TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መግለጫ⬆️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አሕመድ #አሸንዳ/ #ሻደይ/ #አሸንድየ በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በየአመቱ ከነሀሴ 14 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በትግራይ ክልል #አሸንዳ፣ በአማራ ክልል በሰቆጣና በላሊበላ #ሻደይ#አሸንድየ በዓል በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ ልጃገረዶች/ ሴቶች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ጌጣ ጌጦች ተውበው ሹሩባ ተሰርተው በነጻነት የሚጨፍሩበት፣ የመሰላቸውን ሀሳብ በዜማቸው የሚገልጹበት ታላቅ ዕለት ነው።

©etv

በዓሉ እያከበራችሁ የምትገኙ የቻናላችን ቤተሰቦች ፎቶዎችን ልታደርሱን ትችላላችሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ

በአዲስ አበባ ደረጃ የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ፣ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ወ/ሮ ያለም ፀጋዬን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚኖሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

እንኳዕ ንበዓል ኣሸንዳ ኣብፀሐኩም!
Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ #ADDISABEBA በአዲስ አበባ ደረጃ የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም #በሚሊኒየም_አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በአዲስ ቴሌቪዥንና DW TV መከታተል ትችላላችሁ!

እንኳዕ ንበዓል ኣሸንዳ ኣብፀሐኩም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ

በአሸንዳ በዓል ዙሪያ የተደረገ ጥናት!

(መብራህተን ገ/ማሪያም)

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሚከበረው የአሸንዳ በዓል ፍቅር፣ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ነው።

በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል፤ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት ሃይማኖታዊና ባህላዊ በዓል ነው።

የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።

በዓሉ የሌሎች ሃሳቦች፣ጭፈራዎችና ትእይንቶችም እንዲታዩ የሚጋብዝ ከመሆኑ ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።

በአሸንዳ በዓል ላይ የሚነገሩ ስነ ቃሎች ይዘት በአብዛኛው ህብረትን የሚሰብኩ፣መድልዎን የሚጠየፉና ለሰው ክብርን የሚያጎናጽፉ ናቸው።

ልጃገረዶች በዓሉን በህብረሰቡ ውስጥ ያለውን እርስ በርስ የመተባበር፣የመረዳዳትና የጀግንነት መልካም እሴቶችን አጉልተው ለማሳየት ይጠቀሙበታል።

በዓሉ ሴቶች ያላቸውን የፈጠራ፣ የመደራደር፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት በተግባር የሚያሳዩበትና መልካም ስሜታቸውን የሚገልጹበትም ነው።

በተጨማሪ በህዝቡ ውስጥ ያሉትን ጉድለቶች በስነ ቃልና በዘፈን መልክ እንዲስተካከሉ የሚነቅፉበት፣ማህበረሰቡ መድልዎን እንዲጠየፍ፣የሴቶችን መብት የሚጋፋ የአስተዳደር መዋቅር አሊያም ወንድ ካለ እንዲስተካከል መልዕክት የሚያስተላልፉበት ጭምር ነው።

አሸንዳ በዓል ለትግራይ ህዝብ ባህል የመሰረት ድንጋይ ተደርጎ ይወሰዳል፤ በዓሉ ማንነትን አጉልተው የሚያሳዩ እሴቶች አሉት።

አሸንዳ ለሴቶች መብት አጥብቆ የሚታገል፣ መከባበርንና መረዳዳትን አብዝቶ የሚሰብክ፣ ሰዎች ባላቸው የሃብት መጠን ሳይሆን በሰውነታቸው ብቻ ክብር እደሚገባቸው በስነ ቃልና በዘፈን መልክ መልዕክት ይተላለፍበታል።

#Repost2013

@tikvahethiopia