TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት⬇️

ጠቅላይ አቃቢ ህግ በሰኔ 16ቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ #ቦምብ አፈንድተዋል ያላቸው አምስት ግለሰቦች ላይ #ክስ መሰረተ፡፡

አምስቱ ግለሰቦች ጌቱ ግርማ፣ ብርሃኑ ጃፈር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ባህሩ ቶላ እና ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው አቃቤ ህግ ቦምብ በማፈንዳት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው፡፡

ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት የተከፈተ ሲሆን ክሱን ለእያንዳንዳቸው በችሎት እንዲደርስ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደሚያመላክተው አንደኛ ተከሳሽ ጌቱ ግርማ ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር ሱሉልታ ላይ በመገናኘት ሰልፉን የጠራው ገለልተኛ ወገን ሳይሆን ኢህአዴግ ነው ኤችአር 128 የተባለውን በአሜሪካ ኮንግረስ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል የሚል ምክንያቶችን በመግለጽ ቦምቡን #በመወርወር እንዲበተን እናድርግ በማለት እንዲዘጋጅ መግለጹን በክሱ ተመላክቷል፡፡

ለሦስተኛ ተከሳሽ #ደውሎም ቦምብ የሚወረውር ሰው አንዲፈልግ ተልዕኮ መስጠቱ በክሱ ተጠቅሷል፡፡

ሁለተኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ጃፈር ደግሞ በሚያዝያ ወር 2010 ዓመተምህርት ሁለት ኤፍ 1 እና አንድ የጭስ ቦምብ ያለው መሆኑን ለአንደኛ ተከሳሽ መግለጹን የጠቀሰው አቃቤ ህግ ሱሉልታ ከተማ ተገናኝተው ቦምቡን የድጋፍ ሰልፉ ላይ በመወርወር ጥቃት ለማድረስ በመነጋገር ቦምቡን መወርወር የሚችሉ ልጆች እንዲዘጋጁ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር ተነጋግረዋል ሲል አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል፡፡

ሦስተኛ ተከሳሽ ጥላሁን ጌታቸው በድጋፍ ሰልፉ ላይ ቦምብ እንዲያፈነዳ በአንደኛ ተከሳሽ ተገልጾለት ለአራተኛ ተከሳሻ በመደወል ቦምብ ለመወርወር ማቀዱን በመግለጽ በጉዳዩ ላይ #ለመወያየት እንዲገናኙ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

አራተኛ ተከሳሽ ባህሩ ቶላ በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት መስቀል አደባባይ ቦምቡን ለመወርወር ማቀዱን በመጥቀስ በሁኔታው ለመወያየት #አስኮ የተቀጣጠሩ ሲሆን ከዚያም ቡራዩ ላይ በአምስተኛ ተከሳሽ ቤት ተገናኝተዋል፡፡

ከተገናኙ በኋላም በአምስተኛ ተከሳሽ ቤት ያደሩ ሲሆን አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች በሰኔ 16 2010 ዓመተምህረት ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ላይ ሁለተኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ2 262335 አዲስ አበባ በሆነ መኪና ውስጥ ሁለት ኤፍ 1 ቦምብ እና አንድ የጭስ ቦምብ በመያዝ አንደኛ ተከሳሽ ቤት ማስቀመጣቸውን በክሱ ተጠቅሷል፡፡

ያስቀመጡትን ቦምብም በዚሁ ተሸከርካሪ ጭነው አዲስ አበባ ውንጌት አካባቢ ከሦስተኛ፣ ከአራተኛ እና ከአምስተኛ ተከሳሽ ጋር በመገናኘት ፒያሳ አካባቢ የገቡ ሲሆን በምን መልኩ ጥቃቱን ማድረስ እንዳለባቸው መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በዕለቱ የዶክተር አብይ አህመድ ምስል ያለበትን ቲሸርት ገዝተው እንዲለብ ሱ በማድረግ በተጠቀሰው መኪና ቴዎድሮስ አደባባይ ድረስ በመሸኘት ቦምቡ እንዲፈነ ዳ ተልዕኮ በመስጠት የተመለሱ ሲሆን ሦስተኛ፣ አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሾች በተሰጣቸው ተልዕኮ መሰረት ከሰልፈኞች ጋር በመቀላቀል ሦስተኛ ተከሳሽ በሐራምቤ አቅጣጫ በማድረግ ወደ መስቀል አደባባይ መግባቱ የተጠቀሰ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር አድርገው ሲጨርሱ ከመድረኩ በቅርብ ርቀት ላይ በመገኘት ቦምቡን ወርውሮ ማፈንዳቱን አቃቢ ህግ ጠቅሷል፡፡

በዚህም ሙሳ ጋዲሳና ዮሴፍ አያሌው የተባሉ ግለሰቦች በፍንዳታው ህይወታቸው ማለፉን በክሱ ተጠቅሷል፡፡

በፍንዳታው ከ163 በላይ በሆኑ ንጹሃን ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት አድርሰውባቸዋል ተብሏል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia