TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amaharic #Russia

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በሞስኮ የሚገኙ ት/ቤቶች የአፍሪካ ቋንቋዎችን ማስተማር ይጀምራሉ ተባለ።

በዚህም የአማርኛ ቋንቋ አንዱ ሆኖ ይሰጣል።

የሞስኮ ትምህርትና ሳይንስ ክፍልን ዋቢ በማድረግ ስፑትኒክ እንደዘገበው ፤ ሩሲያ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ከመስከረም ወር ጀምሮ #አማርኛ እና #ስህዋህሊ ቋንቋዎችን በሞስኮ በሚገኙ በአራት ት/ቤቶች ማስተማር እንደምትጀምር ባሳወቀችው መሰረት ትምህርቱ መሰጠት ይጀምራል።

እንደ ዘገባው ከሆነ " 1517 " የተሰኘው የፔዳጎጂ ትምህርት ቤት ስዋህሊ ቋንቋን ሁለተኛው የውጭ ቋንቋ አድርጎ ያስተምራል።

" 1522 " የተሰኘው ትምህርት ቤት ደግሞ አማርኛ ቋንቋን እንደሚያስተምር ተገልጿል።

ሩሲያ የአፍሪካ እና ሞስኮን ወዳጅነት ለማጠናከር በሳምንት አንድ ወይም ሁለት የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ለአፍሪካ ቋንቋዎች ማስተማሪያ እንዲውሉ ይደረጋል ብላለች።

ሩሲያ በቀጣይ በምዕራብ አፍሪካ ሰፊ ተናጋሪ ያለው ዩርባ ቋንቋን ማስተማር እንደምትጀምር ገልጻለች።

በመቀጥልም #ሶማልኛ እና የዙሉ ቋንቋዎችን በሩሲያ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው።

ሌላኛዋ ሀገር ቻይና አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ ማስተማር እንደምትጀምር ከዚህ ቀደም መግለጿ ይታወቃል።

አማርኛ ቋንቋ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) ከሚሰጡ 101 የውጭ ቋንቋ ትምህርቶች አንዱ ሆኖ ይሰጣል ተብሏል።

መረጃው የ #አልዓይን (ስፑትኒክ) ነው።

ስፑትኒክ አፍሪካ ፦ https://www.facebook.com/100091796831512/posts/pfbid02Zf2NYdkBuBFDA8UDxBbtf5ZBGbRVPjYGUWzgeLVL365qBrKQgthGS622GJqo2PNul/?app=fbl

@tikvahethiopia