TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- ሼንዠን ውሻና ድመት ለምግብነት እንዳይውሉ ያገደች የመጀመሪያዋ የቻይና ከተማ ሆናለች።

- በሊባኖስ የፊሊፒንስ አምባሳደር በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል።

- በሩስያ ተጨማሪ 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ተሰምቷል።

- በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ950,000 በልጧል። ከ48,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፣ ከ200,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።

- በዓለም ላይ የኮቪድ-19 ተጠቂ 1 ሚሊዮን ሊደርስ በተቃረበበት ወቅት ሰሜን ኮሪያ አሁንም አንድም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በሀገሬ የለም ብላለች።

- የሩዋንዳ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመቆጣጠር ተግባራዊ ያደረገውን ጥብቅ ከቤት ያለምውጣት ክልከላ ለተጨማሪ 3 ሳምንታት አራዝሟል።

- በአውሮፓ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ግማሽ ሚሊዮን ደርሷል።

- በስፔን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ10,000 በልጣል። በ24 ሰዓት የ950 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

#SkyNews #BBC #Euronews #Aljazeera

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገሪቱ የጣሉትን በቤት የመቀመጥ ውሳኔ በአንድ ወር አራዝመዋል

- እስካሁን ቫይረሱ ሀገሯ ሳይገባ የቆየችው ማላዊ በዛሬው ዕለት ሶስት ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች።

- የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በምዕራብ አፍሪካ የነበሩ 3 የፈረንሳይ ወታደሮች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰምቷል። ወታደሮቹ ወደፈረንሳይ እንዲመለሱም ተደርጓል።

- በጣልያን በ24 ሰዓት ውስጥ የ760 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 13,915 ደርሷል። በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም ከ115,000 በልጧል።

- በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5,626 ደርሰዋል። 235,860 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- በመላው ዓለም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በልጧል። ከ51,000 በላይ ሰዎችም ሞተዋል። 210,308 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

-ሳዑዲ አረቢያ የ24 ሰዓት የሰዓት እላፊ በቅዱስ ከተሞቿ ላይ ጥላለች። በመካ እና በመዲና የተጣለው የሰዓት እላፊ የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ነው ተብሏል።

#SkyNews #BBC #Euronews #Aljazeera

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DonaldTrump

የጤና ባለሞያዎችን ያስቆጣው የትራምፕ ሀሳብ!

(በሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኮሮና ቫይረስ የፈውስ መላዎች የሰጡት አስተያየት የጤና ባለሙያዎችን አስቆጥቷል።

ፕሬዝዳንቱ ለበሸታው ፈውስ የረቂቅ ተሕዋስያን ማጥፊያ ዲስ ኢንፌክታንት ኬሚካል በመርፌ የሚሰጥበት ምርምር እንዲደረግ ሀሳብ ማቅረባቸው የጤና ባለሞያዎችን በእጅጉ አስቆጥቷል ተብሏል፡፡

የሕክምና ባለሞያዎች ዲስኢንፌክታንት (ኬሚካል) ወደ ሰውነት ከገባ አደገኛ መራዥ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ሌላ የዋይት ሐውስ ሹም የፀሐይ ጨረርም ለኮሮና ቫይረስ ፍቱን ነው ማለታቸው የጤና ባለሞያዎች ተቃውመውታል። ሐኪሞች የትራምፕ ሐሳብ ስራ ላይ ይዋል ከተባለ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

#BBC #SEHGER_FM #AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ጦርነቱን አሸንፈናል!" - ጠ/ሚ ጃሲንዳ አርደን

ኒውዚላንድ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መዛመት ለከለላከል ስትል ደንግጋው የነበረውን የመንቀሳቀስ ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ አንስታለች፤ ሀገሪቷ አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረሷንም አስታውቃለች። አንዳንድ ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋሞች እንዲከፈቱ ተፈቅዳል።

የኒውዝላንዷ ጠ/ሚ ጀሲንዳ አርደን - "አሁን በኒውዚላንድ ውስጥ ያልተለየና የተስፋፋ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት በማህበረሰቡ ውስጥ የለም ፤ ይህን ጦርነትም አሸንፈናል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይህ ወረሽኝ [ኮቪድ-19] መቼ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፋ እንደማይታወቅ በማስገንዘብ ፤ የሰዎች ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት መደበኛነት እንዲመለስ የሚያስችል የተረጋገጠ ሁኔታ እንደሌለም አስጠንቅቀዋል።

"ሁሉም ሰው ወደ ቀደመው እና ወደናፈቀው የማህበራዊ ግንኙነት መመለስ ይፈልጋል ፤ ይህን በሙሉ መተማመን ለማድረግ ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ አለብን" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ አንድ (1) ብቻ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። በአጠቃላይ 1,469 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም ውስጥ 1,180 ሰዎች አገግመዋል፤ በሀገሪቱ የሞቱት 19 ሰዎች ናቸው።

ኒውዚላንድ ውስጥ ለአንድ ወር ያክል ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡና አስፈላጊ ያልሆኑት የንግድ ተቋማት ሁሉ ተዘግተው ነበር።

#VOA #AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DonaldTrump

በትላንትናው ዕለት ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአንዲት ኤሲያዊ-አሜሪካዊ ጋዜጠኛ የተነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በተፈጠረ ንትርክ ምክንያት ሲሰጡት የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ በድንገት አቋርጠዋል፡፡

ትራምፕ ጋዜጠኛዋ ላነሳችው ጥያቄ “ቻይናን ጠይቂ “ የሚል መልስ ከሰጡ በኋላ ከሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

የCBS ዜና የኋይት ሀውስ ዘጋቢ የሆነችው ጋዜጠኛ ዌይጃ ጂያንግ ከ80,000 በላይ አሜሪካውያን በሞቱበት ወቅት የኮሮና ቫይረስ ምርመራን ለምን እንደ አለምአቀፍ ውድድር እንደሚያዩት ፕሬዘዳንቱን ጠይቃለች፡፡

ትራምፕ ቻይና ተወልዳ በ2 አመቷ ወደ አሜሪካ ለመጣችው ጋዜጠኛ “ያንን ጥያቄ ቻይናን ነው መጠየቅ ያለብሽ፣ ቻይናን ጠይቂ፤ እሽ”ብለዋታል፡፡

ትራምፕ ይህን ካሉ በኋላ ወደ ሌላ የኋይት ሀውስ ዘጋቢ ለማለፍ ሞክረው ነበር፤ነገርግን ጂያንግ በተከታይ ጥያቄ ትራምፕን አቋረጠቻቸው፡፡

“ጌታው፣ ያንን በተለየ ለምን እኔን አሉኝ” በማለት በትራምፕ የተገረመችው ጂያንግ ጠየቀች፡፡

“እየነገርኩሽ ነው” ትራምፕ ይመልሳሉ፡፡ “ ይህን በተለየ ለማንም አልናገርም፡፡ አስቀያሚ ጥያቄ ለሚጠይቅ ለማንም እመልሳለሁ” ብለዋል፡፡

“ይህ አስቀያሚ ጥያቄ አይደለም” ስትል ጂያንግ መልሳለች፡፡ “ምን ችግር አለው?” በዚህ ጊዜ ትራምፕ ከሌላ ጋዜጠኛ ጥያቄ ለመቀበል ሲሞክሩ ነበር፡፡

(በአል ዓይን የተዘጋጀ)

#AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WHO

የኮሮና ቫይረስ ከዓለማችን ላይ እስከወዲያኛው ላይወደገድ እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ ህክምናዎች ዳይሬክተር ዶክተር ማይክ ረያን በትናንትናው እለት በሰጡት ማብራሪያ፥ ቫይረሱ የሚያበቃበትን ጊዜ መተንበይ ትክክል እይደለም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሁላችንም የኮሮናቫይረስ በዓለም ማህበረሰብ ዘንድ ሌላኛው ወረርሽኝ ሆኖ እስከወዲያኛው ሊቆይ ይችላል የሚለውን ከግምት ማስገባት አለብን ያሉት ዶክተር ረያን፥ ቫይረሱ እስከወዲያኛው አብሮን ሊኖርም ይችላል ብለዋል - #BBC

#AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* Update

የእስራል እና ሀማስ ከ11 ቀናት ግጭት በኃላ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል ተብሏል።

በጋዛ 232 ፍልስጤማውያን (65ቱ ህፃናት) በእስራኤል በኩል 12 ሰዎች (2ቱ ህፃናት) ህይወታቸውን ካጡ በኃላ ነው ይህ የተኩስ አቁም ስምምነት የተደረሰው።

የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ ትላንት በግብፅ አስታራቂነት የተኩስ አቁም እንዲደረግ የቀረበውን ስምምነት በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

ተኩስ አቁሙ ከተተገበረ በኋላ በርካታ ፍልስጥኤማዊያን በጋዛ ጎዳናዎች ደስታቸውን ለመግለፅ የወጥተው ነበር።

ሁለቱም አካላት በየፊናቸው አሸናፊነታቸውን አውጀዋል።

የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ቢኒ ጋንትስ የጋዛው ጥቃት ‹‹ያልተጠበቁ ትርፎችን አስገኝቶልናል›› ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል።

አንድ የሃማስ ባስልጣን ለAP ፥ እስራኤል የተኩስ አቁም ማድረጓ እንደትልቅ ድል የሚቆጠር እና ይህም ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒናሁ ሽንፈት ነው ብለዋል።

በሃማስ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ም/ ቤት አባል የሆኑት ባሴም ናይም በበኩለቸው ፥ ስለተኩስ አቁሙ ዘላቂነት ጥርጣሬ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

‹‹ለፍልስጥኤማዊያን ፍትህ ሳይመጣ፣ እስራኤልን ወረራዋን እና በእየሩሳሌም በሕዝባችን ላይ የምትፈፅመውን የጭካኔ ተግባር ሳታቆም የሚደረግ የተኩስ አቁም ጠንካራ መሰረት አይኖረውም›› ብለዋል።

የሃማስ የፖለቲካ ቢሮ አባል ኢዛት አል-ረሺቅ ለእስራኤል ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

"እርግጥ ነው ውጊያው ዛሬ ቆሟል። ነገር ግን ኔታኒያሁ እና መላው ዓለም እጃችን በተቀባበለው ጠብመንጃችን ላይ መሆኑን እና ትግላችን ተጠናክሮ እደሚቀጥል ማወቅ አለባቸው፤ ለኔታኒያሁ እና ለሰራዊቱ መግለፅ የምንፈልገው ከተመለሳችሁ እኛም እንደምንመለስ እወቁ ›› ብለዋል።

#BBC #AlJazeera

@tikvahethiopia
#Sudan

በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል።

ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል።

በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣ 39 ሰዎች ቆስለዋል በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል።

በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል።

ምንም እንኳን ሱዳን በአካባቢው ተጨማሪ ወታደሮችን ብታሰማራም ግጭቱ እስከ ትላንት ከሰአት በኋላ ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል።

መንግስት ደም አፋሳሹን ግጭት ለማስቆም ችግር ባለባቸው ቦታዎች ላይ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል።

#CGTNAFRICA #AlJazeera #AP

@tikvahethiopia
#Rwanda

በሩዋንዳ በተካሄደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፖል ካጋሜ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ የማሸነፍ እድል እንዳላቸው ያልተጠናቀቀ ቆጠራ አሳይቷል።

የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን በበርካታ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ላይ ባካሄደው ቆጠራ (79% ቆጠራ) ካጋሜ 99.15 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል።

24 ዓመታትን ሩዋንዳን በፕሬዜዳንትነት የመሩት ፖል ካጋሜ ውጤቱ ለተጨማሪ 5 ዓመታት በስልጣን እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል።

ሶስት ብርቱ ናቸው የተባሉ ተቀናቃኞቻቸው ከምርጫ ፉክክሩ ውጭ በሆኑበት ነው ምርጫው የተካሄደው።

በምርጫው የተሳተፉት የአየር ንብረት ጥበቃ ተሟጋች ፍራንክ ሃቢኔዝ እና ጋዜጠኛና ደራሲ ፊሊፕ ምፓይማና ከ1 በመቶ ያነሰ መራጭ ነው ያገኙት።

ከዚህ በፊት በነበረው የአውሮፓውያኑ 2017 ምርጫ ካጋሜ በ98.8 ድምጽ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ፖል ካጋሜ እኤአ 1994 የሩዋንዳ የዘር ፍጅት በኋላ በመሪነት ስፍራ የተቀመጡ ሲሆን ከ2000 በኋላም በፕሬዚዳንትነት ቀጥለዋል።

#BBC #AlJazeera

@tikvahethiopia