TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia