TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ።

ዶ/ር ጌዲዮን ፓርቲው ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት መንግሥት ተገዶ የገባበት መሆኑን ገልፀው ፤ መንግሥት ይህንን ለመፍታት እየሠራ ስለመሆኑም አስረድተዋል ።

ፓርቲዉ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ታሳቢ በማድረግ #ለሰላም_ቅድሚያ_ይሰጣል ነው ያሉት።

ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት ፓርቲዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የሰላም አማራጩ፡-

1. ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊነትን የሚያስከብር መሆን አለበት፡፡

2. የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ መሆን አለበት፡፡

3. በሀገር ዉስጥ መፍታት ካልተቻለ #በአፍሪካ_ሕብረት ጉዳዩ መታየት እንዳለበት በሥራ አስፈጻሚ እና በማእከላዊ ኮሚቴ ዉይይት ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ትንኮሳዎች ካሉ ሕግ አስከባሪዉ አካል እርምጃ እንዲወሰድ ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል። ሕዝቡም ለዚህ ተሳታፊ እንዲሆንም ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia