" የፖለቲካ ሥርዓቱ እስካልተረጋጋ ድረስ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም " - ዶ/ር ዲማ ነጋዎ
ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ ባሰራጨው ዕትሙ ፤ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በግል ተወዳድረው ያሸነፉት፤ የሕ/ተ/ ም/ቤት አባል እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የም/ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ዲማ ነጋዎን ቃለ ምልልስ አድርጓል።
በዚህ ቃለምልልስ ፥ ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንዳለ በሚነገርባት ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ለዚህ ሕዝብ የሚመጥን ወጥ የሆኑ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲዎች መመሥረት ለምን አልተቻለም ? ሲሉ ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
ዶ/ር ዲማ ነጋዎ ፦
" አንደኛው ግለኝነት ነው፡፡ እስካሁን ባለኝ አረዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቡድን መሥራት ላይ ክፍተት አለበት፡፡ ለዚህ ማሳያ አንድ ምሳሌ ልጥቀስልህ፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የቡድን ስፖርትና የግል ስፖርት አለ፡፡ እኛ እንደ አገር የቡድን ስፖርት አሸንፈን አናውቅም፡፡ ነገር ግን በግል በሚደረገው የሩጫ ስፖርት ካየህ ልህቀት አለን፡፡
ወደ ፖለቲካ ስንመጣ ግን መሆን የነበረበት የቡድን ስፖርት ነበር፡፡ በቡድን አብሮ መሥራትና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንጂ፣ በቡድን ውስጥ እኔ ያልኩት ብቻ ከሆነ ግን አይሠራም፡፡ ሁሉም የሚያነሳው ጉዳይ ወደ አንድ መጥቶ ነው በጋራ የሚወሰነው።
በእኛ ፖለቲካ ውስጥ የምታየው እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን የሚለው ነገር ትልቅ ቦታ አለው፡፡
በፖለቲካ ደግሞ ግለሰቦች በምኞት የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ ብቻ የሚቀርፁበት ሁኔታ ይታያል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ሥራ የሚከናወነው አብዛኛው ሕዝብ ምን እንደሚፈልግ ተመሥርቶ መሆን አለበት፡፡
ማንኛውም ኅብረተሰብ ውስጥ ዳርና ዳር የቆሙ ሰዎች አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው ጫፍ የረገጡ ቡድኖች ናቸው፣ በቀኝም በግራም በኩል የቆሙ ማለት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የማኅበራዊ ሚዲያው እነዚህን ዳር የረገጡ ሰዎች ድምፅ እያጎላ ነው የሚሄደው፡፡
አብዛኛው ኅብረተሰብ በእጁ ስልክ አለው፣ እሷን ሲያዳምጥ ይውላል፡፡ በቃ ፖለቲካችን ያ ነው ለእኛ፡፡ ፖለቲካ ግን ከመሀል ነው የሚጀምረው፡፡ ይህ ማለት ከመሀል ገብተህ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ምን ዓይነት አስተሳሰብ ነው የሚፈልገው ? ምናልባት ሁላችንም የምንፈልገው አንድ ዓይነት ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህን ማቻቻልና ሁላችንንም የሚያስማማ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ ሥርዓትና ዕድገት በማምጣት፣ ይህንን ሕዝብ ከድህነት ማውጣት አለብን፡፡
የፖለቲካ ሥርዓቱ እስካልተረጋጋ ድረስ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም፡፡ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት በአገሪቱ የነበረው ጦርነት 5 ዓመት ነው ወደኋላ የመለሰን፡፡
የዛሬ አምስት ዓመት የነበርንበት ጊዜ ላይ ለመድረስ ወደፊት አሥር ዓመታት ያስፈልጉናል፡፡ ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት ይህ ነው ችግሩ፡፡
የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና ሕዝቡን ከድህነት ለማውጣት ሲታሰብ ከባድ ነው፡፡ አሁን አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ እኔ ምን በልቶ እንደሚያድር አላውቅም፡፡ በእውነቱ አንዳንዴ ለመገመትም ያስቸግራል፡፡
ድሮ ከተማው ውስጥ እንደነበረው አገልግሎት በገጠሩ ስላልነበረ፣ ገጠር ነበር በብዛት ሰው በድህነት የሚኖረው፡፡
አሁን አብዛኛው ደሃ ያለው ከተማ ውስጥ ነው፣ በተለይ ደግሞ ትልልቅ ከተሞች ውስጥ፡፡ የገጠሩን ስታይ ይብዛም ይነስም አርሶም ቆፍሮም የሚበላው ያገኛል።
አሁን አብዛኛው ሕዝብ #እያማረረ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከተማ ውስጥ የተከማቸውና በኑሮ ውድነቱ የተማረረ ሕዝብ ለፖለቲካ ሥርዓቱም አሥጊ ነው፡፡ ተገቢው ምላሽ መሰጠት አለበት። "
ሙሉ ቃለምልልሱ፦ www.ethiopianreporter.com/119191/
@tikvahethiopia