትና የልጃቸውን ሕይወት ለመታደግ ሲሉ ዕዳ ውስጥ ገቡ።
ጎረቤቶቻቸው ከልጅ የሚበልጥ ነገር የለም ብለው ቤታቸውንም ቢሆን ሽጠው እንደሚከፍሉ በመግለፅ 1 ሚሊዮን ብር አሰባስበው ሞሉላቸው።
አጋቾቹ ብሩን በባንክ አንቀበልም በማለታቸው ብሩን ተሸክመው ከአማኑኤል ተነስተው አጋቾቹ ወደ ነገሯቸው የመቀበያ ስፍራ ፤ እገታው ከተፈፀመበት አቅራቢያ ገብረ ጉራቻ ይዘው ሄዱ።
ገንዘቡን በማዳበሪያ የተሸከሙት መምህር ፤ ገርበ ጉራቻ ከደረሱ በኋላ አስተርጓሚ ቀጥረው ከከተማው 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ቦታ ተጓዙ።
ከዚያች ቦታ እንደደረሱ አንድ ግለሰብ ሲጠብቃቸው አገኙ። ለአጋች ነኝ ላለው ሰው ሲደውሉ ብሩን የሚቀበለው ይህ ግለሰብ መሆኑን ነገራቸው።
ይህ ሲሆን ግን ልጃቸው የት እንዳለ አያውቁም። ተስፋ ያደረጉት ብሩን እንደሰጡት ልጃቸው በዚያው አቅራቢያ እንደሚለቀቅላቸው የነበረ ቢሆንም ከአጋቾች የተሰጣቸው መልስ የሰጣቸው መልስ ፦
" ገንዘቡን ፈትተን አሳይተን አስረከብነው። ብሩ ከሰባት ሰዓት ጉዞ በኋላ ዋናዎቹ አጋቾች ጋር ይደርሳል። ከዚያ በኋላ ብሩ ተቆጥሮ አድሮ ሙሉ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ይነገርሃል " ብለው ሸኙኝ " የሚል ነበር።
በማግስቱ ግን ልጃቸው ተለቆ በአካል አገኙት።
መምህሩ ፤ " በአንድ ሚሊዮን ብር ነፍሱን የገዛሁት ልጄ፣ ረጅም ርቀት የተጓዘበት ጫማው ተቀዶ እና እግሮቹ አባብጠው ሳገኘው እንደገና እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። የአገሩ ሰው እስኪገረም ድረስ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ " ሲሉ ተናግረዋል።
መምህር አንለይ እና የሌሎች ታጋች ቤተሰቦች በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ ከአጋቾቹ ጋር ስለሚያደርጉት ግንኙነት ሆነ ስለተጠየቁት ገንዘብ ለማሳወቅ ከፀጥታ አካላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አላደረጉም።
ለዚህም አንደኛው ምክንያት ፖሊስ በጉዳዩ ውስጥ ከገባ ታጋቾቹ በታጣቂዎቹ ሊገደሉ ይችላሉ የሚል ሲሆን ሌላኛው ጉዳዩ አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው በመሆኑ ከመንግሥት ኃይሎች የተሰወረ ነው ብለው ባለማመናቸው ነው።
" መንግሥት እና ሕግ ባለበት አገር የአሁኑን በእዚህ ሁኔታ ፈታነው። " ያሉት መምህር አንለይ " ቀጣይስ? ልጄ ድጋሚ ላለመታገቱ ምን ዋስትና አለኝ ? ሥራ አቁም እንዳልለው አቅም የለኝም። እንዲያውም ከፍተኛው ስጋቴ የወደፊቱ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
በነገራችን ላይ ይህ የአንድ ቤተሰብ ታሪክ ነው። በርካቶች ሚዲያ ላይ ያልቀረቡ ታሪኮች ይኖራሉ። ሀገር ሰላም ብለው ከቤት ወጥተው የታገቱና ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ብዙ ናቸው።
የመምህር አንለይ መኩሪያን ታሪክ ያጋራው ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ዛሬ መሰጠት ይጀምራል፡፡
በ2014 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩና በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች የሪሚዲያል ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል።
ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ለሚሰጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የላከው የጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ፈተናው ዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 መሰጠት ይጀምራል፡፡
የፈተና የፍተሻና የክፍል ቅድመ ዝግጅት በየዕለቱ ከቀኑ 8:00 የሚጀምር ሲሆን ፈተናው ደግሞ ከቀኑ 9:00 መሰጠት ይጀምራል። (የፈተናው መርሃ ግብር ከላይ ተያይዟል፡፡)
ተፈታኝ ተማሪዎች ለፍተሻ እና የክፍል ቅድመ ዝግጅት ሥራ 8:00 ላይ በመፈተኛ ክፍላቸው በር ላይ እንዲገኙ ተብሏል፡፡
Via : t.iss.one/+RYD_4tbNBwRoKR2h
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

#coop
ያለ ማስያዣ ብድር - COOP
We finance your dream with Michu. Embrace the hassle-free digital world and get loan without a collateral. Visit your nearest Coopbank of Oromia’s nearest branch today!
Follow us on https://t.iss.one/coopbankoromia
#Michu #NoCollateralNeeded #difitalfinancing

#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል። 3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 011851289 ሆኖ ወጥቷል። 👉 3 ሚሊዮን ብር - 0111851289 👉 1,200,000 ብር - 0111137546 👉 800 ሺህ ብር - 0112042798 👉 400 ሺህ ብር - 0110682365 👉 250 ሺህ…
#DigitalLottery
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ወጥቷል።
3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0120773349 ሆኖ ወጥቷል።
👉 3 ሚሊዮን ብር - 0120773349
👉 1,200,000 ብር - 0121599869
👉 800 ሺህ ብር - 0120855225
👉 400 ሺህ ብር - 0122312400
👉 250 ሺህ ብር - 0120231703
(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)
በሌላ በኩል ደግሞ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ሽልማት ማደጉ ተገልጿል።
ሽልማቱ ያደገው በደምበኞች አስተያየት መሆኑን የገለፀው ብሔራዊ ሎተሪ ፦
- የአንደኛው ዕጣ 4 ሚሊዮን ብር፣
- የሁለተኛው ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር
- የሶስተኛው ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር በማድረግ ከሰኔ 24 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን አመልክቷል።
ምንጭ፦ ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሔራዊ ሌተሪ አስተዳደር

" አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አልተገኙም " - ባለስልጣን መ/ቤቱ
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ አስጠንቅቋል።
የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከዛሬ ሰኔ 26/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 29/2015 ዓ.ም መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ ዛሬ ባደረገው ክትትል፤ አብዛኞቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳልተገኙ ገልጿል።
የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎቻቸው ሞዴል ፈተናውን እንዲወስዱ አለማድረጋቸውንም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል፡፡
በመሆኑም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በአቅራቢያቸው በሚገኙ ለመውጫ ፈተና በተዘጋጁ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በመላክ ሞዴል ፈተና እንዲወስዱ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳስቧል።
More : @tikvahuniversity

" ጥቃቱ የተፈፀመው የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ት/ቤት ሲጓዙ ነው " - የደጀን ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን
በዛሬው ዕለት መሰጠት የተጀመረውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና ሲጓዙ የነበሩት የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በጥይት ተመተው ተገደሉ።
በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትገኘው የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ እና ምክትላቸው በተከፈተባቸው ተኩስ ሲገደሉ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤትን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።
የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት፤ የደጀን ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ጥቃት የተፈጸመባቸው ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ እንደሆነ ገልጿል።
ጥቃቱ የተፈፀመውም በግለሰብ አማካኝነት መሆኑን አመልክቷል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በተለያዩ አካባቢዎች ዛሬ መሰጠት የተጀመረውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ደህንነት ለመከታተል ወደ አባይ ሸለቆ ትምህርት ቤት በመኪና እየተጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑን አሳውቋል።
የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፤ ሁለቱ የፖሊስ አዛዦች " ግልገሌ " የተባለች ቀበሌ ላይ ሲደርሱ " መንገድ ላይ ሲጠብቃቸው ነበር " በተባለ ግለሰብ ተኩስ እንደተከፈተባቸው በዚህም በጥይት የተመቱት የፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር ዘውዱ እና ምክትላቸው ኢንስፔክተር ወርቁ ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን አስረድቷል።
ሹፌራቸው እግሩን ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰበትም አመልክቷል።
ጥቃቱን የፈጸመው ግለሰብ፤ ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ደጀን ከተማ ሲጓዝ የነበረን " ገልባጭ " መኪና በማስቆም ከአካባቢው ያመለጠ ሲሆን " ኪዳነ ምህረት የሚባል አካባቢ ሲደርስ ወርዶ የገልባጩን ሹፌር በጥይት እንደመታው የኮሚኒኬሽን ቢሮው ሀልጿል።
ሁለቱ በጥይት የተመቱ ሹፌሮች በአሁን ሰዓት በደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንዳሉ ተገልጿል።
ለወረዳዋ ፖሊስ አዛዦች ህልፈት እንዲሁም ለሹፌቶቹ መቁሰል ምክንያት የሆነውን ተኩስ ከፍቷል የተባለ ተጠርጣሪን ለመያዝ ፍለጋ እየተከናወነ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

#Update
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲጠናቀቅ የጋራ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ምክክር መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።
በመድረኩ፦
- የትምህርት ሚኒስቴር፣
- የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች፣
- የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ ከሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በ102 የፈተና ጣቢያዎች የሚካሄደው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታውንና የክረምቱን የአየር ሁኔታ ያገናዘበ በርካታ የሰው ኃይል መመደቡን አሳውቋል።
ፈተናው ከሥርቆት በፀዳ መልኩ እንዲካሄድ ሁሉም ኃላፊነቱን ወስዶ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም ኮሚሽኑ አሳስቧል።
በአማራና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች በፈተና ጣቢያዎች የፀጥታ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቂ ዝግጅት ማድረጉንም ኮሚሽኑ አሳውቋል።
ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ፦
- የሀኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት በሽሮፕም ሆነ በታብሌት፣
- የህክምና መስጫ መርፌ፣
- የአንገት ሀብል፣
- የፀጉርና የጆሮ ጌጥ፣
- ከጋብቻ ቀለበት ውጭ ፈርጥ ያለው የጣት ቀለበት እና የእጅ አንባር አድርገው መምጣት እንደማይችሉ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በተጨማሪም ፦
- ተንቀሳቃሽ ስልክ፣
- አይ-ፓድ፣
- ታብሌት፣
- ላፕቶፕ፣
- ስማርት ሰዓት፣
- ሲዲ፣
- ሚሞሪ ሪደርና ኦ-ቲጂ ኮንቨርተር እንዲሁም ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።
የተከለከሉ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥም ሆነ በዙሪያው ይዞ መገኘት፣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት እንዲሁም በዩኒቨርሲቲ ግቢ ወስጥ በግልም ሆነ በቡድን ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው።
ይህንን ተላልፎ በተገኘ ተማሪ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ አንዳንድ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ ለተማሪዎች ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና በዞን ትምህርት ቢሮ አማካኝነት የፈተና መመሪያ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ መሆኑን አሳውቋል።
መረጃው የፌዴራል ፖሊስ ነው።

#አቢሲንያ_ባንክ
ጊዜ ፔይ በማንኛውም ዓይነት ስልኮች መገልግል የሚችሉት የሞባይል ዋሌት አገልግሎት ነው። *817# በመደወል አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
#BankofAbyssinia #BankingService #BankinginEthiopia #SavingAccount #EducationSaving #gizepay #mobilewallet #TheChoiceForAll #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ