TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለጥያቄው_ምላሽ፦ TIKVAH-ETH የተመሰረተው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በሃምሌ 19/2009 ዓ/ም ነው። TIKVAH በተመሰረተበት ወቅት የቤተሰቡ አባላት 20 አይደርሱም ነበር። የነበሩትም #ንቁ ተሳታፊ አልነበሩም። ዛሬ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኘው የቤተሰባችን አባል ከ320 ሺ በላይ ነው። በተመሰረተበት ወቅት ቀለል ያሉ የመዝናኛ ነክ ጉዳዮችንና ፎቶዎችን ያቀርብ ነበር። ለጥቂት ጊዜ ትውውቅ ከተደረገ በኃላ በወቅቱ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በነበረው ችግር ሳቢያ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተማሪ ድምፅ ሆኖ አገልግሏል።

TIKVAH ማለት #ተስፋ ማለት ነው!

√እኛ ማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ የሚከበርበት፤ ሰውነቱ ሲከበር ብሄሩ፣ ቋንቋው፣ ባህሉ፣ አመለካከቱ፣ እምነቱ የሚከበርበት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ አስተማማኝ ደህንንነት እና ሰላም ያለባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ማንም ሰው በአመለካከቱ የማይገፋበት ለሁሉም ዜጎች እኩል የሆነች ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን!

√እኛ አይደለም ለኢትዮጵያዊ በምድር ላይ ላለሰው ሁሉ የምትሆን ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

√እኛ ዜጎቿ የማይበደሉባት ሀገር እንደምትኖረን ተስፋ እናደርጋለን።

#ተስፋችን_ደግሞ_በፍጡር_ሳይሆን_በፈጣሪ_ብቻ_ነው!

ይህ አቋማችን የዛሬ ሳይሆን የነበረ፤ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው!! #ETHIOPIA

🏷ይሄ ቤተሰብ "የኢትዮጵያ ተስፋ" ነው ብለን እናምናለን!! በመነጋገር የሚያምን ከጥላቻ የራቀ፤ ስድብ የሚፀየፍ አንድ ጠንካራ የሆነችን ሀገር ለመገንባት ዘውትር የሚተጋ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ስብስብ ነው።

ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray , #Mekelle

የፕሪቶሪያውን #የሰላም_ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል መዲና መቐለ በምግብ እና ሸቀጦች ላይ ቅናሽ እየታየ መሆኑን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ስለታየው ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ በ " ቀዳማይ ወያነ ገበያ " ያሉ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

አለቃ አረጋዊ ጨርቆስ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፦

- ሰርገኛ ጤፍ 11 , 000 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ከ6000 እስከ 6500 እየተሸጠ ነው።

- ነጭ ጤፍ 14,000 እስከ 13,500 ይሸጥ የነበረው አሁን 10,000 ብር እየተሸጠ ነው።

" ይህ የሚመጣው ከመኸኒና ከአካባቢው ብቻ ሲሆን አላማጣ ዝግ ነው፣ ጨርጨር ዝግ ነው። መንገድ በምዕራብ አቅጣጫ በሽረ በኩል ዝግ ነው ፤ ወቅቱ ጥቅምት እና ህዳር ቢሆንም በሁሉም አቅጣጫ መስመር ቢከፈት ይቀንሳል።

ሰላሙን ተከትሎ ከመሃል ሀገር ቢመጣ ደግሞ በደንብ ይቀንስ ነበር።

በተለይ ነዳጅ ቢገባ አሁን ውድ የሆነው ትራንስፖርት ይቀንስ ነበር። አንድ ሊትር ነዳጅ በጥቁር ገበያ 350 ብር እየተገዛ ሲሆን ከነዳጅ ማደያ የሚገዛ ነዳጅ ቢኖር ኖሮ በደንብ ይቀንስ ነበር " ብለዋል።

በመቐለ የስንዴ ዋጋ በኩንታል ከ10 ሺህ ብር ወደ 7 ሺህ ብር ቀንሷል።

ሰመሃል ኪዳኔ የተባለች የበርበሬ ነጋዴ ደግሞ ለአንድ ኪሎ ግራም 700 ብር የነበረው በርበሬ አሁን 500 ብር ገብቷል ይህ የሆነው በሰላሙ ስምምነት ተስፋ በማድረግ ነጋዴው ይቀንሳል ብሎ ስላመነ የያዘውን በቅናሽ እየሸጠ በመሆኑ ነው ብላለች።

" ህዝባችን ተጨቁኗል፣ በጣምም ተርቧል፣ አጥቷል #ሰላም በመሆኑ ተጠቃሚ ነን ፤ በጦርነት ኪሳራ እንጂ ልማት የለም ፤ ድርድርን ተከትሎ ባንክ ቢከፈት የቴሌኮም አገልግሎት ቢጀመር እንዲሁም ነዳጅ እንዲገባ ነው #ተስፋችን " ብላለች።

ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ሩፋኤል የተባሉ ሸማች ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የሸቀጦች ዋጋ በጣም ወርዶ ማግኘታቸውን ገልፀዋል። ሙሉ በሙሉ ቀንሷል ባይባልም ለውጦች እየታዩ መሆኑን አመልክተዋል።

ዘይት 1,700 እና 1,800 የነበረው ወደ 1,400 ዝቅ ማለቱን ገልፀዋል። ፉርኖ ዱቄት በኩንታል እስከ 13,000 ብር የነበረው ወደ 9,000 ብር ወርዷል (እንደየጥራቱ)።

ነጭ ጤፍ ከአንድ ወር በፊት 13,000 ብር እንደገዙ አሁን ግን 3,000 ብር ቀንሶ በ10,000 ብር እንደገዙ ገልፀዋል፤ ከዚህም ይቀንሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ሰርገኛ ጤፍ ፣ ቀይ ጤፍ ላይም መቀነስ እንዳሳየ አስረድተዋል።

በሩዝ ፣ በመኮሮኒ ዋጋዎች ላይም ከፍተኛ የሆነ ቅናሽ መመዝገቡን እኚሁ ሸማች ለሬድዮው ተናግረዋል።

#በአስቸኳይ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በመክፈት ህዝቡ የመግዛት አቅም እንዲኖረው ቢደረግ ጥሩ መሆኑን የገለፁት ሸማቹ የመሰረታዊ አገልግሎት መከፈት ፣ የንግድ ቀጠናዎች ትራንስፖርት ቢከፈት አሁን ካለው ዋጋም እንዲቀንስና ገበያው  እንደሚረጋጋ ገልፀዋል።

መሀመድ ካህሳይ የተባሉ ነጋዴ ለሬድዮው በሰጡት ቃል ፥ " ሰላምን ምንም የሚወዳደረው ነገር የለም ፤ ጥፋት ጥፋት ነው ሁልጊዜ ሰላም ግን ሰላም ነው ፤ አሁን ሰላም ከተጀመረ ጀምሮ 5 ሊትር ዘይት 2,100 የነበረው በአንድ ጊዜ ወደ 1,500 እና 1,450 ብር ገብቷል።

የበለጠ መኪና/ትራንስፖርት ሲከፈት ባንኩ ሲከፈት በጣም ቆንጆ ነገር ይሆናል ።

ባንክ ሳይከፈት ዋጋው እንደዚህ የሆነ ባንክን ጨምሮ መሰረታዊ ነገር ሲከፈት ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል በጣም ደስ ይላል። ስኳርም አንድ ኪሎ 270 የነበረ 160 ገብቷል በጣም ደስ ይላል።

መድሃኒትም ይሁን ጥራጥሬ ከመጣ ሁሉም ነገር ወደቦታው እየተስተካከለ ይመጣል ሱቁም ይሞላል ፣ ትራንስፖርትም 24 ሰዓት የሚሰራ ከሆነ በጣም ቆንጆ ነው።

መንግሥት ቶሎ ብሎ አስተካክሎ ካደረገው በጣም ደስ ይለናል። "

በመቐለ ገበያ ፤ ከሳምንት በፊት 2,700 ብር ሲሸጥ የነበረ የ25 ኪሎግራም መኮሮኒ አሁን 1800 ብር እየተሸጠ ነው። አንድ ፓስታ ከ130 ብር ወደ 60 ብር ቀንሷል። 1 ኪሎ ኦቾሎኒ ከ370 ብር ወደ 160 ብር ቀንሷል። ሽኩርት ፣ ቲማቲም ፣ ድንች ዋጋ ላይ ለውጥ የለም።

Credit : ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ (ቪኦኤ ፌድዮ)
የፅሁፍ ዝግጅት ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia