TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ " መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝበ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍፅም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ እናወግዛለን " ብሏል። ምክር ቤቱ ፤ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም…
#Update

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሒምን ጨምሮ የአዲስ አበባ መጅሊስ ፕሬዝዳንት ሀጅ ሱልጣን አማን እንዲሁም ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በትላንትናው እለት በጸጥታ አካላት ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል እያገኙ ያሉ ሙስሊሞችን ሆስፒታል በመገኘት መጠየቃቸውን ሀሩን ሚዲያ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፥ በትላንትናው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ ልዑክ በታላቁ አንዋር እና ኑር ( ሰፈር በኒ) መስጂዶች ከጁምዓ ሰላት በኃላ  በሸገር ከተማ አስተዳደር  "በሕገ ወጥ" ስም የፈረሱ መስጂዶች  ተቃውሞ ለማሰማት በወጡ ምዕመናንና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል የተፈጠረውን ችግር  በተመለከተ ወደ ፌደራል  ፖሊስ ኮሚሽን ዋናው መስሪያ  ቤት በማቅናት ከኮሚሽኑ የስራ ኃላፊዎች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዉይይቱ መሰረትም በጊዜያዊነት በፖሊስ ተዘግቶ የነበረው ኑር (ሰፈር በኒ) መስጂድን ለሰላት ክፍት ማድረግ ተችሏል።

በቀጣይ የተፈጠሩ ችግሮችን የሚያጠናና የመፍትሔ አማራጮችን ለሚመለከተው የመንግስት አካል የሚያቀርብ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ኮሚቴው ፤ ከጠቅላይ  ምክር ቤቱ ፣ከአዲስ አበባ  እና ከኦሮሚያ  እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ከእያንዳዳቸው ሶስት አባላት ያሉት ሲሆን ስራም እንደጀመረ ተነግሯል።

ሰላም ወዳዱ ሙስሊሙ ማህበረሰብ  በሁለቱ ተቋማት የተቋቋመው  መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የደረሰበትን ውጤት እስኪያሳውቅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቅ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ጠቅላይ ምክር ቤቱ #በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አስቸኳይ ጉባዔ ተቀምጧል። 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

አስቸኳይ ጉባዔው በዑማ ሆቴል እየተካሄደ  ሲሆን መርሀ ግብሩን በቁርዓን የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማምና ኻጢብ በሆኑት በሼይኽ  ጧሐ ሙሀመድ ሐሩን መከፈቱ ተገልጿል።

የጠቅላላ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ይህንን ጉባዔ ስናካሂድ በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶች  የፈረሱበት የመስጂዶችን ፈረሳ ለመቃወም ከወጡ ሰዎች ዉስጥ መስዋት የሆነበት ጊዜ ነው ብለዋል።

" መስጂዶች የአሏህ ቤቶች ናቸው። ይህ ክስተንን ከሚመለከተው  አካል ጋር ለመመካከር የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።

" ሙስሊሞች  የሀገር የሰላም ዘብ ናቸው " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " በሸገር ከተማ እየፈረሱ ያሉትን መስጂዶች ጉዳይ በሚመለከት  ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ መቅረቡን አስታውሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ ነገሮችን ወዳልተፈለገ መልኩ በሚወስዱ ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ የሚፅፉ  አንዳንድ  አካላትን ከተግባራቸው  እንዲቆጠቡ  አሳስበዋል።

" በመንግስት ዉስጥ ሆነዉ መንግስትና ሕዝብን የሚያጋጩ አካላት በሕገ ተጠያቂ መሆንን ይኖርባቸዋል "ም ብለዋል።

በትላንትናው  ዕለት  በሸገር ከተማ በ " ሕገ ወጥ " ስም የፈረሱ መስጂዶችን  ለመቃወም ወጥተው መስዋዕት የሆኑ  ወንድሞች አሏህ ጀነተል ፍርዶስ እንዲወፍቃቸው ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መፅናናት እንዲሰጣቸው ጉዳት የደረሰባው ወገኖቻችን ከደረሰባቸው ጉዳት አፊያቸውን እንዲመልስላቸው ፕሬዜዳንቱ ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በጉባዔው የኦሮሚያና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ሪፖርታቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ባለ አስራ አንድ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባዔዉን አጠናቋል።

ከአቋም መግለጫዎቹ መካከል ፦

- በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአንዋር እና በኑር መስጂዶች የተፈጠረው ክስተት #እንዴት_እንደተፈጠረና የደረሰውን ሞትና ጉዳት መንስኤዎች የሚያጣራ ከመንግስትና የእስልምና ጉዳይ ም/ቤት በጋራ ያሉበት ገለልተኛ አጣሪ ቡድን #በአስቸኳይ እንዲቋቋም ተጠይቋል።

- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በ " ሸገር ከተማ " ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት #ምትክ_ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በሌሎች የሀገራችን ክልሎች ለእምነት ቦታዎች ተገቢውን ክብርና ጥበቃ እንዲደረግ፥ እንዲሁም ለመስጂዶች ካርታ በመከልከልና ሆነ ብሎ ቢሮክራሲውን በማንዛዛት ሕዝቡን ላማረሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መንግስት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በአፋጣኝ እንዲፈታቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

- ሕዝበ ሙስሊሙ ከመሪ ተቋሙ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ጎን በመቆም ሃይማኖታዊ መብቶችን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

- መንግስት ኢስላም ጠል የሆኑ እና በመንግስት መዋቅር ዉስጥ በተለያዩ እርከኖች ያሉትን አካላት በመገምገም እና በማጥራት ሕዝብንና መንግስትን ሆነ ብለው ለማጋጨትና ሀገሪቷን ወደ ለየለት ቀውስ ለመውሰድ እየሰሩ ያሉ አካላትን ፈትሾ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ መዋቅሩን እንዲያጠራ ጥሪ ቀርቧል።

(ዝርዝር የአቋም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

" 522 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ፤ የተገኘው ሀብት ግን ዝቅተኛ ነው " - የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ

በአማራ ክልል ፤ #በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ ለመገንባት 522 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ሲል የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ የመንግሥትና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዓመታዊ የአጋርነት የምክክር መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።

ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰተው ችግር 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዜጎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በክልሉ እንደሚገኙ የገለፀው ቢሮው ፤ 11 ነጥብ 4  ሚሊዮን ሕዝብ  ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ  የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

ሰባት ዞኖችና ሶስት ሜትሮፖሊታንት ከተሞች በጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸእ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን ዞኖች መልሶ ለማቋቋም እና  መልሶ ለመገንባት ከ522 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል ብሏል።

ጉዳት የደረሰባቸውን ዞኖች  መልሶ ለመገንባት ጥረት ቢደረግም  የተገኘው ሀብት ዝቅተኛ በመኾኑ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት አለመቻሉን ቢሮው አመልክቷል።

ቢሮው ፤ መንግሥት ከሚያደርገው ሥራ ባለፈ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በተለያዩ የልማት ሥራዎች እና በመልሶ ግንታ ሥራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህ ዓመትም በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች 374 ፕሮጀክቶች በክልሉ እየተከናወኑ ነው ተባቧል።

ድርጅቶች በቀጣይም የጀመሩትን ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ፤ ዛሬ በላከልን መግለጫ መንግስት ከጁመዓ ሰላት በኃላ በምዕመናን ላይ እርምጃ መውሰዱንና ይህንንም በፅኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

ፓርቲው ፤ " ባለፉት ጥቂት ወራት በ ' ሸገር ከተማ ' እየተካሄደ ያለውን ' ህገወጥ ' መስጂዶችን የማፍረስ እርምጃ በሰላማዊ መንገድ በመቃወም በአዲስ አበባ በተለይ በአንዋር መስጂድ ከጁምአ ሰላት በኃላ ድምጻቸውን ባሰሙ ሙስሊሞች ላይ በተወሰደው እርምጃ የሰው ህይወት አልፏል ፣ በርካታ ምዕመናን ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል " ያለ ሲሆን " የተወሰደው የእብሪት እርምጃ ነው ፤ ይሄንንም በፅኑ እናወግዛለን " ሲል አሳውቋል።

መንግስት ከሀይማኖት ተቋማት ላይ እጁን እንዲያነሳ ፣ የሀይማኖት እና የመንግስትን ህገመንግስታዊ ልዩነት እንዲያከብር ፓርቲው በላከልን መግለጫው ጠይቋል። 

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ፦

- መንግስት የጀመረው መስጊዶችን የማፍረስ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ተባባሶ ወደ ከፋ ሀገራዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር ከመቀየሩ አስቀድሞ እርምጃውን በአስቸኳይ እንዲያቆም፣ እስከ አሁን ለደረሱ የህይወት፣ የንብረት እና የስነ ልቦና ጉዳቶች ህዝብን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

- ዜጎች የመንግስትን የተሳሳቱና ብልሹ አሰራሮችን የመቃወም ህገ መንግስታዊ መብታቸውን እንዲያከብር፣

- መንግስት በሀይማኖት ተቋማት ላይ በሚወስደው ኢ -ህገ መንግስታዊና ኢ-ዴሞክራሲያዊ ጣልቃ ገብነት ሀገራችን ወዳልተፈለገ የፖለቲካ ቀውስ መግባቷን ከቅርብ የሀገራችን ታሪክ ትምህርት በመውስድ ራሱን እና ሀገራችንን ከቀውስ እንዲታደግ፣

- መንግስት ራሱ ከፈጠረው ተምኔታዊ የብልጽግና እና ልዕልና ትርክት በተቃራኒ ሀገራችን በተጨባጭ ያላችበትን ጥልቅ እና አሳሳቢ የደህንነት፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውሶችን ከግምት ያስገባ፣ ዜጎች ያሉበትን የከፋ ድህነት እና ስራ አጥነት፣ አድሏዊ እና ብልሹ አሰራር፣ ሙስና፣ በሰላም ወጥቶ የመግባት ስጋት፣ . . . ችግሮችን ያገናዘበ ፈጣን እና ስር ነቀል የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ሀገሪቱን ከከፋ የፖለቲካ ቀውስ እንዲታደግ አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
በሲቢኢ ብር ነዳጅ ሲቀዱ ሁለት አማራጮች አሉ!
***************

 የመጀመሪያው

ራስዎ ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያዎ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ክፍያ ፈጽመው ነዳጅ የሚቀዱበት ነው፡፡

 ሁለተኛው

ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹ የሰሌዳ ቁጥርዎን እና የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ የሚቀዱበት አማራጭ ነው።

****************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#EthiomartShopping

ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ : 0911582926

security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ) ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ።

- 4 ካሜራዎች :- 4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች :- 8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር

ቦሌ መድሀንያለም ቤዛ ህንጻ 208
#ነዳጅ

ለመጪው የ2016 ዓ/ም ወደ አገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ለማስገባት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ " ቪቶል " የተባለው የባህሬን ኩባንያ በድጋሚ በማሸነፉ የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2016 ዓ.ም. ለማስገባት ያቀደውን ሙሉ ለሙሉ ቤንዚን፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የነጭ ናፍጣ ግዥ 40 በመቶውን " ቪቶል " ኩባንያ እንደሚያስገባ ታውቋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ለ1 ዓመት የሚያስፈልገውን 760 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ኩባንያው ያቀርባል፡፡

" ቪቶል " ጨረታውን ያሸነፈው ከሁለት ሌሎች ኩባንያዎች ጋር ተወዳድሮ እንደሆነ ተነግሯል።

" ቪቶል " እየተጠናቀቀ ላለፈው የበጀት ዓመት በተመሳሳይ የወጣውን ጨረታ አሸንፎ ሲያቀርብ ነበር።

ለ2016 በጀት ዓመት ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው ነዳጅ ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በስምንት በመቶ ብልጫ አለው፡፡

በተናጠል ሲታይ ቤንዚን ስምንት በመቶና ነጭ ናፍጣ አምስት በመቶ ጭማሪ ይኖራቸዋል፡፡ 

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ። እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት…
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው "

ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የግለሰቡን መታሰር መሰል ወንጀሎችን የፈፀሙ ከፍትህ ማምለጥ እንደማይችሉ ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።

ጉተሬዝ ፤ " እንዲህ አይነት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎች ከፍትህ ሊያመልጡ እንደማይችሉ እና ከሩብ ምዕተ አመት በኋላም ቢሆን #ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሚያሳይ ኃይለኛ መልእክት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

እ.አ.አ በ1994 በሀገረ ሩዋንዳ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800 ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሜ ህዝቡ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል።

በአሁን ሰዓት የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል።

እስካሁን ባለው 96.01 በመቶ የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ በተካሄደ ቆጠራ ፦

- ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.28 % 
- የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.72 % ድምፅ አግኝተዋል።

በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ተወዳዳሪዎች የሚፈለገውን ያህል  ድምጽ (ከ50 በመቶ በላይ) ማግኘት ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ እንደሚደረግ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሜ ህዝቡ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል። በአሁን ሰዓት የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል። እስካሁን ባለው 96.01 በመቶ የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ በተካሄደ ቆጠራ ፦ - ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.28 %  - የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.72 % ድምፅ አግኝተዋል። በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ተወዳዳሪዎች የሚፈለገውን ያህል …
#UPDATE

በቱርክ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አሁናዊ የድምፅ ቆጠራው 97.94 በመቶ ደርሷል / የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ ቆጠራ ተካሂዷል።

በዚህም የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን 52.14 % በመቶ ድምፅ ምርጫውን እየመሩ ሲሆን የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.86 % ድምፅ በማግኘት እየተከተሏቸው ነው።

ከወዲሁ የሀገራት መሪዎች ለአሁኑ ፕሬዜዳንት የ " #እንኳን_ደስ_አልዎት " መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia