TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።…
#Update

የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።

ሕጉ ምን ይዟል ?

- ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል።

- በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ #የረጅም_ጊዜ_እስር ይጠብቀዋል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል።

- በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው።

ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ ለፓርላማ የቀረበው ይህ ሕግ በከፍተኛ ድምጽ ነው ትናንት ማክሰኞ የጸደቀው።

ከዚህ በኋላ ሕጉን የመሻር ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሲሆኑ ሕጉ ላይ በፈረሙ ቅጽበት ተፈጻሚነቱ ይረጋገጣል።

ከቀናት በፊት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው " ሲሉ አሳስበው ነበር።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኡጋንዳ

" ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ #አይፈርሙ " - ተመድ

" ህጉ ኤችአይቪ/ኤድስን በመዋጋት ረገድ የተገኘውን ውጤት ሊቀለበስ ይችላል " - አንቶኒ ብሊንከን (የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ከቀናት በፊት ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት / አፍቃሪዎች ጋር በተያያዘ የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ ተቃወመ።

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በሕግ አውጭዎች ማክሰኞ የፀደቀውን ህግ እንዳይፈርሙ በይፋ ጥያቄ አቅርበዋል።

ኮሚሽነሩ ህጉን " ጨካኝ ህግ " ሲሉ ጠርተው በአጠቃላይ በህብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እና የሀገሪቱን ህገ መንግስት እንደሚጥስ ገልጸዋል።

እኚሁ የተመድ ባለስልጣን ፤ ፓርላማው ያሳለፈው ይኸው ህግ አድሎአዊ ነው ብለው " ምናልባትም በዓለም ላይ ካሉት እጅግ በጣም አስከፊው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳት ሙሴቬኒ በህጉ ላይ እንዳይፈርሙም ጠይቀዋል።

የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ የተለያዩ ምዕራባውያን ሀገራት እየተቃወሙ መሆናቸው ይታወቃል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ውሳኔውን ተቃውመው ያሰራጩት መልዕክት በብዙሃን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ብሊንከን ህጉን " የኡጋንዳውያንን መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች የሚገታ እና ኤችአይቪ/ኤድስን በመዋጋት ረገድ የተገኘውን ውጤት ሊቀለበስ ይችላል። " ሲሉ ነው የገለፁት።

" የኡጋንዳ መንግስት የዚህን ህግ ተግባራዊነት እንደገና እንዲያጤነው #እናሳስባለን" ም ብለዋል።

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሞሴቬኒ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሀገሪቱ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ምንም አይነት ቦታ እንደሌላት ገልፀዋል።

ከቀናት በፊትም በፓርላማ ባሰሙት ንግግር #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉም ነው የገለፁት።

ፕሬዜዳንቱ ፓርላማው ባፀደቀው አዲሱ ህግ ላይ ፊርማቸውን ይኖራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ፤ ልክ ፊርማቸው እንዳረፈ በቅፅበት #ተግባራዊ ይሆናል።

በአዲሱ የኡጋንዳ ህግ ፦

- በኡጋንዳ ምድር ማንም ሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ በሚል ማንነቱን ቢገልፅ ህይወቱን ሙሉ / ለበርካታ አመታ እስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ ይሆናል።

- በአንዳንድ ሁኔታዎች #ሞት ያስፈርዳል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን ይጥላል።

- ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይፀናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

@tikvahethiopia