TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቢሲያን_ባንክ

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኢትዮዽያ ክልሎች አገልግሎት የሚሰጡ ወደ 20 የሚጠጉትን የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን በመጠቀም ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት ፦
- ገንዘብ ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ፤
- ቼክ መመንዘርና ተቀማጭ ማድረግ፤
- የሃገር ውስጥ ሓዋላ፤
- ገንዘብ ማስተላለፍ እና እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ካርድ ባንኪንግና ሞባይል ዋሌት (ጊዜፔይ) ያሉ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላሉ፡፡

እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን ያማከለ ከወለድ ነጻ የቨርቹዋል ባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከሎቻችንም፣ በቅርንጫፎች የሚሰጡትን የተሟላ አገልግሎቶች ማግኘት ያስችላሉ፡፡

#BankofAbyssinia #Banking #BanksinEthiopia #VirtualBanking #ITM #MoneyTransfer #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ethiotelecom

በቴሌብር ሱፐርአፕ በአንድ ጊዜ ለበርካታ ሰዎች ገንዘብ መላክ ተችሏል !

በቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ገንዘብ ለበርካታ ሰዎች በአንድ ጊዜ ለመላክ የተቀባይ ቡድን በመፍጠር ለቡድኑ አባላት ተመሳሳይ ወይም የተለያየ የገንዘብ መጠን በአንድ ትዕዛዝ ለሁሉም እኩል ይልካሉ ጊዜዎን ድካምዎን ይቀንሳሉ!
ለሰራተኞችዎ ደሞዝ ክፍያ፣ ለወዳጅ ዘመድ ገንዘብ ሲልኩ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮችዎ ይጠቀሙበት ይወዱታል!

አዲሱን የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ።

#ኢትዮቴሌኮም #ቴሌብር
#Tigray

በትግራይ ላሉ ዩኒቨርሲቲዎች የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች አድርጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች በክልሉ ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችል ውይይት በመቐለ አድርገዋል።

በትግራይ ክልል የሚገኙት አራት ዩኒቨርሲዎች ፕሬዝዳንቶች ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የሚያሳይ ሪፓርት በመድረኩ አቅርበዋል፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ተቋርጦ የቆየውን የዩኒቨርሲቲዎች እና አጠቃላይ መደበኛ ትምህርት ለማስጀመር የመምህራንና የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የትብብር መድረክ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሀና "በጦርነቱ የተጎዱ የወሎ፣ ወልድያ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የታየው ትብብር በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚደገም" ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንሰርቲየም ለጊዜው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች አድርጓል፡፡

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።

" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ፕሮግሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-  

- ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአራተኛ ክፍለ  ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SpecialForce " ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ አይደለም " - ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ መንግሥት እያካሄደ ያለው የልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀት መርሃ ግብር ትጥቅ ከማያስፈታት ጋር እንደማይገናኝ አሳወቀ። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " የሁሉንም ክልል ልዩ ኃይል አባላት መልሶ የማደራጀት ስራ ነው የሚሰራው እንጂ ሂደቱ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር የሚገናኝ…
#SpecialForce

" በመልሶ ማደራጀቱ ሂደት ምንም አይነት የሚበተን ኃይል የለም " - የአማራ ክልል መንግሥት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊው የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጉዳይ በተመለከተ ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጠ።

በዚህ መግለጫው የክልል ልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀቱ ተግባር በሁሉም ክልሎች የሚፈፀም ነው ብሏል።

ዓላማውም የኢትዮጵያን ሕልውናን የበለጠ የማበርታት መሆኑንና የጋራ ግብን ያነገበ ስለመሆኑ ገልጿል።

" ይህ ተግባር በተሟላ ሀገራዊ ጥናት ላይ የተመሰረተ፣ የህዝቦችን አንድነትንና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተተለመ እንዲሁም የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን እውን ለማድረግ በሁሉም ክልሎች ታምኖበት የተገባበት ወሳኝ ተግባር ነው " ሲል ክልሉ አሳውቋል።

የአማራ ክልል ፤ የልዩ ኃይል አደረጃጀቶችን መልሶ የማደረጃት ወይም የሪፎርም ስራ በሁሉም የፌዴራልና ክልላዊ መንግስታት መሪዎች የጋራ ስምምነትና እንደ አንድ ሀገር አንድ ጠንካራ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ መዋቅር እንዲኖረን ታስቦ የተለያዩ ማራጮች ለልዩ ኃይል አባላቶች ቀረቦ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በኩር በማድረግ የሚተገበር ሀገር አቀፍ ታሪካዊ ተግባር ነው ሲል አስገንዝቧል።

ተግባሩ ለሁሉም ክልል የልዩ ኃይል አደረጃጀቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌድራልና የክልል መደበኛ ፖሊስ፣ የፌዴራልና የክልል የማረሚያ ቤቶችን ፖሊስ አባል እንዲሆኑ አማራጮች ያቀረበ መሆኑን ክልሉ አመልክቷል።

የክልሉ መንግሥት " እውነታዉ ይሄ ሆኖ ሳለ አንዳንድ አካላት የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን አየር ላይ እንዲበተን እየተደረገ ነው " የሚል ከእውነት የራቀ ፍፁም በተሳሳተ መንገድ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የአማራን ሕዝብ ውስጣዊ ሠላምና አንድነት የሚያደፈርስ፣ የልዩ ኃይሉን አንድነት የሚረብሽ፣ ባልተገባ መንገድ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ የሚያደርጉ እንቅስቃሴ ላይ ተጠምደው ይገኛሉ ብሏል።

ይህ ድርጊት ህዝቡን እና የልዩ ኃይል አባሎችን በተጨባጭ እየረበሸ እንደሚገኝ የሚገልፀው የአማራ ክልል ፤ " መንግስት ይህንን የመልሶ ማደራጀት ስራ የሚከውነው የልዩ ኃይላችንን የሰው ኃይል ለበለጠ ፋይዳ ላለው ተልዕኮ መልሶ የማደራጀትና ብቁ የማድረግ ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳ የማዘጋጀት ተግባር እንጅ በመልሶ ማደራጀቱ ሂደት ምንም አይነት የሚበተን ኃይል የሌለ መሆኑን ግንዛቤ ሊያዝበት ይገባል " ሲል አስረድቷል።

የክልሉ ህዝብም በአሉቧልታ ሳይታለልና ሳይደናገር እንደ አንድ ሕዝብ ያለውን ታሪኩን እና ሥነ ልቦናውን በሚመጥነው የኢትዮጵያዊነት ላእላዊ ማእቀፍ ጥላ ስር በመሰባሰብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊ አንድነትን የማጽናት ሂደትን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

(የክልሉ መንግሥት ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SpecialForce " በመልሶ ማደራጀቱ ሂደት ምንም አይነት የሚበተን ኃይል የለም " - የአማራ ክልል መንግሥት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊው የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጉዳይ በተመለከተ ዛሬ ምሽት መግለጫ ሰጠ። በዚህ መግለጫው የክልል ልዩ ኃይል አባላትን መልሶ የማደራጀቱ ተግባር በሁሉም ክልሎች የሚፈፀም ነው ብሏል። ዓላማውም የኢትዮጵያን ሕልውናን የበለጠ የማበርታት…
" የክልሉን ሕዝብ መብትና ጥቅም የሚጋፋ የትኛውም አይነት ውሳኔ ተግባራዊ አይደረግም " - የአማራ ክልል መንግሥት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልሉን ሕዝብ መብትና ጥቅም የሚጋፋ የትኛውንም አይነት ውሳኔ ተግባራዊ እንደማያደርግ ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት ፤ የተጀመረው ልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀት ስራ መላው ህዝቡን እና ልዩ ኃይሉን በማወያየት እና በመተማመን የሚፈፀም መሆኑን በመግለፅ የልዩ ኃይል አባላት በየካምፓቸው ወይም በየተመደቡበት የስራ ቦታ ተረጋግተው በትግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላት እንዲሁም መላው የክልሉ ሕዝብ ክልሉን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ ከሚሠሩ አካላት ራሳቸውን በመጠበቅ የክልሉ የፀጥታ ኃይል ብቁ ዘቦች ሁነው ሰላምና ፀጥታን በማስጠበቅ ሥራ እንዲተግቡ ክልሉ በምሽቱ መግለጫው አሳስቧል።

ሙሉ መግለጫው ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77597

@tikvahethiopia
ጄነራሉ ምን አሉ ?

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እና ለመከላከያ ሰራዊት ቴሌቪዥን ፕሮግራም ቃለመጠይቅ ሰጥተዋል።

ይኸው ቃለመጠይቃቸው ዛሬ ለህዝብ ተሰራጭቷል።

ጄነራሉ ምን አሉ ? በተለይም ስለ ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ጉዳይ ምን ሃሳቦችን አንስተው ተናገሩ ?

ጄነራል አበባው ታደሰ ፦

- መላ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን የምንፈልገው በሀገሪቱ የፀጥታ ኃይል እንዲገነባ ህገመንግስቱ የሚፈቅደው #መከላከያ_ሰራዊትና #ፌዴራል_ፖሊስን ነው።

- በየክልሉ ያለው ልዩ ኃይል በሳይዙ ልክ አለው ፤ በሌላ አነጋገር ሀገር በሚመስል ደረጃ 14 እና 15 ሬንጀር አለው ይሄ ፈፅሞ አይቻልም።

- አሁን ያለው የክልል ልዩ ኃይልን መልሶ የማደራጀት ስራ ዛሬ የተጀመረ / በሞራል የተገባበት ሳይሆን ከዚህ ቀደም ለረጅም ጊዜ ጥናት ተደርጎበት ነው።

- የክልል ልዩ ኃይሎች ፦ የክልልን ፀጥታን ይጠብቁ ነበር ፣ ከእኛ (ከመከላከያ) ጋር ሆነው ይሞቱ ነበር ህይወታቸውን አሳልፈዋል ፣ ቆስለዋል ደምተዋል። ይሄ ኃይል ይሄን የመሰለ ትልቅ ኳሊቲ ነበረው።

- ከህገመንግስት አንፃር ስናየው እነዚህ ኃይሎች ህጋዊ አይደሉም ህገመንግስቱ እውቅና አይሰጣቸውም። ለክልል ኃይል የሚሰጠው መደበኛ ፖሊስን ብቻ ነው። ህገመንግስቱ የታጠቀ ኃይል የሚያውቀው አንደኛ መከላከያ፣ ሁለተኛ ፌዴራል ፖሊስ፣ ሶስተኛ መደበኛ ፖሊስ ነው ከዚህ ውጭ ህገመንግስቱ አይልም።

- የኃይል አገነባቡ (የልዩ ኃይል መዋቅር) ብሔር ተኮር ነው ፤ ለኦሮሞ ህዝብ እሞታለሁ ብሎ ቃል ይገባል አማራውስ ? ጉዳዩ አይደለም ማለት ነው በግልፅ አማርኛ ፤ አማራው ደግሞ ይመጣና ለአማራ ህዝብ እሞታለሁ ይላል ኦሮሞውስ ? ጉዳዩ አይደለም ። ብሄር ተኮር ስለሆነ ሀገር አቀፍ የሆነውን አብሮነት የመኖር ፤ የህዝቦችን አንድነት ይሸረሽረዋል።

- የክልል ልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ፕሮግራም ወደ መከላከያ ሰራዊት ማስገባት፣ ወደ ፌዴራል ፖሊስ ማስገባት፣ ወደ መደበኛ ፖሊስ ማስገባት ነው። በማን በራሱ ምርጫ፣ በምን ? ክብሩን ሞራሉን ፣ ጥቅሙን በማይነካ ሁኔታ።

- አፈፃፀሙ በተመለከተ ሁሉንም እኩል እደራጀዋለን ፣ በጥንቃቄም ይሰራል።

- አንደኛውን ክልል ኃይል እንዲኖረው ሌላውን ክልል ኃይል እንዳይኖረው አናድረግም። ይሄ ኢትዮጵያ ውስጥ አይታሰብም።

- የታጠቁ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው ለምሳሌ የትግራይ የትግራይ ክልል እንደማንኛውም ክልል መደበኛ ፖሊስ ብቻ ነው የሚኖረው ፣ የታጠቀ ልዩ ኃይል የሚባል በፍፁም አይኖረውም።

- በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢና ዩኒቶች ካልሆነ በስተቀር አማራ ልዩ ኃይል የሚባለው በአብዛኛው ተቀብሎታል ፤ ይሄ በኮሚኒኬሽን ያለ ችግር ነው ይሄን የኮሚኒኬሽን ችግር እየፈታን ነው ያለነው። አፈፃፀሙ ላይ የታየው ጉድለት ይሄ ነው እንዲህ አይነት ነገር ሊኖር እንደሚችል እንጠብቃለን አስበንም ነው የገባነው። ከዛ  ውጭ ባወጣነው ፕሮግራም መሰረት ይሄን ኃይል ወደምንለው ፕሮግራም እናስገባዋለን ሁሉንም እኩል አድርገን።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-07
#ብርሃን_ባንክ

የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን (*881#) ተጠቅመው :-

- የዋይፋይና ሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዎችን በቀላሉ ያከናውኑ!
- የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ!
- ቀሪ የብድር መጠንዎን ይወቁ
- ያለ ኢንተርኔት በቀላሉ ገንዘብ ያስተላልፉ!
- በሞባይልዎ የቼክ ደብተር ይዘዙ!
- የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ!
- ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ ያስተላልፉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
አንድ ወር የሚቆይ የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ!

በሚሊዮን ለሚቆጠሩ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች፥ የምልክት ቋንቋ መግባቢያቸው ነው። የምልክት ቋንቋን ይፋዊ የሥራ ቋንቋ ማድረግ ደግሞ ለበርካታ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች ምላሽና ለዕኩል እድል ተጠቃሚነት በር ከፋች ነው።

በዓለም ላይ 75 ሀገራት የምልክት ቋንቋን እንደ ብሔራዊ ቋንቋቸው መቀበልን ጨምሮ በሰነድ የተደገፈ ሕጋዊ እውቅና ሰጥተዋል፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ዙምባቡዌ ብሔራዊ ቋንቋቸው አድርገው ተቀብለውታል፡፡

በኢትዮጵያም የምልክት ቋንቋ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንጠይቅ!

በሀገራችን ይህ ተፈጻሚ እንዲሆን #እየተጠየቀ ነው። እርሶም ድምጽ በመስጠት፤ የተዘጋጀውን የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ በመቀላቀልና ለሌሎች በማጋራት #በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች ድምጽ ይሁኑ።

ለመፈረም፦ https://chng.it/zJwncqjqC5

በጉዳዩ ላይ ሞያዊ ሂስና አስተያየት ለመስጠት [email protected]

#HandsSpeakEyesListen
#እጆች_ይናገራሉ_አይኖች_ያዳምጣሉ
#AmharaRegion

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው መንገድ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ደጀን ከተማ ላይ ተዘግቷል።

በዚህ ምክንያት የሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጣል።

በዛሬው ዕለት ደግሞ የንግድ እንቅስቃሴ መቆሙ እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸው ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ የከተማው የሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ዘውዱ ተከታዩን ቃል ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ሰጥተዋል ፦

" ደጀን ከተማ የሚያስገባው መንገድ የተዘጋው ፤ የክልሉ ልዩ ኃይል መበተንን በሚቃወሙ ነዋሪዎች ነው።

ወጣቶች ተቃውሟቸውን ማሰማት የጀመሩት ከትላንት አርብ ከሰዓት ጀምሮ ነው።

ከቀኑ አስር ሰዓት ገደማ ላይ ተቃውሞ የሚያሰሙ ነዋሪዎች፤ ወደ ከተማዋ የሚያስገባው መንገድ ላይ ድንጋይ በማስቀመጥ የተሽከርካሪዎች ፍሰት እንዲቆም አድርገዋል።

በትላንቱ ተቃውሞ የፌደራል ፖሊስ ንብረት የሆነ አንድ ‘ፒክ አፕ’ ተሸከርካሪ ተቃጥሏል የሚል መረጃ እደርሶናል።

ድርጊቱን የፈጸመው አካል ማንነት ግን ገና አልተረጋገጠም። የትኛው ነው ያቃጠለው? ‘ወጣቱ ነው ወይስ ለመንግስትም ለህዝብም አልመች ያለ ጠላት ነው?’ የሚለውን ነገር አልደረስንበትም።

የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ተሰሚነት አላቸው በተባሉ ወጣቶች አማካኝነት፤  የነዋሪዎችን ተቃውሞ ለማረጋጋት ጥረት እየተደረገ ነው።

የሚደረገው ንግግር፤ በከተማይቱ በተነሳው ተቃውሞ ሰዎች እንዳይጎዱ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው። "

የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ በበኩላቸው ተከታዩን ብለዋል ፦

" ከደጀን ከተማ መግቢያ በተጨማሪ በከተማው የሚያልፈው መንገድ ተዘግቷል።

በደጀን በየሳምንቱ ይካሄድ የነበረው የቅዳሜ ገበያ በዛሬው ዕለት ሳይከናወን ቀርቷል።

ገበያ የመጣውም ህዝብ እንዲመለስ ተደርጓል። ሱቅም ተዘግቷል። የሰው እንቅስቃሴ አለ፤ ወጣቱ ላይ ታች ይላል። የንግድ እንቅስቃሴ ግን የለም።

ቅዳሜ በርካታ ህዝብ ገበያውን የሚያሳልጥበት ቀን ነው። ግን ዛሬ አንድም የለም። "

በደጀን ከትላንት አንስቶ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት ዛሬ ቅዳሜ ወደ ከተማዋ የመጣ ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪ አለመኖሩ ተነግሯል።

ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችም መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ዛሩ ወደ ባህር ዳር አውቶብሶችን አለማሰማራታቸውን አስታውቀዋል።

Credit : Ethiopia Insider

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

ዛሬ በአዲስ አበባ " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ይካሄዳል።

ምዕመናን ስትመጡ የሚከተሉትን እንዳትዘነጉ ፦

- ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ።

- የሰላት መስገጃ ይዞ መምጣት።

- ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

- የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር #ሰላም እና #ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

- ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎች እና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ አሳውቁ።

- በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia