TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#በድጋሚ ጥንቃቄ! ለእናት ሀገራቹ ስትሉ ወጣቶች ከስሜታዊነት እርቃችሁ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ ተመልከቱ። ለውጡን የማይፈልጉ አካላት በሀገሪቱ አለመረጋጋት ለመፍጠር የሶሻል ሚዲያውን እየተጠቀሙበት ነው።

ቀላል ይሆናል!
ለውጥ ብዙ እንቅፋቶች አሉቱ!
ዛሬም ከወጣቱ መሪያችን ጎን ልንቆም ይገባል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#በድጋሚ የቀድሞው የኢ.ፌ.ድ.ሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ግርማ ወ/ጊዮርጊስን አስመልክቶ በፌስቡክ የሚሰራጩት መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው። ክቡር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሰላም ናቸው።

#ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

አዲሱ የአዲስ አበባ አስተዳደር የኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ቆጠራ #በድጋሚ እንዲካሄድ ትዕዛዝ መጠቱ ተሰማ፡፡

ካቢኔው ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ የመሬትና #መሬት ነክ አገልግሎት ዘርፍ #ኦዲት እንዲደረግ ወስኗል፡፡

በቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ ኩማ የሥልጣን ዘመን የኮንዶሚኒየም ቤቶችና የቀበሌ ቤቶች ቆጠራ ተካሂዶ የነበረ ቢሆንም አዲሱ አስተዳዳር “እንደገና ይቆጠር” ብሏል፡፡

©ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 12 የመማር ማስተማር ስራ ይጀምራል!

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክተር ዶ/ር አብድልዋሴ ሁሴን #በድጋሚ ለTIKVAH-ETH በስልክ እንዳሳወቁት ተማሪዎች ከመስከረም 5 ጀምሮ ወደ ግቢው መምጣት እንደሚችሉ ጠቁመው ከመስከረም 7-10 ባሉት ቀናት ምዝገባቸውን አከናውነው መስከረም 12 ትምህርት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።

TIKVAH-ETH ዶክተር አብልዋሴ ሁሴንን ለቀና ትብብራቸው ሊያመሰግናቸው ይወዳል!

TIKVAH ETH MAGAZINE የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎችን ብቻ በዚህ ተከታተሉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ATTENTION

ከሚያዚያ 29 እስከ ግንቦት 10 በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ፦

• ሚያዚያ 29/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ሚያዚያ 30/2012 ዓ/ም - ሶስት (3) ሰዎች
• ግንቦት 1/2012 ዓ/ም - አስራ ሶስት (13) ሰዎች
• ግንቦት 2/2012 ዓ/ም - ሃያ አንድ (21) ሰዎች
• ግንቦት 3/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 6/2012 ዓ/ም - አምስት (5) ሰዎች
• ግንቦት 7/2012 ዓ/ም - ስምንት (8) ሰዎች
• ግንቦት 8/2012 ዓ/ም - ሁለት (2) ሰዎች
• ግንቦት 9/2012 ዓ/ም - አራት (4) ሰዎች
• ግንቦት 10/2012 ዓ/ም - ሃያ ዘጠኝ (29) ሰዎች

በድምሩ 111 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል!

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አሁንም #በድጋሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ፤ መዘናጋት እና መሰላቸት የሚያስከፍለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#በድጋሚ

ቴሌግራም ላይ Tikvah-Marketና Tikvah-Mart በሚል በአጭበርባሪዎች የተከፈቱ እንጂ ትክክልኛ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስር ያሉ አይደሉም።

ገፆቹ በመቶ ሺዎች ሚቆጠሩ ሰዎች ያሉባቸው መሆኑን የተመለከትን ሲሆን ሁሉም ድርጊታቸው ከቲክቫህ ጋር የማይገናኝ እና ስራቸውም በስማችን ማጭበርበር ነው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ከመሰል አጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ በድጋሚ አደራ እንላለን።

በዚሁ አጋጣሚ በየዕለቱን የቲክቫህ አባል እየሆናችሁ ለምትገኙ በሺዎች የምትቆጠሩ ቤተሰቦቻችን በኛ ስር ያሉት ትክክለኛ ገፆች የሚከተሉት ናቸው ፦

🕊 @tikvahethiopia (ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethmagazine (ከ240 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethsport (ከ145 ሺህ በላይ አባላት ያሉት)
🕊@tikvahuniversity (ከ103 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 @tikvahethAFAANOROMOO (ከ19 ሺ በላይ አባላት ያሉት)
🕊 ቲዊተር twitter.com/tikvahethiopia?s=09

NB : ቲክቫህ ኢትዮጵያ Face book ሆነ አሁን ላይ አገልግሎት የሚሰጥ የYou Tube አካውንት በስሙ የለም።

ቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ሰብዓዊነትን ያስቀደሙ እና ሀገራቸው ኢትዮጵያን የሚያከብሩ እንዲሁም የሚወዱ ዜጎች መሰባሰቢያ መድረክ ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ክንውኖች ዙሪያ የእርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ ይደረግበታል።

ከየትኛውም የፖለቲካ ፣ የብሄር፣ የሃይማኖት ውግንና የራቀ ሲሆን ኢትዮጵያን እንደሀገር ያከበሩና ሀገሪቱን አደጋ ላይ የማይጥሉ የተለያዩ አመለካከቶች እንዲሁም አስተሳሰቦች ያሏቸውን ቤተሰቦቹን የሚያሰባስብ ነው።

@tikvahethiopia
#ችሎት

የቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎችም በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ እና እርሻ መሳሪያ ክስ ላይ የመከላከያ ምስክርነታቸው በአካል ቀርበው እንዲያሰሙ #በድጋሚ ታዘዘ።

ቀደም ሲል በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲመሰክሩ ታዞ የነበረው ትዛዝ ተቀይሮ ነው በአካል ቀርበው እንዲመሰክሩ የታዘዘው።

ከሁለት ወር በፊት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የእርሻ መሳሪያና የመርከብ ግዢ ሙስና ክስ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጥቶ ባለመቅረባቸው ምክንያት ታስረው እንዲቀርቡ መታዘዙ ይታወሳል።

" መጥሪያ ሳይደርሰኝ ታስሬ እንደበር የተሰጠው የፍርድ ቤት ትዛዝ ተገቢ አይደለም " ሲሉ ከኢትዮጲያ ውጪ እንደሚገኙና የስራ ጫና እንዳለባቸው አመላክተው በአካል ለመቅረብ እንደሚቸገሩ በመግለጽ ባሉበት ቦታ የምስክርነት አሰማሙ ቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲሆንላቸው ጠይቀው ነበር።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-07-04

Credit : Journalist Tarik Adugna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጉራጌ ዞን ምክር ቤት #በክላስተር_ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ፤ ዛሬ ሐሙስ ባካሄደው አስቸካይ ጉባኤ ከሌሎች የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር በክላስተር ለመደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አደርጓል። የጉራጌ ዞንን በደቡብ ክልል ስር ከሚገኙ ሌሎች 4 ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ ጋር በማዳመር የጋራ ክልል ለመመስረት የቀረበው…
#ተጨማሪ

" መንግስት የዞኑ ህዝብ በም/ቤት ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ ጥያቄ #በድጋሚ ሊያይ ይገባል " - የጉራጌ ዞን ም/ቤት

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በጉራጌ ዞን ዋና አስተዳደር የቀረበውን #በክላስተር የመደራጀት ምክረ ሐሳብ በአብልጫ ድምፅ #ውድቅ አድርጎታል።

የዞኑ ህዝብ በም/ቤቱ ያፀደቀው ህገመንግስታዊ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ ሊያይ ይገባል በሚል ነው ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ የክላስተር ውሳኔውን ምክረ ሀሳብን ውድቅ ያደረገው።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ህዳር 17/2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባኤ ዞኑ ራሱን ችሎ ክልል ለመሆን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት የሚከፍለውን የክልልነት አደረጃጀት በም/ቤቱ ባለማጽደቅ የጉራጌ ዞን #ብቸኛው ሆኗል።

ቀሪዎች የደቡብ ክልል 10 ዞኖች እና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ ላይ ሁለት ክልል የመመስረት ውሳኔን በምክር ቤቶቻቸው ማጽደቃቸው ይታወሳል። 

ፎቶ ፦ የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#የመምህራን_ቅሬታ #ምላሽ

ለ487 ' የአዲአርቃይ ወረዳ ' መምህራን የ22 ወራት የደረጃ ዕድገት ደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ማሳደሩን የሰሜን ጎንደር ዞን መምህራን ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፤ " በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን "  የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።

የሰሜን ጎንደር ዞን የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሀብታሙ አቸነፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- የመምህራንን #የመልካም_አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ የሆነ የፖለቲካ የመንግሥት አመራር ባለመፈጠሩ ምክንያት 487 የአዲአርቃይ ወረዳ መምህራን ከጥር 1/2014 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ በጊዜ ቆይታ የደረጃ እድገት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ይህ በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የቅሬታ ምንጭ ሆኖብናል።

- ለመምህራን ከጥር 01/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የደረጃ እድገታቸው እንደሚያድግና ለእድገታቸው የሚሆን በጀት ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሥማቸው ተይዞ ነበር። ይህንን በጀት ' አዘዋውረን ለሰላም ማስከበር አውለነዋል' ነው የሚለው የአስተዳደር ምክር ቤቱ።

- ጥያቄያችንን #በተደጋጋሚ አቅርበን ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት አካል አላገኘንም።

- ባለፈው ዓመት በወረዳው ላይ በነበረ አንድ ጉባኤ ' የመምህራን ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፣ በአዲሱ በጀት ዓመት ጥያቄውን እመልሳለሁ ' የሚል ምላሽን ሰጠ #አስተዳዳሪው። በዚህ ዓመት ደግሞ ፦
* ሀምሌ፣
* መስከረም፣
* ጥቅምት ወራት ላይ ተጠየቀ አሁን የመጨረሻው ውሳኔ ' እኔ በጀቱን አላውቅም ፣ በወቅቱ የነበረውን አስተዳዳሪ በጠየቃችሁ ፣ እኔ አሁን የምከፍልበት ኮንዲሽን የለም ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው ፤ በዚህ መምህራን በጣም #ተበሳጭተው ነው ያሉት።

- መምህራን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለመጠየቅ ሲሄዱ 'እናስራችኋለን፣ እንመታችኋለን' የሚል ተፅእኖ አለ።

- በወቅቱ የነበረው ችግር የሁላችንም ችግር ቢሆንም ደመወዝ ቀጥታ ተከፋይን አንስቶ ' ለሰላም ማስከበር ' በሚል ላለአስፈላጊ ጥቅም ማዋል ተገቢ አይደለም። ላለአስፈላጊ ጥቅም ነው የዋለበት ያልኩት ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኮማንድ ፖስት የትዕዛዝ አቅጣጫ ተሰጥቶ የነበረው ሁሉም ደመወዝ ለሰላም ማስከበር ይሆናል የሚል ሳይሆን፣ 'የሥራ ማስኬጃ 40%ን ተጠቀሙ' የሚል ስለነበር ነው።

- እንደ 'ሰሜን ጎንደር ዞን' ብዙ ወረዳዎች ተሳትፈዋል በጦርነቱ። ጠለምት ተሳትፏል፣ ዳባት ተሳትፏል ነገር ግን አንድም ከበጀት ጋር የተያያዘ ደመወዝ የተነሳበት ወረዳ የለም። በዞናችን አሥር ወረዳዎች አሉ ሙሉ በሙሉ የደረጃ ዕድገታቸውን እየከፈሉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። #አዲአርቃይ ግን እንዲህ አይነት ችግር ገጥሞናል።

- ያልተከፈለውን የደረጃ እድገት ምን ያህል እንደሆነ አላሰላሁትም፣ ግን ቢያንስ ለ487 መምህራን ዝቅተኛ 800፣ ከፍተኛ እስከ 2,000 ብር የደረጃ እድገት ያገኛሉ። ነገር ግን ይኸው እንግዲህ አሁን ጥር ወር ሲገባ 2 ዓመታት ሊሆነው ነው ሳይከፈል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ " የመምህራኑን #የደረጃ_እድገት ደመወዝ ለምን እስካሁን ድረስ አልተከፈለም ? " ሲል የአዲአርቃይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ ጆርጌ ጠይቋል።

አቶ አረቡ ጆርጌ " አሁን ያለበት ሁኔታ በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " ሲሉ መልሰዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " መምህራኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እንዳልተከፈላቸው፣ በመጨረሻም በጀቱ ለሌላ ጥቅም እንደዋለ " እንደገለፁለት ለኃላፊው #በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።

በተጨማሪ ፦

* ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለምን ገንዘቡን አልከፈላችሁም ?

* አሁን ለመክፈልስ ምን የታሰበ ነገር አለ ? ብለን ጠይቀናቸዋል።

ኃላፊው " ኦሬዲ ጠይቀዋል በጀት ተይዞ እንደሚከፈል ብቻ ነው የነገርናቸው እንጂ ለዚህ የተመደበ #ለሌላ ጥቅም የዋለ ገንዘብ የለም " ብለዋል።

" መከፈሉ ግዴታ ነው፣ እንደ ተቋም እንደ አስተዳደር ምክር ቤትም ' አይከፈልም ' የሚል ማስተባበያ አይኖረንም ምክንያቱም ደመወዝ ስለሆነ " ያሉት ኃላፊው፣ " ለሁለት ዓመታት ያክል የገቢ መሰብሰብ ችግር ስለነበር በጦርነቱ ምክንያት በጀቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነው ያሳደረው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ስለዚህ እኛም አሁን የያዝነው ፕሮግራም ሙሉውን እንኳ ባይከፈል እየተከፈለ (የአመቱን ወደ 6 ወራት፣ የ6 ወራቱን ወደ ሦስት ወራት እየተደረገ በጀት እየያዝን እንከፍላለን እንጂ አይከፈልም የሚል አቋም የለም። ተገቢነትም የለውም " ብለዋል።

መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የዛሬውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን አወደሱ። አቶ ጌታቸው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር በትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው ብለውታል። ዛሬ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያሳለፈው " የኢትዮጵያ የምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ…
#Update

ፓርላማው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን / በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድለትን የአዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።

" የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን " የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በ2 የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።

" በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ " የፖለቲካ ፓርቲዎችን " በልዩ ሁኔታ " እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው።

የጸደቀው የአዋጅ ማሻሻያ ፥ " ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል " በሚል " ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ " የተደረገው ህወሓት #በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።

" አንድ የፖለቲካ ቡድን ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጽ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እንደሆነ እና ይህንን ተግባር ማቆሙን እና ሕገ መንግስታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን አክብሮ ለመንቀሳቀስ መስማማቱ በሚመለከተው የመንግስት አካል ከተረጋገጠ፣ የፖለቲካ ቡድኑ በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ሊመዘገብ ይችላል " ሲል አዋጁ ደንግጓል።

#EthiopiaInsider
#TPLF

@tikvahethiopia