TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አብና🕯

" የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! "

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል።

የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ?

" የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም።

በጉዳቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ ተደርጓል።

በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። " #አሚኮ

@tikvahethiopia