TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ እናሳጥራለን " - ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ትግራይ ውስጥ ትምህርት የሚጀምርበት ቀን ይፋ ተደርጓል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለ4 ዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ቀን ቆርጧል። የመንግሥትም ይሁን የግል ተቋማት ከሚያዚያ 18 /2015…
#Tigray

ከዓመታት በኃላ በትግራይ ያሉ #ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ምዝገበ እየተካሄደ ይገኛል።

የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ለዓመታት በኮቪድ-19 እና በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር ከሚያዚያ 18 ጀምሮ ምዝገባ እንደሚከናወን እና ሚያዚያ 23 ትምህርት እንደሚጀመር ማሳወቁ የሚዘነጋ አይደለም።

ተማሪዎች ያለፋቸውን ጊዜ ለማካካስ በሳምንት 3 የትምህርት ፕሮግራሞች የነበሩትን ወደ 5 እና 6 በመቀየር አንድ ሴሚስተር የሚጨርሰውን ጊዜ ለማሳጠር እንደሚሰራ መነገሩም ይታወሳል።

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

እንደ ህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) መረጃ በትግራይ 2.3 ሚሊዮን ሕጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
#BerhanBank

We Are Hiring!

Berhan Bank seeks to hire applicants for the positions of
1. Customer Service Officer
2. Junior Customer Service Officer

Link; https://t.iss.one/berhanbanksc
#ቴክኖ_ሞባይል

በስፓርክ 10 ሲሪየስ  ፎቶ ሲያነሱ፣ ቪዲዮ ሲቀረፁ፣ ጌም ሲጫወቱ፣ ስለ ባትሪ እንዳያስቡ !

አንዴ ቻርጅ ከተደረገ ረጅም ሰዓታት እየተጠቀሙበት የሚቆይ፥ በፍጥነት ቻርጅ ማድረግ የሚችል አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 10 ሲሪየ ከ 5000 mAh ባትሪ ጋር እና በ18 ዋት ፈጣን የኃይል መሙያ ድጋፍ ጋር ቀርቦሎታል። ፎቶ ሲያነሱ፣ ቪዲዮ ሲቀረፁ፣ ጌም ሲጫወቱ፣ ስልክ ላይ በመነጋገር ቢቆዩ ቴክኖ ስፓርክ 10 ሲሪየስ ባትሪ ንቅንቅ አይልም።

በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro
#IOM

እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል።

ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14 በመቶ ናቸው።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ 200 የነበረው የስደተኞቹ ቁጥር  ያለፈው ማክሰኞ ወደ 1,300 ደርሷል።

ድርጅቱ በሱዳን ድንበር ላይ ለሚደርሱ 700 ያህል የሶስተኛ ሀገር ዜጎችን ለመቀበል የትራንስፖርት እርዳታ በርካታ ኤምባሲዎች ጥያቄዎች  እንዳቀረቡለት ታውቋል።

የአይኦኤም ባለስልጣናት ከድንበር ከተማ መተማ ወደ ጎንደር እና አዲስ አበባ ከተሞች የሚመጡ ስደተኞች መብዛትን ተከትሎ  ትራንስፖርት በማዘጋጀት ላይ ናቸው።

ድርጅቱ የሱዳኑ ግጭት  270,000 የሚደርሱ ሰዎችን ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ፣ ቻድ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ እንዲሰደዱ ሊያደርግ ይችላል ብሏል።

በሱዳን ወታደሮች እና ታጣቂዎች መካከል የተደረገው ጦርነት ሚያዝያ 15 ቀን 2023 ከተቀሰቀሰ ወዲህ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲሞቱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል።

በርካታ የሀገሪቱ ዜጎችም በከፍተኛ የውሃ፣ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የነዳጅ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።

በሌላ በኩል፤ ከቀናት በፊት በተፋላሚ ወገኖች ስምምነት የተደረሰበት የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ለተጨማሪ ቀናት እንዲራዘም የተደረገ ቢሆን አሁንም በሀገሪቱ ግጭት ቀጥሏል።

ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም የተደረገው በሱዳን ጎረቤት አገራት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት፣ በአሜሪካ እና በዩናይትድ ኪንግደም ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ / ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia
#MoE #ExitExam

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች #በኦንላይን ለሚካሄደው የመውጫ ፈተና 30 ሺህ ኮምፒውተሮች ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከ240 ሺህ በላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። 

በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ድግሪ የማይሰጣቸው በመሆኑ ተማሪዎች ለሚሰጠው ፈተና ራሳቸውን አንዲያዘጋጁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በሀምሌ ወር ከሚሰጠው ፈተና በፊት በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ የሙከራ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ በኦንላይን ፈተናው መሰጠቱ ኩረጃን ለማስቀረት፣ የወረቀት ወጪና ማጓጓዣን ለመቀነስ ይረዳል ብሏል።

ለፈተናው በአጠቃላይ ከ15 በላይ ኮርሶች በየትምህርት መስኩ ተወጣጥተው ዝግጁ መሆናቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ " የፈተናው ውጤት በኦንላይን ይፋ የሚደረግና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ይሆናል " ብሏል።

ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች ያለገደብ በተደጋጋሚ የመፈተን እድል እንደሚኖራቸው በመመሪያ መቀመጡን ያስታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር " የመውጫ ፈተናው የተለየ ዓላማ የሌለው እና የተማሩትን ብቻ የሚመዝን በመሆኑ ተማሪዎች ሳይደናገጡ እንዲዘጋጁ ለተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመፈተኛ ጣቢያ እንደሚሆኑ ይፋ ተደርጓል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ማይ_ዊሽ_ኢንተርፕራይዝ

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዶሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://t.iss.one/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
ህጻናትን መሬት ላይ ሸፋፍኖ፣ አስተኝቶ መለመን ... የልመና ስልት ይሆን ?

በመዲናዋ ብዙ አይነት የልመና አይነቶችን እንመለከታለን። አንዳንዶቹ ልመናዎች ግን ህጻናትን ጭምር በመጠቀም የሚደረጉ በመሆናቸው ልብን ሰብሮ ምጽዋት ከመስጠት ባለፈ ጥያቄ ይጭራል።

በተለይ መገናኛ አካባቢ ህፃናትን አስተኝቶ መለመን መለመዱን ጥቆማውን ያደረሱን ቤተሰቦቻችን የገለጹ ሲሆን ጨቅላ ህፃን አስፓልት ላይ አስተኝቶ መለመን ለጤናም ሆነ ለሞራል የሚከብድ ነገር እንደሆነ ነው የጠቀሱት።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሴቶችና ህጻናትጉዳዮች ቢሮን አነጋግሯል ፦

ጉዳዩ እንደ ቢሮ በሚገባ ይታወቃል፤ ለኛም በጣም አሳሳቢ እና አስጨናቂ ጉዳይ ሲሉ በቢሮው የህጻናት መብት ደህንነት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ አንዷለም ታፈሰ  ይገልጻሉ። ሆኖም ቢሮው ክልከላ የማድረግ ወይንም የህግ አግባብን ለመተግበር ግን ስልጣን እንደሌለው ነው ያነሱት።

ዳይሬክተሩ አክለውም "እየከፋ እየመጣ ያለው ልመናን በወንጀል ደረጃ አስቀምጦ ወይንም አላግባብ የሆነ የልመና ሂደቶችን ክልከላ ያስቀመጠበት ህግ ስለሌለን እነዚህን እናቶች ወጥታቸሁ አትለምኑም ማለት አንችልም" ሲሉ ተናግረዋል።

ለመሆኑ ህጻናቱን ለልመና ብለው የሚሰርቁት ለዚሁ ይሆን ?

እንደ ቢሮው መረጃ ልጅ ጠፋ ሚባሉ ነገሮችን በተደጋጋሚ እንደሚሰማና አንዱ ልጅ የሚጠፋበትም ምክንያትም ለገቢ ማስገኛ ዘዴ እነደሆነ ይጠቁማል፡፡

ለምሳሌ በ2014/15 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት 58 አካባቢ የሚሆኑ ልጅ የመጥፋት ኬዞች የተመዘገቡ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በሁለት መንገድ ሕጻናቱን በመስረቅ ለገቢ ማስገኛ እንደተጠቀሟቸው ተገልጿል።

የመጀመሪያው ልጅን አግቶ ገንዘብ መደራደር አይነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አሁን እንደምናየው በተለያየ መንገድ ልጆቹን በመውሰድ ለልመና እንደሚጠቀሟቸው እንሰማለን፡፡

ቢሮው ችግሩን ለመቅረፍ የህግ ማዕቀፍ እያዘጋጀው ነው ብሏል።

የህጻናት መብት ደህንነት ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ አንዷለም ታፈሰ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል ይህንን ድረጊት በህግ ሊከለክል የሚችል (ሊያስቆም የሚችል) አዋጅ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑንና ረቂቁ ማለቁን ጠቁመዋል።

ይህ አዋጅ ተተግብሮ ወደ ሥራ ከተገባ ትልቅ እፎይታ ይፈጥራል ብለው እንደሚያስቡ የገለጹት ዳይሬክተሩ አዋጅ ተግባራዊ እስከሚደረግ ድረስ ቢሮው መመሪያ ማዘጋጀቱን አንስተዋል።

ለመሆኑ መመሪያው ላይ ምን ተካቷል?

መመሪያው ህጻናትን የያዙ እናቶች ልጆቻቸውን የቀን ማቆያ ውስጥ ማዋል እንዲችሉ፤ ምቹ በሆነ ቦታ ላይ ህጻናቱን አድርገው የተለያዩ ገቢ ሚያስገኙ ስራዎቹን ሰርተው በመመለስ ህጻናቱን መልሰው ሊወስዱ የሚችሉበት አሰራር የሚዘረጋ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

መመሪያው ህጻናቱ ማቆያ ውስጥ ሲቆዩ ምን ምን አገልግሎቶችን ያገኛሉ? ምን አይነት ነገሮች ሊሟሉላቸው ይገባል? ምን አይነት ህጻናቶች ናቸው እዚህ ውስጥ ሚገቡት? የሚሉትን የሚመልስ ሲሆን አሁን ላይ ተጠናቆ የፍትህ ቢሮ የህግ አስተያየት ሰጥቶበት ለፋናንስ ቢሮ መላኩን አክለው ገልጸዋል።

ይህ ጎዳና ላይ ለሚለመንባቸው ህጻናት ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸው አካል ጉደተኛ ሆነው ወተው መስራት ለማይችሉ፤ ልጆቻቸውን ብቻ ይዘው ቤት ውስጥ ለሚቀመጡ ወላጆች፤ በማረሚያ ቤት ውስጥ ልጆቻቸው ላሉ (በረጅም ጊዜ በማቆየት) ሁሉን ሊያቅፍ በሚችል መልኩ መመሪያው መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ ልጆቻቸው በማቆያ ከሆኑ ወላጆቻቸው ገቢ ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ጭምር ጎን ለጎን እያሰቡ መመሪያው መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

Via @tikvahethmagazine
#AxumUniversity

በጦርነት ምክንያት አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቁሟቸው ነበሩትን አገልግሎቶች ማስጀመሩን ለማወቅ ተቸሏል።

ዩኒቨርሲቲው ለቀድሞ ተማሪዎቹ ፦
➭ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት
➭ ስቱደንት ኮፒ
➭ ጊዚያዊ ሰርተፊኬት
➭ የዲግሪ ማረጋገጫ
➭ እንግሊዝኛ የማስተማሪያ ቋንቋነት ማረጋገጫ መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በመሆኑም የቀድሞ ተመራቂዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በዩኒቨርሲቲው በአካል በመገኘት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ አክሱም ዩኒቨርሲቲ በሁለት ወይም በሦስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ኦሪጅናል ዲግሪ መስጠት እንደሚጀምር አሳውቋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በትግራይ ጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራ ለማስጀመርና ተማሪዎቹን ለመቀበል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ችለናል።

More : @tikvahuniversity
#ቴክኖ_ሞባይል

በስፓርክ 10 ሲሪየስ ስልኮች ድንቅ ፎቶዎችን ይነሱ!

አዲሱ ቴክኖ ስፓርክ 10 ሲሪየስ ሞዴል የፊትና የሗላ ካሜራ ያለ እንከን ቁልጭ አርጎ ድንቅ ምስሎችን እንዲያነሱ ታስቦ የተሰሩ በባለ 50 ሜጋ ፒክስል ዋና ካሜራ ያለው ሲሆን በተጨማሪ ከፊት ለፊት ጥራት ያለው ፎቶ ያለ እንከን ማንሳት የሚያስችል በባለ 32 ሜጋ ፒክስል ሰልፊ ካሜራ ከፍላሽ መብራት ጋር ቀርቦሎታል።

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ ካሜራን የያዘው ስፓርክ 10 ሲሪየስ ትክክለኛውን የፊታችንን ተፈጥሯዊ ገፅታ እና ከለር ሙሉ በሙሉ የማንሳት ችሎታ የያዘ ነው።

በየትኛውም የስልክ መሸጫ መደብሮቻችን ያገኙታል።
ለበለጠ መረጃ: Facebook, Instagram, Tiktok

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark10Series #TecnoMobile #Ethiopia #Spark10pro
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከቀናት በፊት በተፈፀመባቸው ጥቃት የተገደሉት የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ እሁድ ተፈፅሟል።

የአቶ ግርማ የሽጥላ ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በትውልድ ስፍራቸው መሃል ሜዳ ነው።

ከስርዓተ ቀብራቸው ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ የሽኝት ስነስርዓት ተከናውኖ ነበር።

አቶ ግርማ ባለትዳርና የ3 ሴትና የ4 ወንድ ልጆች አባት ነበሩ።

ፎቶ፦ አሚኮ

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እንዲሁም #በሽብር_ወንጀል " እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።

ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል እየወሰድኩ ነው ባለው እርምጃ " ፅንፈኛ ናቸው " ላላቸው ኃይሎች የሚዲያ እና ፕሮፖጋንዳ ክንፍ በመሆን እየሰሩ ናቸው ያላቸውን አካላት ነው #በወንጀል እንደሚፈልጋቸው ያሳወቀው።

በውጭ ሀገር ያሉትን ተፈላጊ ግለሰቦች በዐለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት እንዲሁም ከሚኖሩባቸው ሀገር መንግስት የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት ጋር በተመሰረቱ የትብብር ማዕቀፎች ተላልፈው እንዲሰጡ እየሰራሁ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል የፀጥታ እና ደህንነት  ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል " በህቡዕ አደረጃጀት " ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ አገኘኃቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

ከእነዚህ 47 ግለሰቦች ውስጥ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውጋቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ተዳርጋ የተፈታችው መምህርት መስከረም አበራ ይገኙበታል።

ግብረ ኃይሉ የተያዙት ግለሰቦች የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን " ለመግደል፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል " በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ስለደረስኩባቸው ነው ብሏል።

ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia