TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሰሞኑን ተከታትለው የወጡት የተኩስ አቁም ጥሪዎች !

በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት በተከታታይ የተኩስ አቁም እና የድርድር ጥሪዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል።

1ኛ. #ሩሲያ፦ በድጋሚ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቃለች።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃለች ፤ ሰሞኑን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የተካሄዱት ጦርነቶች የሲቪል ዜጎችን ህይወት ጎድቷል ብለዋል።

ሩሲያ #የኢትዮጵያን_ግዛት_አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ብለዋል።

2ኛ. #ኬንያ ፦ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳስበዋል።

ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ጠይቀዋል።

ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል ኡሁሩ።

ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ያሉም ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

3ኛ. #ኢጋድ ፦ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዶ/ር ወርቅነህ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ከግጭት ተቆጥበው በመካከላቸው ያለውን መካረር እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

4ኛ. #ዩጋንዳ ፦ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሐገራት መሪዎች ጦርነቱ ሥለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሰበሰቡ ጠይቀዋል።

5ኛ. #አሜሪካ ፦ ዛሬም (ጥቅምት 26) አሜሪካ በድጋሚ በኢትዮጵያ ተኩስ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ማብቃት አለበት ፤ አሁኑኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድር መጀመር አለበት ብለል፤ ተኩስ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

6ኛ. #AU ፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ያወጡትን መግለጫ በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።

በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።

ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በሌላ መረጃ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ለድርድር የሚሆን ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ UN ፣ AU ፣ ኢጋድ ፣ አል አይን ኒውስ ፣ Daily Nation ፣ António Guterres (Twitter) ፣ BBC ፣ Antony Blinken (Twitter)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ ሩስያ ነዳጅ 300 ዶላር ሊደርስ ይችላል ብላለች። ሩስያ የምዕራባውያን መንግስታት ከሩስያ በሚገባው የነዳጅ አቅርቦት ላይ ክልከላ ከጣሉ የነዳጅ ዋጋ 300 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ገልፃለች። አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ለመጣል እያሰበች ነው። በአሁን ሰዓት በዓለም ገበያ ላይ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 140 ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህንም በ14 ዓመት ውስጥ የታየ ከፍተኛ ጭማሪ ነው።…
" ... የነዳጅ ማዕቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ ይሆናል፤ ዳፋውም ለዓለም ይተርፋል " - የሩስያ ምክትል ጠ/ሚ አሌክሳንደር ኖቫክ

አሜሪካ በ #ሩሲያ_ነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ የምታቀብለውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ ዝታለች።

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒትር አሌክሳንደር ኖቫክ ፤ የሞስኮን ነዳጅ ማቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ዳፋውም ለዓለም ይተርፋል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ማስጠንቀቂያቸው ሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ከተጣለ ምናልባትም የአንድ ድፍድፍ በርሜል የነዳጅ ዋጋ አስከ 300 ዶላር ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ ለመጣል አማራጮችን እያየች ነው።

ጀርመንና ኔዘርላንድስ ግን በሩሲያ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ማዕቀብ መጣል እኛኑ መልሶ ይጎዳናልና ይቅርብን እያሉ ይገኛሉ።

አውሮጳ ኅብረት ኃይል አቅርቦቱ በአመዛኙ የሚያሟላው ከሩሲያ ነው፡፡ በአማካይ ካየነው የአውሮጳ ኅብረት 40 % የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቱን እና 30 % የነዳጅ አቅርቦቱን የሚያገኘው ከሩሲያ ነው፡፡

የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኖቫክ ፤ የአውሮጳ ገበያ ሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ካቆመች ለከፍተኛ ችግር ይጋለጣል ብለዋል። " ተተኪ የኃይል አቅርቦት ለማግኘት ዓመታት ሊወስድባቸውም ይችላል ፤ ከኛ ይልቅ እነሱ ይጎዳሉ " ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በኢትዮጵያ ገዳይ መክሯል ?

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ #ኢመደበኛ_ዝግ ስብሰብ ያደርጋል ተብሎ ነበር። ስብሳባው ስለመደረግ አለማደረጉ እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለዚህ ስብሰባ የሚታወቀው ነገር የሚከተለው ነው ፦

- ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ መስከረም 2 (እኤአ) አይርላንድ ከአልባኒያ ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጋር በመሆን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በክፍት እንዲሰብሰብ ጠይቃ ነበር። አይርላንድ " በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት ምክንያት በረሃብ እየተሰቃዩ በመሆናቸው ለሰብአዊ ዕርዳታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በጣም ያሳስበናል " በሚል ነው ክፍት የሆነ ስብሰባ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርባ የነበረው፤ ሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና በአፍሪካ ህብረት (AU) ወደሚመራው የሰላም ንግግር እንዲመለሱ እንደምትፈልግ ነው የገለፀችው።

- የክፍት ስብሰባ ጥያቄው በ #A3 ሀገራት ማለትም #በኬንያ#በጋቦን እና #በጋና ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሀገራቱ ይህን የስብሰባ ይዘት የተቃወሙ ሲሆን የተስማማቱ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) እንዲካሄድ ነው። ይህም ኢትዮጵያ የምትመርጠው አይነት የስብሰባ ይዘት እንደነበር ተነግሯል።

ℹ️ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) ማለት ምንድነው ? IID መደበኛ ያልሆነ ዝግ ስብሰባ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ያልሆኑትን እንዲሳተፉ የሚያስችልም ነው። የዚህ  የስብሰባ ይዘት የስብሰባ መዝገቦች የሌሉት ሲሆን በም/ቤቱ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥም አይካተትም።

- አይርላንድ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ እና ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚጠይቅ ረቂቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭታ ነበር ሆኖም ግን #A3#ቻይና እና #ሩሲያ በረቂቅ ጽሑፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። ሀገራቱ መግለጫውን ከስብሰባው በኃላ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ነው የመረጡት ተብሏል። በዚህም በመግለጫው ላይ የነበረ ውይይት ባለበት እንዲያዝ ተደርጓል።

- ትላንትና ይካሄዳል የተባለው እና እስካሁን ተካሂዶ ስለመሆን አለመሆኑ በይፋ ያልታወቀው የተ.መ.ድ. ፀጥታ ምክር ቤት የIID ስብሰባ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ተቴህ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆም አጭር መግለጫ እንዲሰጡ ተጋብዘው እንደነበር ታውቋል ፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ተጋብዛ ነበር።

- ትላንት ለሊት በተያዘው እቅድም መሰረት ኢመደበኛ ስብሰባው (IID) መካሄዱ ከተረጋገጠ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረበት ነው የሚሆነው።

መረጃው ከSCR ፣ ከተመድ የአይርላንድ እና ኖርዌይ ተልዕኮ ፅ/ቤት የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia