TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል።

በጦርነት ምክንያት በክልሉ ያሉት ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኃላም ተማሪዎችን በፍጥነት ወደ ቀደመው የትምህርት ህይወታቸው እንዲመለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ዘግይቷል።

ከሰሞኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት እስኪጀመር #በሬድዮ እና #ቴሌቪዥን ትምህርት እንዲጀመር ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ስለማሳወቁ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅድሚያ ትንንሽ ህፃናት ላይ ትኩረት እንዳደረገ የገለፀው ቢሮው ይህም በአቅም ውስንነት እና በጀት ስለሌለው መሆኑን አመልክቷል። በሚዲያ ትምህርቱን ከመዋለህፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጿል።

የሬድዮ ትምህርት በድምፂ ወያነ፣ የቴሌቪዥን ትምህርት በትግራይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል ተብሏል።

ትምህርቱ ፤ የትግራይ ህፃናት በጦርነት ከደረሰባቸው ጫና እንዲወጡ ለማድረግና ለመደበኛው ትምህርት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ እንጂ ከክፍል ወደ ክፍል የሚያሻግራቸው እንዳልሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሬድዮ እና ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ትምህርት በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ ፤ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በሬድዮ የሚሰጠው ትምህርት ትግርኛ ፣ እንግሊዘኛ እና አካባቢ ሳይንስ ሲሆን በቴሌቪዥን ሒሳብን እንደሚያካትት አሳውቋል።

@tikvahethiopia