TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዓለም አቀፍ ርብርብ የተዘጋው ድረገፅ " ጄነሲስ ማርኬት " !

የሰዎችን የይለፍ ቃሎች ጨምሮ የግል መረጃዎችን ለአጭበርባሪዎች በመሸጥ የሚታወቀው ድረ-ገጽ በአለም አቀፍ ፖሊስ ትብብር መዘጋቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

ድረገጹ በኢንተርኔት ላይ የማጭበርበር ስራ የሚፈጽሙ ግለሰቦች መረጃዎችን የሚሸምቱበት የዓለማችን ትልቁ የመረጃ መረብ ወንጀል ጣቢያ ሆኖ ቆይቷታ።

" ጄኔሲስ ማርኬት " የተሰኘው ድረገጽ የግለሰቦችን ዲጂታል የጣት አሻራዎችን ጨምሮ፣ አድራሻዎችን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለወንጀለኞች ሲሸጥ ነበር።

ከዚህ ድረገጽ የተገኙ የግል መረጃዎችና የይለፍ ቃሎች የግለሰቦችን #የባንክ_አካውንት ድና የኢንተርኔት ግዢዎችን በቀላሉ ወንጀለኞች እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ድረገጹ እነዚህንም መረጃዎች አብዛኛውን ጊዜም #ከአንድ_ዶላር ባነሰ ዋጋ ሲሸጥ ቆይቷል።

ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የፖሊስና ደህንነት አካላት በመቀናጀት ነው ይህንን የሳይበር የወንጀል ጣቢያ ያዘጉት።

ጉዳዩን በተመለከተ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የወንጀል ኤጀንሲ (ኤንሲኤ) ምን አለ ?

" በተከታታይ በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ድረገጹን ሲጠቀሙ የነበሩ 24 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዚህም መካከል ድረ-ገጹን በመጠቀም የማጭበርበር ስራ እየፈጸሙ ያነበሩ ግለሰቦችም ይገኙበታል። "

ማክሰኞ ረፋድ ላይ በተጀመረው ክትትልና ፍተሻ ከ17 አገራት የተውጣጡ ፖሊሶችና የደህንነት አባላት በቅንጅት ተሳትፈዋል።

ዘመቻው በአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ / #FBI / እና በኔዘርላንድ ብሄራዊ ፖሊስ የተመራ ሲሆን የዩኬው NCA፣ የአውስትራሊያ ፌደራል ፖሊስ እና በርካታ የአውሮፓ ሃገራት ተጣምረውበታል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ያህል ፍተሻዎች የተከናወኑ ሲሆን በዚህም 120 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ረቡዕ ዕለት ወደ ጀነሲስ ድረገጽ የገባ ማንኛውም ሰው ‘ኦፐሬሽን ኩኪ ሞንስተር’ የሚል ማስጠንቀቂያና ድረገጹም መቆሙን የሚያሳይ መልዕክት አግኝተዋል።

የጄኔሲስ ድረገጽ 80 ሚሊዮን የሚሆኑ የዲጂታል አሻራዎችና የግል መረጃዎችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የማጭበርበር ገበያ የተፈጸመበት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ነው " - መንግስት

መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ መጀመሩን አሳውቋል።

በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የልዩ ኃይል አባላት እንደ ምርጫቸውና እንደ ፍላጎታቸው ፦
- በመከላከያ፣
- በፌደራል ፖሊስ
- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ ብሏል።

በዚህ ሐሳብ ላይም ከልዩ ኃይል አመራሮችና አባላት ጋር ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።

ቀደም ብሎም በሁሉም ክልል አመራሮች ጥናት ተደርጎበት፣ በተገኘው ውጤት ያለምንም ልዩነት ውሳኔው ስምምነት ተደርሶበታል ሲል አስታውሷል።

የክልል ልዩ ኃይልን በተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች የማካተት ውሳኔና የተግባር እንቅስቃሴ በጥናት ላይ ተመሥርቶ የሚከናወን ነው ያለው መንግስት " ይህ አካሄድ የኢኮኖሚ ዐቅማችን በማሰባሰብ የሠራዊታችንን የሥልጠና፣ የትጥቅ እና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከፍተኛ ፋይዳ አለው፤ ይሄንን በመረዳትም በሁሉም ክልሎች ሂደቱ በመግባባትና በውይይት እየተከናወነ ይገኛል " ብሏል።

ነገር ግን በ " አማራ ክልል " በሚገኙ የተወሰኑ የልዩ ኃይል ክፍሎች ውስጥ ሂደቱን የሚያውኩ ተግባራት መታየታቸውን ገልጿል።

ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ የመልሶ ማደራጀት ሥራውንና ዓላማውን በአግባቡ ባለመረዳት፤ በሌላ በኩል የጥፋት አጀንዳ አራጋቢዎች ሆን ብለው በሚነዙት የሐሰት ወሬ በመጠለፍ ነው ሲል አስረድቷል።

መንግስት በመግለጫው ፤ " ከሚነዙት የሐሰት አጀንዳዎች መካከል፤ የመልሶ ማደራጀቱ መርሐ ግብር በአማራ ክልል ብቻ እየተካሄደ ነው፤ ሕወሐት ትጥቅ ሳይፈታ እንዴት የክልሉ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፈታል የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል " ብሏል።

" የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ነው። " ያለው መንግስት " ሥራውም በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኝ ነው። ሂደቱንም መንግሥት በጥናት፣ በዕቅድ እና በጥንቃቄ እየመራው ይገኛል። " ሲል አሳውቋል።

ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ተግባር በሚፈጸምበት ጊዜ በክልሎች አስተማማኝ ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ቦታዎች ሥምሪት መውሰዱ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ሕወሐት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንዲፈታ እየተደረገ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

" የሕወሐት ትጥቅ የመፍታት ሂደት በተፈረመው ስምምነት መሠረት ያለማወላወል የሚፈጸም እንጂ ከሌላ ሀገራዊ ዕቅድ ጋር የሚቀናጅም የሚጣረስም አይደለም። የሂደቱ ዋና ዓላማ የትኛውንም ልዩ ኃይል ትጥቅ ማስፈታት አይደለም " ሲል መንግስት አስረድቷል።

ዋናው አላማ ልዩ ኃይሉ ትጥቁን ይዞ እና የተሻለ ዐቅም ተፈጥሮለት በምርጫው መሠረት የክልል ፖሊስን፣ የፌደራል ፖሊስን ወይም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀል ማድረግ ነው። በዚህ ሂደት መካተት የማይፈልግ ማንኛውም የልዩ ኃይል አባል ካለ መብቱ ተጠብቆ ወደ መደበኛ የሲቪል ሕይወት እንዲገባ መንግሥት አስፈላጊውን የማቋቋም ሥራዎች ይሠራል ፤ እንዲቋቋምም ድጋፍ ያደርጋል ብሏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ነው " - መንግስት መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ…
#የክልል_ልዩ_ኃይል

አብን እና ባልደራስ ፓርቲዎች የመንግስትን እንቅስቃሴ ተቃወሙ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፤ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎችን አስመልክቶ ያሳለፈውን እቃወማለሁ ሲል አቋም ይዟል።

ፓርቲው ከሕጋዊነት ፣ ከወቅታዊ እና ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር በመመርመር የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና ማፍረስ ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎችን ተገማች እና ቀጥተኛ ለሆነ ጥቃት ተጋላጭ የሚያደርግ በመሆኑ ነው ውሳኔውን አጥብቆ የሚቃወመው።

አብን ፤ ገዢው ፓርቲ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ እንዳያደርግ ባሳስብም ማሳሰቢያዬን ወደጎን ትቶ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴ ውስጥ በመግባቱ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን ተገንዝቢያለሁ ብሏል።

የአማራ ልዩ ኃይልን ያለ በቂ ዝግጅት ፣ ውይይት ፣ የጋራ መግባባትና መተማመን ሳይደረስ በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና ለማፍረስ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ኃላፊነት የጎደለው እና ዳፋው በአማራ ክልል ብቻ ሳይወሰን በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚፈጥር ነው ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ክልሉን እና ሀገሪቱን ወደ ሌላ የቀውስ አዙሪት የሚከት አደገኛ አካሄድ በመሆኑ ድርጊቱ እንዲቆም ገዥውን ፓርቲ ፣ የፌዴራሉ መንግስት፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲሁም የሁሉም ክልሎች መስተዳደሮች በጥብቅ አሳስቧል።

የገዥው ፓርቲ (ብልፅግና) ሥራ አስፈጻሚ ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲቀለብስ እና ከአማራ ክልል መንግስት እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እና ምክክር እንዲደረግ እና የክልሉን እና የሃገራችንን ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ ውሳኔው እንዲከለስ አብን ፓርቲ ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የአማራ ልዩ ኃይል መፍረስን እንደሚቃወም ገልጻል።

ፓርቲው በመርህ ደረጃ የክልል ልዩ ኃይል መፍረስ እንዳለበት እና ሀገራዊ በሆነ ተክለ ሰውነት በተላበሰ የመከላከያ ሠራዊት መጠናከር እንዳለበት እንደሚያምን ከወቅታዊ ሁኔታዎች አንፃር እና አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ጉዳዩ ተቀባይነት እንደሌለው አቋሙን ገልጿል።

ባልደራስ ፓርቲ ፤ የፌዴራሉ መንግሥት የአማራ ልዩ ኃይል እንዲፈርስ ያስተላለፈድበሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ላይ በእኩል ደረጃና መጠን ተፈፃሚ  በማይሆንበት ሁኔታ ነው ያለ ሲሆን ይህ ደግሞ የአማራን ህዝብ ለጥቃት የሚዳርግ እኩይ ውሳኔ ስለሆነ እቃወማለሁኝ ብሏል።

(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ረመዷን

የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፣ የረመዷን ጾምን እየጾሙ ላሉ ዐቅመ ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ በታላቁ ቤተ መንግሥት ማድረጋቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

Photo Credit : PMO Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SpecialForce

" የሁሉንም የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማደራጀው ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ነው " - ፌዴራል መንግሥት

የፌዴራሉ መንግሥት ፤ በሁሉም ክልል ያለውን የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንደገና የማደራጀቱ ስራ  " ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት " ሲባል የሚደረግ ነው ብሏል።

መንግሥት ፤ የዚህ ተግባር ዓላማ ትጥቅ ማስፈታት አይደለም ያለ ሲሆን ስራውን ከሁሉም የክልል መዋቅር ጋር በመወያየት እና በመግባባት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ለዘላቂ የሀገር ጥቅም እና ድህንነት ሲባል የሚሰራው ስራ በጥንቃቄ እንደሚመራው ፌዴራል መንግሥት ህዝቡ እንዲያውቀው ብሏል።

ከዚህ ቀደም የክልል ልዩ ኃይሎች በሀገሪቱ ወዳሉት ሌሎች መዋቅሮች እንዲገቡ ህዝብም ጭምር ሲጠይቅ ነበር ያለው የፌደራል መንግሥት በዚህ መሰረት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደጀመረ አመልክቷል።

በልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ አባላት እንደምርጫቸው / እንደ ፍላጎታቸው ፦
- በሀገር መከላከያ ሰራዊት
- በፌዴራል ፖሊስ
- በክልል ፖሊስ አባልነት መካተት ይችላሉ። ወደነዚህ የፀጥታ መዋቅሮች የሚቀላቀሉት ትጥቃቸውን እንደያዙ ነው ተብሏል።

በዚህ ውስጥ መካተት የማይፈልጉ የልዩ ኃይል አባላት መብታቸው እንደሚጠበቅ እና ወደ መደበኛ ሲቪል ህይወት እንደሚገቡ መንግሥት የማቋቋም ስራ እና ድጋፍም እንደሚያደርግ የፌዴራል መንግሥት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ኢፍጣራችን ለወገናችን " ሶስተኛው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር የፊታችን ቅዳሜ ዕለት / ረመዳን 17 ይከናወናል ተብሏል። የዘንድሮው ኢፍጧል " ኢፍጧራችን ለወገናችን " በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። የቅዳሜው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሰዉ ሰራሽና በተፈጥሮ ምክንያት ጉዳት ያደረሰባቸዉና የተቸገሩ ወገኖቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ…
#ረመዷን

" ኢፍጣራችን ለወገናችን "

ምዕመናን ነገ መጋቢት 30 በአዲስ አበባ በሚካሄደው " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ሲመጡ ሊከተሏቸው ስለሚገቡ ደንቦች አዘጋጆች ይፋ አድርገዋል።

1. የተለመደውን ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ፤

2. የሰላት መስገጃ ይዘው ይምጡ፤

3. ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎችና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲያሳውቁ።

5. የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅት ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር ሰላምና ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

6. በዕለቱ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ ጥሪ ተላልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ ለተቸገሩ ወገኖች የሚሆን ፦
- እንደ ፉርኖ ዱቄት፣
- ሩዝ ፣
- ፓስታ፣
- መኮረኒ፣
- ዘይት፣
- የበቆሎ እህል፣
- ምስር፣
- የህፃናት የታሸጉ ብትን ወተቶች፣
- የሕፃናት አልሚ ምግቦች
- የንጽህና መጠበቂያ፣
- አልባሳት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይዞ መምጣት ይቻላል።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የክልል ልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማስገባት ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ነው " - መንግስት መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ የሚያስችል አንድ ጠንካራ የተማከለ ሠራዊት ለመገንባት አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። በዚህ መሠረት የየክልሉን ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የጸጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ…
#SpecialForce

" የክልል ልዩ ኃይሎች ከስመው በህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መጠቃለላቸውን እንደግፋለን " - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ፌደራልና የክልል ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ የማስገባት በጎ ጅምር አላስፈላጊ ውዥንብር ፈጥሮ ሌላ ሀገራዊ አደጋ እንዳይጋብዝ ጥንቃቄ ይፈልጋል ሲል አሳሰበ።

ፓርቲው ይህ ውሳኔ ከመዘግየቱ በስተቀር ተገቢነቱ ላይ ጥያቄ ሊነሳበት አይገባም ብሏል።

ባለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ከሕጋዊ አሠራር ውጪ እንዲቋቋሙ የተደረጉ የክልል ልዩ ኃይሎች በፌደራል መንግሥት የፀጥታ ዕዝ ሥር እንዲገቡ መደረጉ ተገቢም ልክም ሲል አቋሙን ገልጿል።

ፓርቲው የዘውግ ፖለቲካ ነፀብራቅ የኾኑ የክልል ልዩ ኃይሎች እየፈጠሩ ከነበረው ሀገራዊ አደጋ አንፃር ከስመው ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ እንዲገቡ ከዚህ በፊህ አቋሙን በተለያዩ ሁኔታዎች እና መድረኮች ላይ ሲያሳውቅ እንደነበር አስታውሷል።

የዚህ አቋሙ እና ስጋቱ ትክክለኛነት የትግራይ ክልል ልዩ ኃይሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ በከፈቱት ጦርነት በገሃድ ተረጋግጧል ብሏል።

ለአንድ ዘውግ ወይም ክልል ብቻ ጠባቂ ሆኖ የሚቋቋም ልዩ ኃይል ሀገር እና ሕዝብ ላይ አደጋ እንደሚፈጥር የታየው በትግራይ ክልል ታጣቂዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተመሳሳይ ዝንባሌ እየተስተዋለ ነው ሲል ገልጿል።

" በአስተዳደር ወሰን ይገባናል ጥያቄ መነሻ የኦሮሚያ ፣ የሶማሌ፣ የአማራ፣ የሲዳማ፣ የአፋር እና የቤንሻንጉል ልዩ ኃይሎች አንዳቸው ከሌላኛው ጋር መጋጨታቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው " ያለው ኢዜማ " ይህ ሁኔታ አሁንም ድረስ በአንዳንድ ክልሎች መካከል እየቀጠለ ነው፡፡ ይህም ንፁሀን ዜጎችን ከመጉዳቱም ባሻገር የሀገር ሉዓላዊነት ላይ አደጋ ደቅኗል፡፡ " ብሏል።

በመሆኑም፤ ከሕግ አግባብ ውጪ በአንድ ክልል ወይም ዘውግ ጠባቂነት የተቋቋሙ የክልል ልዩ ኃይሎች ከስመው በህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መጠቃለላቸውን የምንደግፈው ተገቢ ውሳኔ ነው ሲል አቋሙን ገልጿል።

ፓርቲው ምንም እንኳን የክልል ልዩ ኃይሎች ወደ ህጋዊ የፀጥታ መዋቅር ሥር መግባታቸውን ከልቡ የሚደግፈው ውሳኔ ቢሆንም አተገባበሩ ፈንጅ የማምከን ያህል ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚፈልግ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ሁሉ አሳስቧል።

በተለይም በሀገሪቱ ሥር ከሰደደው የዘውግ ፖለቲካ ጡዘት አኳያ አፈጻጻሙ በተጠና መልኩ መሆን አለበት ብሏል።

ለአብነት " በቅርቡ ከአሸባሪነት መዝገብ እንዲፋቅ የተደረገው የህወሓት ቡድን በሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን በኩል በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ሥር ያሉ አካባቢዎችን ስለማስመለስ እንደሚሠራ በስፋት እያስተጋባ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ይህንን ውሳኔ በጥድፊያ እና በድብቅ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር አደገኛ ውጤት እንደሚያመጣ የፌደራል መንግሥት ሊገነዘበው ይገባል " ብሏል።

" ህወሓት የታጠቃቸውን መሣሪያዎች መፍታቱ በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ የትግራይ አዋሳኝ ክልሎች ዳግም የመወረር ስጋት ቢያድረባቸው የሚያስወቅስ አይደለም " ያለው ኢዜማ የውሳኔውን አፈጻጸም ቅደም ተከተል በተመለከተ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አስገንዝቧል።

(የፓርቲው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia